May 21, 2021


የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኢሶዴፓ)ፕሬዚዳንትና የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር -ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ “ጦርነት በሌለበትና ተዋጊ የሆኑ ሁለት ኃይሎች በማይታዩበት ሁኔታ ተኩስ አቁሙ ማለት ግራ የሚያጋባ ውሳኔ ነው” ብለዋል፡፡

ፕሮፌሰር በየነ በተለይም ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳሉት፣ “ በሰላም ተነጋግራችሁ ችግራችሁን ፍቱ የሚለው አባባል የተለመደ ነው፤ ነገር ግን ጦርነት በሌለበትና ተዋጊ የሆኑ ሁለት ኃይሎች በማይታዩበት ሁኔታ ተኩስ አቁሙ ማለት ግራ የሚያጋባ ነው” ብለዋል::

እንደ ፕሮፌሰር በየነ ገለጻ፣ ይህ አሁን ያሉትም የተኩስ አቁሙም ሆነ ተደራደሩ የሚለው ሃሳባቸው እውነታውን የሚያሳይ ነው ወይ? ወይም ደግሞ ኢትዮጵያን የሚመለከት ነው፤ አይደለም? የሚለውን በጥንቃቄ ማየት ያስፈልጋል::

ይህ አባባል “ህወሓት አሁንም እየተዋጋ ነው፤ የኢትዮጵያ መንግሥትም በትግራይ ክልል ውስጥ ጦርነት ላይ ነው፤” የሚል እንደምታ ያለው ነው ያሉት ፕሮፌሰር በየነ ነገር ግን የመንግሥት አቋምም ሆነ መሬት ላይ ያለው እውነት ህገወጥ የሆኑ ኃይሎች ላይ እርምጃ በመውሰድ ወንጀል የፈጸሙትን አድኖ የመያዝ ሂደት መሆኑን አብራርተዋል::

በመሆኑም ጦርነት በሌለበትና ተዋጊ የሆኑ ሁለት ኃይሎች በማይታዩበት ሁኔታ ተኩስ አቁሙ ማለት ትንሽ ግራ የሚያጋባ በመሆኑ ይህንን አቋማቸውን ከቻሉ ሰላማዊ መንገድ ፈልጉ፤ የሚሸሹትንም ጁንታዎች ሽሽታችሁን አቁማችሁ ለህግ ተገዙ በማለት ለማስማማት ቢሞክሩ የተሻለ እንደሚሆንም ጠቅሰዋል::

EPA