ኢትዮጵያ ሰላም ከሌላቸው ሀገራት ተርታ ተሰለፈች

September 10, 2017 – ቆንጅት ስጦታው ኢትዮጵያ ሰላም ከሌላቸው ሀገራት ተርታ ተሰለፈች BBN   በህወሓት የምትመራው ኢትዮጵያ ሰላም ከሌላቸው ሀገራት ተርታ ተሰለፈች፡፡ ሀገሪቱ ከዚህ ቀደም በተደረገ ጥናት ሰላም እና መረጋጋት ከሌላቸው የዓለም ሀገራት 19ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣ የነበረ ሲሆን፣ አሁን ደግሞ ደረጃዋ ለውጥ አሳይቶ 15ኛ ደረጃ ላይ ልትቀመጥ መቻሏን አንድ ጥናት አመልክቷል፡፡ በዩናይት ስቴትስ በተደረገ […]

የአዋሽ ወንዝ ሙላት በኦሮሚያና በአፋር ሥጋት ፈጥሯል

09 Sep, 2017  By ውድነህ ዘነበ  ብሔራዊ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አደጋ ከተፈጠረ ምላሽ ለመስጠት ተዘጋጅቻለሁ አለ የቆቃ ኤሌክትክ ኃይል ማመንጫ ግድብ በመሙላቱና ለግድቡ ደኅንነት ሲባልም ከፍተኛ መጠን ያለው ውኃ እየተለቀቀ በመሆኑ፣ የሚለቀቀው ውኃም ከአዋሽ ወንዝ ገባሮች ጋር ተዳምሮ  በኦሮሚያና በአፋር ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል ሥጋት ፈጥሯል፡፡ የክረምት ወራት እየተገባደደ ቢሆንም፣ በተለይ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ […]

የጦርነት ሰነድ በሰላም ሰነድ ይተካ #ግርማ_ካሳ

  September 9, 2017 19:39 እዚህ ፎቶ ላይ የምታይዋቸው የሕወሃቱ መሪና የትግራይ ክልል ፕሬዘዳንት አቶ አባይ ወልዱ እና የብአዴኑ ምክትልና የአማራ ክልል ፕሬዘዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ናቸው። “በሁለቱ ክልሎች መካከል የነበረውን ችግር በዉይይት ፈተናል። ከዚህ በኋላ የድንበር ጥያቄ የለም” በሚል የተፈራረሙትን ወረቀት ወደ ላይ በማድረግ የተነሱት ፎቶ ነው። አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ይሄን ስምምነት ያደረጉት በኢሕአዴግ […]

የዘመን መለወጫ እና የጌታ ልደት ቀናት ለምን በአንድ ቀን ሳይውሉ ቀሩ? አዲስ ዓመትስ የሚገባው ስንት ሰዓት ላይ ነው? ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

 ምንም እንኳ ሰላምም፣ ጤናም ምንም በሀገር ባይኖር ከዚህች ሀገርና ሕዝቧ ጠላት ቅስፈት ሠውሮ ጠብቆ ለዚህ ዓመት ያደረሰንን አምላክ ማመስገን ይኖርብናልና እንኳን ለ፳፻፲ (2010) ዓ.ም. በሰላም አደረሳቹህ! ፈጣሪ አምላክ መድኃኔዓለም ክርስቶስ አዲሱን ዓመት የሰላም፣ የጤና፣ የደስታ፣ የፍቅር፣ የአንድነት፣ የድል፣ የነጻነት፣ የእድገት፣ የብልጽግና ያድርግልን አሜን!!! በርእሱ መጀሪያ ላይ ያነሣሁት ጥያቄ ብዙ ጊዜ ይነሣል፡፡ ቀጥሎ ያለው ጥያቄ ደግሞ […]

እየመረጡ በሁለት ሚዛን የመለካት አባዜ (በውብሸት ሙላት)

  Posted by admin | September 9, 2017 (ዐፄ ዘርዓያዕቆብን በማሰብ የተጻፈ)   በኢትዮጵያ ታሪክና ፖለቲካ ድርጊትና ሰዉ እየመረጡ በአባይ ሚዛን መሥፈርን ዐቢይ ተግባራቸው ያደረጉ ቡድኖች በርካታ ናቸው፡፡ ከድርጊት አንጻር፣ ከአገሪቱ አንድነት ጋር የሚገናኙትን በመምዘዝ፣ ከሰዎች ደግሞ ለአገሪቱ አንድነት ወደር የለሽ ተግባር የፈጸሙት ላይ ይገንናል፡፡ ድርጊቶቹን እንተውና መሪዎችን እንመልከት፡፡ መሪዎች ላይ ሲሆን ደግሞ ዐፄ ምኒልክና […]

የኢትዮጵያዊነት አረዳድ ላይ የእኔ አስተያዬት (በፈቃዱ ዘ ኃይሉ)

Posted by admin | September 9, 2017 (በኢንጂነር ይልቃል ጌትነት “ኢትዮጵያ ያለ ‹ኢትዮጵያዊነት› ልትኖር አይቻላትምን?” በሚል ለጻፍኩት ጽሑፍ የተሰጠ ምላሽ) በመጀመሪያ ይህ ፅሁፍ በፍቃዱ ኃይሉ በፃፈው ፅሁፍ ላይ የቀረበ ትችት በመሆኑ በተነሱ ነጥቦች ላይ ተመጣጣኝና አጭር ለማድረግ ሲባል የፅሁፉ አወቃቀርና ብስለት በሚጠበቀው መልኩ የእኔን የፖለቲካ አረዳድና እይታ ለአንባቢ ለማቅረብ አይመችም፡፡ በመሆኑም አንባቢ በፅሁፍ ለቀረቡ የመከረከሪያ […]

የዝምታየን ግድብ አስጣሰኝ – (ታምራት ታረቀኝ)

Posted by admin | September 9, 2017 ከተደጋጋሚ እስር በኋላ በቅረቡ ከተፈታው ወዳጄ ዳንኤል ሽበሺ ጋር ባለፈው ሳምንት በስልክ ተገናኘን፡፡ግንኑነታችን አንድም ከረዠም አመት በኋላ ሁለትም እሱ ከእስር በተፈታ ማግስት ቢሆንም በእንዴት ነህ አንዴት ነህ መጠያየቅ ብዙ አልቆየንም፡፡ አንዴ ተለክፈናልና ጭውውታችን ወደ ሀገር ጉዳይ ወደ ወቅታዊው የፖለቲካ ሁኔታ የገባው በደቂቃዎች ውስጥ ነበር፡፡ የአጠቃላይ የሀገራችን የፖለቲካ ሁኔታ […]

አሥራ ሁለት ተቃዋሚ ፓርቲዎች በጋራ ከገዢው ፓርቲ ጋር ለመደራደር ተስማሙ

09 Sep, 2017    By ነአምን አሸናፊ  ከገዥው ፓርቲ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ እየተደራደሩ የሚገኙ 12 ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የመደራደሪያ ሐሳባቸውን በጋራ ለማቅረብና ለመደራደር ወሰኑ፡፡ አሥራ ሁለቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በጋራ ለመደራደር መወሰናቸውን ያስታወቁት ሐሙስ ጳጉሜን 2 ቀን 2009 ዓ.ም. የየፓርቲዎቹ ተወካዮች፣ በመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ዋና ጽሕፈት ቤት […]

በሰሜን ጎንደር ዞን በዓመት ውስጥ 597 ታጣቂዎች መገደላቸው ተገለጸ

  09 Sep, 2017 By ዘመኑ ተናኘ   ከ700 በላይ ደግሞ ትጥቅ መፍታታቸው ተገልጿል በአማራ ክልል የሰሜን ጎንደር ዞን በ2009 ዓ.ም. ጫካ ገብተው ከነበሩ የታጠቁ ኃይሎች ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ 597 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ፡፡ የዞኑ አስተዳደርና ፀጥታ መምርያ ኃላፊ አቶ ዳኘው በለጠ ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ ኤርትራ በመሄድ ከግንቦት ሰባትና አርበኞች ግንባር ጋር ተቀላቅለው በመሠልጠን በዞኑ ሕዝብ […]

የእስራኤል ኩባንያ የኢትዮጵያ መንግሥትን በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ከሰሰ

09 Sep, 2017 By ቃለየሱስ የእስራኤል ኩባንያ የኢትዮጵያ መንግሥትን በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ከሰሰ ከግብር ጥያቄ ጋር በተያያዘ በአፋር ክልል የጀመረውን የፖታሽ ማዕድን ልማት ፕሮጀክት አቋርጦ የወጣው እስራኤል ኬሚካልስ (አይሲኤል) የተሰኘው ግዙፍ የእስራኤል ማዳበሪያ አምራች ኩባንያ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቴን አስተጓጉሎብኛል በማለት በዓለም አቀፍ የግልግል ፍርድ ቤት ክስ መሠረተ፡፡ ታማኝ የዜና ምንጮች ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ አይሲኤል […]