
By admin May 27, 2021
ቦርዱ በእስር ላይ የሚገኙት የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አመራሮች የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ግንቦት 13 ቀን 2013 ዓ.ም ያሳለፈውን ውሳኔ ለመፈፀም እንደሚቸገር በትናንትነው ዕለት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
ለዚህ እቸገራለሁ ላለበት ውሳኔ እንደ ምክንት ያስቀመጠው የዕጩዎች ምዝገባ የካቲት 30 ቀን 2013 ዓ.ም በመጠናቀቁ፣ እያንዳንዱ ዕጩ ተወዳዳሪች በድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ የሚኖረውን ስፍራ የሚወስን ሎተሪ ዕጣ በመውጣቱና በዚሁ መሠረት የድንፅ መስጫ ወረቀት ህትመት ተጠናቆ ወደ ምርጫ ጣቢዎያዎች በቅርብ ባለው ጊዜ የሚጀመር በመሆኑ ነው፡፡
ከአንድ ሳምንት በፊት ምርጫው የሚካሄድብትን ዕለት ይፋ ያደረገው ቦርዱ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር(ኦነግ) በምርጫው እንደማይሳተፍ አስታውቆ ነበር፡፡ ከዚህ ውሳኔ አስቀድሞ የልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ኦነግ በመጋቢት 4 ቀን 2013 ዓ.ም ያደረገውን ጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ በስብስባው ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች ቦርዱ እንዲቀበል ቢበይንም ልክ እንደ ባልደራስ ሁሉ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ሳያስተናግደው ቀርቷል፡፡
ቀን 19/09/2013
አሐዱ ራድዮ 94.3

Previous article