May 27, 2021


የግብፁ ፕሬዝደንት አብዱልፈታህ አል ሲሲ ከጂቡቲ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት እስማኤል ኦማር ጌሌ ጋር ለመወያየት ዛሬ ማለዳ ወደ ጅቡቲ አቅንተዋል፡፡

– የፕሬዚዳንቱ የጅቡቲ ጉብኝት በዓይነቱ የመጀመሪያ ነው ተብሏል።

– የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በጋራ ትብብር እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚወያዩ ታውቋል። በተለይም በፀጥታ ፣ በወታደራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች የሁለቱን ሀገራት ትብብር ማጠናከር የውይይቱ ዓላማ መሆኑ ተጠቁሟል።

– የግብፅና የጅቡቲ መሪዎች የጋራ በሆኑ ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት እና ሀሳቦችን ለመለዋወጥም አቅደዋል፡፡

ግብፅ እና ኬንያ በትናንትናው እለት ወታደራዊ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

– በናይሮቢ የተፈረመው ስምምነት ዓላማ የሁለቱን ሀገራት የጋራ ጥቅም ለማስጠበቅ የሚደረገው የሁለትዮሽ ትብብር አካል ነው።

– ግብፅ ከኬንያ ጋር ያደረገችው ወታደራዊ ስምምነት እ.ኤ.አ. በ2021 በምስራቅ አፍሪካ ከሚገኙ ሀገራት ጋር ያደረገችው አራተኛ ስምምነት ነው፡፡

– ከኬንያ በተጨማሪ ከሱዳን ፣ ከኡጋንዳ እን ከብሩንዲ ጋር ግብፅ ወታደራዊ ስምምነት ፈርማለች፡፡

ግብፅ እና ሱዳን በትናንትናው ዕለት ለ 6 ቀናት የሚቆይ ሁለገብ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ በሱዳን ጀምረዋል፡፡

ኢትዮጵያ በሕዳሴው ግድብ ጉዳይ ከሁለቱ ሀገራት ጋር ውጥረት ውስጥ በምትገኝበት በዚህ ወቅት የሚካሔደው ይህ ልምምድ ፣ የናይል ጠባቂዎች (Nile Protectors/ናይል ፕሮቴክተርስ) የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡