ፍሬከናፍር

በጋዜጣዉ ሪፓርተር

September 25, 2024

ይህን ኃይለ ቃል ዓለም አቀፍ የሰላም ቀን በድሬዳዋ ከተማ መስከረም 11 ቀን 2017 ዓ.ም. ሲከበር የተናገሩት የአሜሪካ ኤምባሲ ምክትል ኃላፊ ግዌንዶሊን ግሪን ናቸው፡፡ ኃላፊዋ አያይዘውም ኢትዮጵያ እንድትረጋጋና አንድነትን እንድታገኝ ማኅበረሰቦች መቻቻልን ማክበርና መቀበል፣ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ድምፅም እንዲሰማ ማድረግ አለባቸው ሲሉም ተሰምተዋል፡፡ የዓለም መሪዎች ግጭቶችን እንዲያቆሙና በተባበሩት መንግሥታት ቻርተርና በተዛማጅ ዓለም አቀፍ ሕግ የተደነገገውን የሰላም ባህል እንዲቀበሉና በፅኑ እንዲተገብሩም ጠይቀዋል። ዓለም አቀፉ የሰላም ቀን የተከበረው ‹‹ስለ ሰላም እንነጋገር›› በሚል መሪ ቃል በመወያየት ጭምር ነው፡፡