Socepp Can
በትግራይ ውስጥ ያሉ የድብቅ እስረኞች ጉዳይ አሁንም ምላሽ ይጠይቃል
በትግራይ ውስጥ እጅግ ብዙ መዳረሻቸው ያልታወቀ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ እባሎችና አመራሮች በድብቅ እስር ቤቶች ታፍነው እየተሰቃዩ እንደቆዩ ሲነገር ቆይቷል። ከነዚሀም ውስጥ የኢሀአፓ ብርቅ ታጋዮችና አመራሮች ይገኛሉ።
በዚሀ አኳያ አሁን በ ትግራይ ውስጥ እየተካሄደ ባለው ትግል ውስጥ እነዚሀ በስቃይ ውስጥ የሚገኙ ታጋዩች የስብአዊ መብት ሰለባዎች የት እንዳሉ አፈላልጎ ለነጻነት እንዲበቁ አስፈላጊውን ሁሉ ማደረግ የመንግስትና የሰራዊቱ አንዱ ሀላፊነት እንደሆነ በድጋሚ ልናሳስብ እንወዳለን።
ጠቅላይ ሚኒሰቴር አብይ በመጀመሪያው የ ዋሽንግተን ዲሲ ጉዟቸው ሰለዚሀ ጉዳይ ተጠይቀው በስጡት ምላሽ እነዚሀን እስረኞች ማፈላለግ የኛም ሀላፊነት ነው እኛንም እጅግ ያሳስበናል አብረን እናፈላልጋለን ብለው የሰጡትን ቃል መንግስታቸው አጽንኦት ሰጥቶ እንዲተረጉም እጅግ አጥብቀን እናሳስባለንሁሉም ነጻ ሳይሆን ማንም ነጻ አይሆነም
—–
ይህ ጉዳይ ተኩረት እንዲያገኝ ሽር በማድረግ ተባበሩን