published:May 19, 2021

ኢትዮጵያ  በኤቲኤም ማሽኖች ስርጭትና ድርሻ  ከዓለም 179 አገራቶች 178ኛ ደረጃ አገኘች !!!    (ክፍል ሁለት)    ሚሊዮን ዘአማኑኤል (ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY

ለዲጂታል ባንኪንግ ፀሓይ ወጣች!   The Sun Is Rising on Digital Banking in  Ethiopian

በኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ለሚገኙ አስተማሪዎችና ተማሪዎች ለውይይት የቀረበ ቁንፅል መነሻ ጥናት

የመንግሥት የፖለቲካ ጣልቃገብነት  ከባንክ አሰራር ውስጥ ይውጣ!!!

የሰው ኃይል ልማት ሳይደረግ የሠላሳ ስድስት ወለል ፎቅ ግንባታ ያስጀመሩት የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ተክለወልድ አጥናፉ ግብረ አበሮቻቸው  የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው በመሰየማቸው ያለፈው የባሌስትራ ወርቅ ቅብ የሙስና ስራቸው እና ሃገሪቱን በብድር እዳ ከተው ሳይጠየቁ ዛሬ የባንክ ሙያተኛውን የተተኪ ድርቀት በማለት እነዚህ የፖለቲካ ካድሬዎች በህወሓት፣ብአዴን፣ ኦህዴድ፣ ደኢህዴን ካድሬነት ባንኮቹ እንደሚዘወሩ የጠፋቸው ይመስላል፡፡ ብዙ የባንክ ሙያተኛ የናንተን የበሰበሰ ፖለቲካ ውስጥ ስላልገባ ሥልጣን አልተሰጠውም እንጂ በሃገር ውስጥና ከባህር ማዶ ያሉ የባንክ ሙሁራንን አላሰራም ብለችሁ እንጂ የተተኪ ድርቀት ኖሮ አይደለም፡፡  የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ ዋና ቢሮ ባለ 46 ወለል ያለው ፎቅ የግንባታው ወጪ በ266.5 ሚሊዩን ዩኤስ ዶላር ወይም 6 ቢሊዩን 129 ሚሊዩን 500 ሽህ  ብር ኮንትራክተር፤ የቻይና መንግስት የኢንጅነሪንግ ግንባታ ኮርፖሬሽን China State Construction engineering Corporation (CSCEC)፤ በአዲስ አበባ ከተማ ሥራው ተጠናቆ ለምርቃት ኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ ፖለቲከኞች እንደ ምርጫ ቅስቀሳ ሸር ጉድ በማለት ለምረቃ በዓሉ ሃመሳ ሚሊዩን ብር በላይ በማውጣት በአገር አቀፍ ደረጃ ለማስመረቅ ላይ ይገኛሉ፡፡ የሃገሪቱ ዜጎች ከአምስት ሚሊዮን ህዝብ በላይ  አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል፡፡

በአውቶማቲክ ቴለር ማሽኖች (ኤቲኤም) አስራአንድ ጠቀሚ አሰራሮች ለዓለም ህዝብ አበርክተዋል፡፡ እነሱም  ፈጣን አገልግሎት፣ ተስማሚ፣ ሃያ አራት ሰዓት የሚሠራ፣ የደንበኛው አድራሻ ቦታ የትም ቢሆን የማይገደው፡፡ በተጨማሪ በኤሌክትሮኒክ ባንኪንግ ባንኩ አገልግሎት በመስጠት  አስተማማኝና ዘለቄታዊ አገልግሎት በርካሽ ዋጋ ይሰጣል፡፡ ለምሳሌ፡- በጡብና ሞርታል የባንክ አገልግሎት ዘመን አንድ ደንበኛ የአገልግሎት ወጪ አንድ ዶላር ሲሆን ደንበኛው በስልክ ከተገናኘ ስልሳ ሣንቲም ይከፍላል፡፡ በዘመናዊው ኤሌክትሮኒክ ባንኪንግ የገፅ ለገፅ አገልግሎት ወጪው ዚሮ ነጥብ ዚሮ ሁለት ሣንቲም  ብቻ ነው፡፡  ‹‹The Electronic banking has been around for some time but in form of Automatic Teller Machines (ATMs) and telephone transactions. More recently, it has been transformed by the Internet and mobile technologies, the new delivery channels for banking services with 11 benefits to both customers and banks. Access is fast, convenient, and available around the clock, whatever the customer’s location. Additionally through Electronic banking, the banks are able to provide services more efficiently and at substantially lower costs. For example, a typical customer transaction costing-about $1 in a-traditional- “brick and mortar” bank branch or $0.60 through a phone call costs only about $0.02 online (Crane, 1996).››

በ2009 ዓ/ም በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙት አውቶማቲክ ቴለር ማሽኖች (ኤቲኤም) 1,700 (አንድ ሽህ ሰባት መቶ) ብቻ ናቸው፡፡ ከአጠቃላይ የህዝብ ብዛት ጋር ሲካፈል አንድ ኤቲኤም ማሽን 54,117 (ለሃምሳ አራት ሽህ አንደ መቶ አስራሰባት) ሰዎችን ያገለግላል፡፡ በዓለም አገሮች አማካይ አንድ ኤቲኤም ማሽን 2,325 (ለሁለት ሽህ ሦስት መቶ ሃያ አምስት) ሰዎች ያገለግላል፡፡ ኢትዮጵያ ሃገራችን ለ110 (መቶ አስር) ሚሊዮን ህዝብ የአለም አማካይ ላይ ለመድረስ 47,312 (አርባ ሰባት ሽህ ሦስት መቶ አስራ ሁለት) ተጨማሪ ኤቲኤም ማሽኖች አገራችን ውስጥ ማስገባት ይኖርብናል ማለት ነው፡፡ ሰማይ ጠቀስ ፎቆች ከመቆለል ኤቲኤም ማሽኖች አገራችን ውስጥ አስገብቶ በማሰራጨት የብዙ ቅርንጫፍ ባንኮች ሥራ በመስራት ባገለገሉ ነበር እንላለን፡፡ ‹‹ There are about 1,700 ATMs in Ethiopia, making the ATM to population ratio 1: 54,117, well below the world average of 1:2325.Jan 24, 2017 (https://addisfortune.net › columns › atm-woes-plague-cust…)››

በአሜሪካ ሃገር 470,135 ኤቲኤም ማሽኖች ሲኖሩ 181,741 በባንክ ኃብትና ንብረት ሲሆኑ 278,394 የነፃ የግል ዘርፍ ሃብት ነው:: (Currently, there are approximately 470,135 ATMs in the U.S., with 191,741 bank-owned and 278,394 independent.) በኢትዮጵያም የባንኮችና የግል ዘርፍ ኤቲኤም ማሽኖች እንዲኖሩ በማድረግ ልዩነቱን ማጥበብ ይቻላል እንላለን፡፡

ደቡብ ኮሪያ 282 ኤቲኤም ማሽኞች ለመቶ ሽህ ሰዎች፣ ካናዳ 205፣ ፖርቱጋል 185፣ ጀርመን 118   ኤቲኤም ማሽኞች ለመቶ ሽህ ሰዎች የስርጭት ድርሻ አላቸው፡፡ በቻይና 1.1 (አንድ ነጥብ አንድ) ሚሊዮን ኤቲኤም ማሽኖች ይገኛሉ፡፡ ኢትዮጵያ 0.46 (ከአንድ በታች)  ኤቲኤም ማሽን ስርጭት  ለመቶ ሽህ ሰዎች  ይደለደላል፡፡  ኤቲኤም ማሽኖች ስርጭትና ድርሻ  ከዓለም 179 አገራቶች ኢትዮጵያ 178ኛ ደረጃ አገኘች !

በ2013 ዓ/ም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መረጃ መሠረት በሃገሪቱ ለዘመናዊ የባንክ አገልግሎት የሚጠቀምባቸው በዚህ መሠረት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙት አውቶማቲክ ቴለር ማሽኖች (ኤቲኤም) 3,083 (ሦስት ሽህ ሰማንያ ሦስት) አድጎል፡፡ ከአጠቃላይ የህዝብ ብዛት ጋር ሲካፈል አንድ ኤቲኤም ማሽን 35,680 (ለሠላሣ አምስት ሽህ ስድስት መቶ ሰማንያ) ሰዎችን ያገለግላል፡፡ በዓለም አገሮች አማካይ አንድ ኤቲኤም ማሽን 2,325 (ለሁለት ሽህ ሦስት መቶ ሃያ አምስት) ሰዎች ያገለግላል፡፡

በአውቶሜትድ ቴለር ማሽኖች (ኤቲኤም) ከመቶ ሽህ አዋቂዎች (Automated teller machines (ATMs) (per 100,000 adults)) ከ179 የዓለም አገራቶች ደረጃ፣ የኢትዮጵያ 178ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ (ከሠንጠረዡ መመልከት ይቻላል)ኤቲኤም ማሽኖች ኮንቲውተራይዥድ የሆነ የቴሌኮሙኒኬሽን ስትራቴጂክ ፕላን ሲሆን ለፋይናንሻል ኢንስቲቲውሽኖች ደንበኞቹ በህዝባዊ ቦታዎች በማመቻቸት የሚሠጠው የገንዘብ ግብይይት አገልግሎት ነው፡፡ Definition: Automated teller machines are computerized telecommunications devices that provide clients of a financial institution with access to financial transactions in a public place.

ከጡብና አዳፍኔ ዘመን ወደ ዲጂታል ባንኪንግ ዘመን ለመሸጋገር በ2013ዓ/ም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መረጃ መሠረት በሃገሪቱ ለዘመናዊ የባንክ አገልግሎት የሚጠቀምባቸው አውቶማቲክ ቴለር ማሽኖች (ኤቲኤም) 3,083 (ሦስት ሽህ ሰማንያ ሦስት) እንደደረሰ ተገልፆል፡፡ በዚህም መሠረት በአንድ አገር የሚገኙ የኤቲኤም ማሽኖች  ስርጭት ለመቶ ሽህ ሰዎች የሚሠጡት አገልግሎት የሚመዘንበት መረጃ የሃገሪቱ ደረጃ የሚያሳይ ሪፖርት ነው፡፡ በዚህም መሠረት ሲሠላ በሃገሪቱ ውስጥ የሚገኘው ኤቲኤም ማሽኖች ቁጥር ሲባዛ ለመቶ ሽህ ሰዎች ሲካፈል ለጠቅላላው የህዝብ ብዛት አዋቂ ሰዎች ያካትታል፡፡ ስለዚህ 3,083 x 100,000=308,300,000/ሲካፈል ከጠቅላላ የህዝብ ቁጥር አዋቂ ሰዎች ይሆናል 0.46 ሆኖ የመቶ ሰባ ስምንተኛ ደረጃ ተሠጥቶታል፡፡

Statistical Concept and Methodology: Data are shown as the total number of ATMs for every 100,000 adults in the reporting country. Calculated as (number of ATMs)*100,000/adult population in the reporting country. …….(2)

Development Relevance: Access to finance can expand opportunities for all with higher levels of access and use of banking services associated with lower financing obstacles for people and businesses. A stable financial system that promotes efficient savings and investment is also crucial for a thriving democracy and market economy. There are several aspects of access to financial services: availability, cost, and quality of services. The development and growth of credit markets depend on access to timely, reliable, and accurate data on borrowers’ credit experiences. Access to credit can be improved by making it easy to create and enforce collateral agreements and by increasing information about potential borrowers’ creditworthiness. Lenders look at a borrower’s credit history and collateral. Where credit registries and effective collateral laws are absent – as in many developing countries – banks make fewer loans. Indicators that cover getting credit include the strength of legal rights index and the depth of credit information index.

General Comments: Country-specific metadata can be found on the IMF’s FAS website at  http://fas.imf.org.

2013 / በኢትዮጵያ የዲጂታል ባንክ አገልግሎት

በኢትዮጵያ የዲጂታል ባንክ አገልግሎት ደንበኞች ቁጥር መጨመር የዲጂታል ባንኪንግ ቴክኖሎጂ እውቀት በደንበኞች ዘንድ መስፋፋቱን አመላካች ነው፡፡ በኢትዮጵያ የዲጂታል ባንክ አገልግሎት በኤቲኤም፣ በሞባይል፣ በኢንተርኔትና መሰል ዘመናዊ የባንክ አገልግሎት በመጠቀም ደንበኞች ወደ ቅርንጫፍ ባንኮች ሳይመጡ  የተለያዩ አገልግሎቶች ማግኘት ችለዋል፡፡ የባንክ ኢንዱስትሪው የዲጂታል ባንክ አገልግሎት እንዲስፋፋና የተጠቃሚዎች የደንበኛ ቁጥር ብዛት መጨመር አዲስ ምዕራፍ ከፍቶል፡፡ በዚህም የተነሳ የተጠቃሚዎች ቁጥር በማደጉም የሚንቀሳቀሰው የገንዘብ መጠን እየጨመረ ሄዶል፡፡ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መረጃ መሠረት  የዲጂታል ባንክ አገልግሎት ደንበኞች የሚደረገው የገንዘብ እንቅስቃሴ ከፍተኛውን ደረጃ መያዙን አሃዙ ያስያል፡፡ በዓለማችን የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በሽታ መዛመት የተነሳ ወደ ቅርንጫፍ ባንክ ሠራተኞች ዘንድ ከመሄድ ደንበኞች ታቅበዋል፡፡ በኮቪድ መከሰት ምክንያት የዲጂታል ባንኪንግ አጠቃቀም በህብረተስብ ዘንድ ተጠናክሮ ቀጥሎል፡፡ በኢትዮጵያ ዲጂታል ቴክኖሎጂ እንዲስፋፋ የዲጂታል ባንክ አገልግሎት  ማሽኖች ኤቲኤም፣ ሞባይል፣ በኢንተርኔት ወዘተ ኢንቨስትመንት ጠቀሜታ ከባንኮች ሰማይ ጠቀስ ፎቆች ግንባታ አስር እጅ ይልቃል እንላለን፡፡ በኢትዮጵያ የዲጂታል ፋይናንስ ቴክኖሎጂ አገልግሎትና አጠቃቀም የባንኮች አፈፃፀም መረጃ መሠረት፡-

በ2013ዓ/ም የዚህ ገንዘብ እንቅስቃሴ መብዛት ትልቅ ትርጉም ያለው መሆኑን የጠቀሱት አቶ አቤ፣ በዚህ አገልግሎት የሚጠቀሙ ደንበኞች ቁጥርም እያደገ መምጣቱን አክለዋል፡፡

ምንጭ፡

(1) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል ባንኪንግ ተጠቃሚዎች ቁጥር መጨመሩን አስታውቋል/5 May 2021

(2) Countries ranked by Automated teller machines (ATMs) (per 100,000 adults) (indexmundi.com)

(3) ATMs machine – Google Search