September 23, 2024 – Konjit Sitotaw 

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር፣ ባኹኑ ወቅት በትግራይ ያለው ችግር በሕወሓትና በጊዜያዊ አስተዳደሩ መካከል ሳይኾን በሕወሓት ከፍተኛ አመራሮች መካከል የተፈጠረ ክፍፍል ነው ሲል ትናንት ምሽት አስታውቋል።

የሕወሓት አመራር ክፍፍል በአስተዳደሩ መዋቅር ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩን ያመነው አስተዳደሩ፣ የጊዜያዊ አስተዳደሩን ውሳኔዎች ለመሻር ወይም መዋቅሮቹን ለማዳከም በሚደረጉ ሙከራዎች ላይ ግን ሕጋዊ ርምጃ እወስዳለኹ በማለት አስጠንቅቋል።

ጊዜያዊ አስተዳደሩ፣ የክልሉን ጸጥታ ሃይሎች ስም በሚያጠፉ አካላት ላይ ሕጋዊ ርምጃ እንደሚወስድም ገልጧል። ሕወሓት በበኩሉ፣ በተለያዩ ከተሞች እያካሄዳቸው በሚገኙት ሕዝባዊ ኮንፈረንሶች፣ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ጥገኛና አምባገነን ኾኗል በማለት በመክሰስ ላይ ነው።