ወገኖቸ እንደ እነ ተጋዳላይ አቦይ ማትያስ ባሉ የወያኔ ቅጥረኞች የሚመራውና የሚዘወረው ሲኖዶስ ተብየ መንግሥት!” ለሚለው ፀረ ቤተክርስቲያን አካል ለማስመሰል ከሚያቀርበው ልመናና ተማጽኖ ውጭ አገዛዙ ኃላፊነቱንና ግዴታውን ተወጥቶ ሕዝበ ክርስቲያኑን ከመታረድ እንዲታደግ እስከማስገደድ በመሔድ ኃላፊነቱን ከመወጣት አንጻር ያደረገውን አንድ ነገር ልትነግሩኝ ትችላላቹህ???

በጎችን ከተኩላትና ከአራዊት እየተከላከሉ እንዲጠብቁ እረኝነት ተሾሙ ወይም ተቀጠሩ እንጅ ተኩላትና አራዊት በጎቹ ወዳሉበት በረት እየሰበሩ እየገቡ በጎችን እየተናጠቁ በአሰቃቂ ሁኔታ ቀረጣጥፈው ሲበሏቸው ዝም ብለው እየተመለከቱ ጸሎተ ፍትሐት አደረግን ነፍስ ይማር!” እያሉ እንዲያላግጡ ነው ወይ እረኝነት የተሾሙት ወይም የተቀጠሩት???

* የአገዛዙ የጸጥታ አካላት ቆመው እያዩ ባሉበት ሁኔታ ኃላፊነታቸውንና ግዴታቸውን ሆን ብለው ለመወጣት ባለመፈለግ ከፊታቸው ላይ ምእመናን እየታረዱ እንደሆነ ለእነኝሁ የሲኖዶስ አባላት ለሚባሉት እየተነገራቸው እየሰሙ፣

* “አድኑን ታደጉን!” ብለው ፖሊስ ጣቢያና ወደ መሰል የሕግ አካላት የተጠጉ ዜጎች ወይም ክርስቲያኖች አንገታቸውን እየታነቁ ተሰጥተው ከደጃቸው እንደ እባብ ተቀጥቅጠው እንደተገደሉ ተነግሯቸው ሰምተው እያሉ፣

* “የሕግ አካል ደኅንነታችንን ሊጠብቅና ከጥቃት ሊታደገን ካልቻለ ዝም ብለን ከምንሞት በቻልነው መጠን እራሳችንን እንከላከል!” ብለው ሕጋዊና ተፈጥሯዊ እራስን ከጥቃት የመከላከል መብታቸውን ተጠቅመው ባለ አቅማቸው አረመኔዎችን አጥቂዎች ለመከላከል የሞከሩትን ወጣቶች አረመኔው መንጋ ጥቃት ሲፈጽም ዝም ብሎ ሲያይና ጎሽ በርቱ!” እያለ ሲያበረታታና ሲያግዝ የነበረና በመግለጫም ሳይቀር ጃዋርን ዓይናችን ነው ለሱ የማንከፍለው መሥዋዕትነት የለም!” ያለ የአሸባሪዎች አጋር የጸጥታ አካል ነኝ ባይ አካል ለምን ዝም ብላቹህ አልታረዳቹህም!” በማለት እየለቃቀመ እያሰራቸው እንደሆነ ቤተሰቦቻቸው የደም እንባ እያነቡ ነግረዋቸው ወይም ተመልክቶላቸው ሰምተውና አረጋግጠውም እያለ እንደኃላፊነታቸው አንድ ነገር አድርገው አገዛዙ ተገዶ የዜጎችን ወይም የክርስቲያኖችን መብት፣ ደኅንነትና ህልውና እንዲጠብቅና እንዲያስጠብቅ፣ እንዲያከብርና እንዲያስከብር ማድረግ ወይም እየተፈጸመ ያለውን ግፍና አሻጥር ማስቆም ሲጠበቅባቸው እንደምታዩዋቸው ጸሎተ ፍትሐት!” እያሉና መንግሥትን ጠይቀናል!” እያሉ እያላገጡ ግፉ በዚያው እንዲቀጥል በዝምታ ከተባበሩ ጌታ በወንጌሉ ስለ መንጋው ወይም ስለበጎቹ እራሱን አሳልፎ የማይሰጥ ይልቁንም ለራሱ ፈርቶና ለጥቅም አድልቶ በጎችን ለተኩላና ለአራዊት የሚያስበላውን እረኛ ቅጥረኛ ወይም ምንደኛ!” ሲል እንደጠራቸው ማለት ናቸው እንጅ እነኝህ ምናቸው ነው መልካም እረኝነታቸው??? የቱ ላይ ነውስ ኃላፊነታቸውን የተወጡት???

ይሄ ቀደም ሲል በአቦይ ተጋዳላይ ጳውሎስ አሁን ደግሞ በተጋዳላይ አቦይ ማትያስ የወያኔ ቅጥረኞች የሚመራውና የሚዘወረው ሲኖዶስ ተብየ እስከዛሬም የምናውቃቸው ለአገዛዙ ቅጥረኛ ሆነው የቤተክርስቲያንን አከርካሪ ሲያሰብሩና መንጋውን ለተኩላትና ለአራዊት ሲያስበሉ ሲያስነጥቁ ነው፡፡ አሁንም ምንም የተለወጠ ነገር የለም እያስመሰሉ የአዞ እንባቸውን በማፍሰስ አከርካሪዋን ሰበርኩት!” ላለውና እንዲሰብርም ላገለገሉት፣ ላስቻሉት፣ ላደረጉት አገዛዙ የቀረውን ፀረ ቤተክርስቲያን የጥፋት ሥራውን ሠርቶ ወይም የፈለገውን አድርጎ ጨርሶ እንዲያጠፋት ለማድረግ በዚያው በኖሩበት ግብራቸው ነው ዛሬም ያሉት!!! ምንም የተለወጠና የሚለወጥ ነገር የለም!!! እንባ ሲያነቡ እናንተን ለማጃጃል ለማስመሰል እንጅ እውነት እንዳይመስላቹህ!!! ከፈለጋቹህ የአዞ እንባ ማፍሰስ አይደለም ሌላም ሊያደርጉላቹህ ይችላሉ፡፡ ሰዎቹ አጋንንትን ቁጭ አድርገው ተንኮል፣ ሸፍጥ፣ ሴራ፣ ደባ፣ አሻጥር ማስተማር ማሠልጠን የሚችሉ ከአጋንንትም አጋንንት ናቸው!!!

ይሄ የወያኔ ቡድን እራሱ ባለፈው እርር ድብን በሉ!” ለማለት ፈራ ተባ እያለ በከፊል ቀንሰው በነገሩን አኀዝ መሠረት ቤተክርስቲያን ወያኔ ከገባ ሃያ ሚሊዮን ምእመናን ወይም ግማሽ በግማሽ የሚቃረብ መንጋዋ በመናፍቃን ተበልቶባታል ወይም ተወስዶባታል!!!

ቤተክርስቲያን ይሄ ሁሉ መንጋ ሲበላባት፣ አጥቢያዎቿ ምእመን አጥተው ሲዘጉና የየአጥቢያው ይዞታ በመናፍቃን ሲወረስ ያላለቀሱና እግዚኦ በሉ!” ያላሉ ዛሬ መቶ ሁለት መቶ ክርስቲያኖች ሲታረዱ ወይም ሠማዕትነት ሲቀበሉ ሊያለቅሱና እግዚኦ በሉ ሊሉ አይችሉም!!! ለቤተክርስቲያን የከፋው ጉዳትና ኪሳራ የትኛው ነው??? ጭራሽስ ይመጣጠናል ወይ??? ስለሆነም እንባው የማስመሰል የአዞ እንባ ነው!!!

እናም እባካቹህ ሕዝበ ክርስቲያን ሆይ! አስመሳይ ቅጥረኞቹ በሚያፈሱት የአዞ እንባ እየተታለልን አንዘናጋ!!! እውነት ለቤተክርስቲያን የሚያስቡ፣ የሚቆረቆሩ፣ የሚገዳቸው ከሆነ እንደተጣለባቸው ኃላፊነት ማድረግ የሚጠበቅባቸውን ሁሉ አድርገው አገዛዙ የዜጎችን መብት፣ ደኅንነትና ህልውና እንዲጠብቅና እንዲያስጠብቅ፣ እንዲያከብርና እንዲያስከብር እንዲያስገድዱት ጫና እናሳድር ግፊት እናድርግ!!! ከዚህ ውጭ ያለው ነገር ሁሉ መጃጃል ነው!!! የአጋንንታዊ ድራማቸው መጫወቻ መሆን ነው!!!

ሲኖዶስ ተብየው በአስመሳዮቹ በእነ ተጋዳላይ አቦይ ማትያስ ባሉ የወያኔ ቅጥረኞች የሚመራና የሚዘወር በመሆኑና እነ አቦይ ማትያስ ቤተክርስቲያንን አከርካሪዋን ሰበርኩት ያለው አገዛዝ ጨርሶ እንዲያጠፋት ስለሚፈልጉ ነው እንጅ ሲኖዶሱ አገዛዙ ይሄንን እየተፈጸመ ያለውን አረመኔያዊ ግፍ እንዲያቆምና እንዲያስቆም ማድረግ ቢፈል በቀላሉ እንዲያቆም ማድረግ ይችላል!!!

እንዴት አድርጎ?” ብትሉ ቃታ ስበው ወይም ሌላ ምንም አድርገው ሳይሆን እንደ ቆራጡ፣ ቅዱሱ ሠማዕት አቡነ ጴጥሮስ ሥልጣነ ክህነታቸውን ተጠቅመው ሁሉንም ነገር ቀጥ ማድረግ ይችላሉ፡፡ ቤተክርስቲያኗ ያሏትን ተከታዮች በሙሉ የሥራ ማቆም አድማ እንዲያደርጉ፣ ለአገዛዙ እንዳይታዘዙና እንዳይተባበሩ ብትገዝት ሕዝበ ክርስቲያኑ በደስታ እንደሚታዘዛቸውና አገዛዙም እንደሚንበረከክ ጠፍቷቸው ይመስላቹሃል ይሄንን የማያደርጉት??? ቅዱሱ ሠማዕት አቡነ ጴጥሮስ ያደረጉት እኮ ይሄንን ነው ሌላ አይደለም!!! “ለፋሽስት ጣሊያን ሰውም ምድሪቱም እንዳትገዙ፣ እንዳትታዘዙ፣ እንዳታገለግሉ የተገዘታቹህ ሁኑ!” ነው እኮ ያሉት ሌላ አላሉም!!!

ተጋዳላይ አቦይ ማትያስ እኔ ሽጉጥ የለኝም በእጀ ያለው መስቀል ነው መንግሥትን ላስገድድ አልችልም፡፡ ወደ አምላክ ከማልቀስ ውጭ ሌላ ላደርገው የምችለው ነገር የለም!” ሲል እንደ ቅዱሱ ሠማዕት አቡነ ጴጥሮስ መገዘትና አገዛዙን ማንበርከክ እንደሚቻል ጠፍቷቸው እንዳይመስላቹህ!!! የአገዛዙ ቅጥረኛ ስለሆኑና አገዛዙ ተንበርክኮ ከፀረ ቤተክርስቲያን የጥፋት ሥራው እንዲገታ ስለማይፈልጉ ነው ወገኖቸ አትታለሉ!!!

በዚህ አካጣሚ ቅዱስ ፓትርያርኩን ማለትም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ቀዳማዊ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያን ጨምሮ አራት አምስት ለሚሆኑት ሐቀኛ ጳጳሳት ማስተላለፍ የምፈለገው መልእክት ቢኖረኝ በፀረ ቤተክርስቲያኑ በዚህ አገዛዝ ቅጥረኞች የሚዘወረውን ሲኖዶስ ተብየ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ማድረግ የሚቻል ካልሆነባቹህ ይሄ ግፍ መቀጠል የለበትምና ከዚህ የከፋም የለምና በየግላቹህ በመንቀሳቀስ ማድረግ የሚጠበቅባቹህን እንድታደርጉ አጥብቄ ማሳሰብ እወዳለሁ!!!

ድል ለቤተክርስቲያን!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

amsalugkidan@gmail.com