October 29, 2019
Source: https://mereja.com/amharic/v2/164338

በተለያዩ የምርመራ መዝገቦች በሽብር ትጠረጠራላችሁ በሚል ለወራት በእስር ላይ ሆነው ምርመራ ሲደረግባቸው የቆዩ ሰዎች ዛሬ ከእስር ተፈተዋል፡፡ እስረኞቹ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አባላት፣ የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት አመራሮች፣ ጋዜጠኞች እና ሌሎች ከሰኔ 15 የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በተያያዘ ተጠርጥራችኋል በሚል ታስረው የነበሩ ይገኙበታል፡፡
ከተፈቱት መካከል፣
1ኛ) አንተነህ ስለሺ
2ኛ) ንጉሡ ይልቃል
3ኛ) ዮናስ አሰፋ
4ኛ) ሽገዛ ሙሉጌታ
5ኛ) በዕውቀቱ በላቸው
6ኛ) ኤልያስ ገብሩ
7ኛ) መርከቡ ኃይሌ
8ኛ) ስንታየሁ ቸኮል
9ኛ) ወ/ሮ ደስታ አሰፋ
10ኛ) ምስጋና ጌታቸው
11ኛ) ጌታቸው አምባቸው
12ኛ) ሲያምር ጌቴ
እና ሌሎችም እንደሚገኙበት የታወቀ ሲሆን፣ የአብን ከፍተኛ አመራሮች የሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ እና አቶ በለጠ ካሳ ዛሬ ከሚፈቱት መካከል ይሁኑ አይሁኑ ግን እስካሁን ማረጋገጥ አልተቻለም፡፡