
ከ 4 ሰአት በፊት
የብሪታንያ ትልቁ ክለብ የቱ ነው የሚለው ጥያቄ ላለፉት ዓመታት እንዳጨቃጨቀ ዘልቋል።
በርካታ ዋንጫዎችን ያነሳው ወይስ ከፍተኛ ገቢ የሚያስገባው ነው?
ብዙ የማኅበራዊ ሚዲያ ተከታታዮች ያሉት ወይስ ትልቅ ስታዲየም ያለው?
በሊጉ ያለው አማካይ ውጤት ነው ትልቅ የሚያስብለው ወይስ ምን?
ጭቅጭቁ አሸናፊ አይኖረውም። ምንም አሳማኝ የሚባል አመክንዮ ቢቀርብም የተለየ ሃሳብ መኖሩ ይቀጥላል።
ይህንን ከግምት በማስገባት ቢቢሲ ስፖርት በጉዳዩ ዙሪያ በዩናይትድ ኪንግደም ያሉ ከ250 በላይ ሠራተኞቹን ሃሳባቸውን እንዲሰጡ አድርጓል።
ብዙ አለመግባባት ነበር። ደስተኛ ያልሆኑ ሰዎችም ነበሩ።
በመጨረሻም ግን ምላሾቹን በማጠናከር ቀዳሚዎቹን አስር ክለቦች መለየት ተችሏል።
በዚህ ደረጃ ይስማማሉ? ላይስማሙ ይችላሉ።
ብዙዎቻችሁ በክለባችሁ ደረጃ ደስተኛ እንደማትሆኑ እርግጥ ነው። አንዳንድ ነገሮችን ከግምት ማስገገባት ግን አስፈላጊ ይሆናል።
ይህ ውጤት አማካይ ተሰልቶ የተወሰደ ነው። ትክክል ነን ብለንም አናምንም።
የቢቢሲ ስፖርት ቀዳሚዎቹ የብሪታንያ ክለቦች የሚከተሉት ናቸው፡-
- ማንቸስተር ዩናይትድ
- ሊቨርፑል
- አርሰናል
- ማንቸስተር ሲቲ
- ሴልቲክ
- ቼእሲ
- ቶተንሃም ሆትስፐር
- ሬንጀርስ
- አስቶን ቪላ
- ኒውካስል ጉዳዩን ሳይንሳዊ ለማድረግ ክለቦቹ ቀዳሚ የሆኑባቸውን አንዳንድ ሁኔታዎች ለመመልከት ተሞክሯል።
የትኛው ክለብ ትላልቅ የሚባሉትን ዋንጫዎች በብዛት አሸነፈ?
በተለምዶ ክለቦች ዋንጫ በተደጋጋሚ ካነሱ ትልቅ ይባላሉ።
ከዋንጫ አንጻር ካየነው ግዙፎቸ የግላስጎው ክለቦች ሴልቲክ እና ሬንጀርስ በቀዳሚነት ይቀመጣሉ።
እንግሊዝ ውስጥ ለብቻው ካየነው ሊቨርፑል ቀዳሚ ሲሆን፣ ማንቸስተር ዩናይትድ በቅርብ ርቀት ይከተላል። ሊቨርፑሎች 20ኛውን የሊግ ዋንጫ ዘንድሮ በማንሳት ክብረወሰኑን ከዩናይትድ ጋር ለመጋራት ከጫፍ ደርሰዋል።
በአውሮፓ መድረክም ብዙ ዋንጫ በማንሳት ከእንግሊዝ ክለቦች ቀዳሚ ናቸው። በርካታ የኤፍኤ ዋንጫዎችን ያነሳው አርሰናል ነው።
ማንቸስተር ሲቲ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ያነሳቸው ዋንጫዎች በደረጃው ላይ ከፍ ብሎ እንዲቀመጥ ረድቶታል።
ቡድኑ ካለፉት ሰባት የውድድር ዓመታት በስድስቱ የሊጉ አሸናፊ ሆነዋል።
የዋንጫ ጉዳይ በራሱ አከራካሪ ነው። የአውሮፓ መድረክ ዋንጫዎች ከአገር ውስጥ ዋንጫዎች ይበልጣሉ ማለት ይቻላል።
የትኛው ክለብ በርካታ የማኅበራዊ ሚዲያ ተከታዮች አሉት?
ቀደምት የሚባሉ ደጋፊዎች የማኅበራዊ ሚዲያ ተከታዮችን ብዛት እንደማወዳደሪያ ማቅረብን ላይስማሙበት ይችላሉ።
ማኅበራዊ ሚዲያ ግን ክለቦች ምን ያህል የዓለም ክፍል እንደሚደርሱ እና ያላቸውን ተቀባይነት ስለሚያሳይ ጥሩ ማነጻጸሪያ ይሆናል።
በዋና ዋና አራት የማኅበራዊ ሚዲያዎች ጠቅላላ ድምር ካየነው ማንቸስተር ዩናይትድ በሰፊ ልዩነት ይመራል። አንዳንድ ክለቦች በተወሰኑ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ቀዳሚ ለመሆን ችለዋል።
ሲቲ ከተቀናቃኙ ዩናይትድ አንጻር በማኅበራዊ ሚዲያ ተከታዮች ቁጥር ቢበለጥም በቲክ ቶክ ግን ይቀድመዋል።
በጠቅላላ ተከታዮች ቁጥር ስድስተኛ ላይ የተቀመጠው ቶተንሃም በቲክቶክ ብቻ ካየነው ሁሉንም ክለቦች ይቀድማል።
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጠንካራ የሚባሉት ስድስት ክለቦች ቀዳሚዎቹን ስፍራዎች ሲይዙ በ2015/16 በአስገራሚ ሁኔታ የሊጉን ዋንጫ ያነሳው ሌስተር ሰባተኛ ደረጃ ይዟል።

- ማንቸስተር ዩናይትድ በ2 ቢሊዮን ፓውንድ አዲስ ስታድየም ሊገነባ ነው11 መጋቢት 2025
- “‘ወንድ ነሽ ተብዬ’ ከሴቶች እግር ኳስ ተገለልኩ” መሳይ ተመስገን1 መጋቢት 2025
- የሰባት ወር ነፍሰጡር ሆና በፓሪስ ኦሊምፒክ በመሳተፍ ዓለምን ያስደመመችው ስፖርተኛ23 የካቲት 2025
ከፍተኛ ገቢ ያስገኘው ክለብ የትኛው ነው?
ከገንዘብ አንጻር ካየነው ማንቸስተር ሲቲ ቀዳሚ ነው።
እንደዴሎይት መኒ ሊግ ጥናት ከሆነ በ2023/24 የውድድር ዓም 708 ሚሊዮን ፓውንድ ገቢ ያገኘው ማንቸስተር ሲቲ ቀዳሚ ነው።
በዓለም አቀፍ ደረጃም በሪያል ማድሪድ ብቻ ነው የሚበለጠው።
ዘጠኝ የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች በዓለም ቀዳሚ ከሆኑ 20 ክለቦች ውስጥ ተካትተዋል።

የትኛው ክለብ ትልቅ ስታዲም አለው?
ለእርስዎ ትልቅ ክለብ ማለት ትልቅ ስታዲየም ያለው ከሆነ ማንቸስተር ዩናይትድ ቀዳሚ ነው።
90 ሺህ ተመልካች የሚይዘው ዌምብሌይ በእንግሊዝ ቀዳሚው ስታዲም ነው።
በክለቦች ደግሞ ዩናይትድ ይመራል። 100 ሺህ ደጋፊ የሚይዝ ስታዲም በሁለት ቢሊዮን ፓውንድ ለመስራትም ከለቡ ማቀዱን ይፋ አድርጓል።
የኤቨርተኑ አዲሱ ብራምሌይ ሙር ዶክ ስታዲየም ሰበታኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ማንቸስተር ሲቲም የተመልካቾችን ቁትር ወደ 61 ሺህ 474 ለማሳደግ የማስፋፊያ ሥራ እያከናወነ ነው።

ባለፉት 10 ዓመታት በፕሪሚየር ሊጉ በአማካይ ጥሩ ደረጃ ይዞ ያጠናቀቀው ቡድን የቱ ነው?
ስለእግር ኳስ ውጤት ካነሳን ወጥ መሆን ቁልፍ ነው።
በዚህ ረገድ ማንቸስተር ሲቲ ባለፉት አስር ዓመታት ተሳክቶለታል። ስድስት ጊዜ ዋንጫውን ከማንሳቱም በላይ በተከታታይ አራት ጊዜ ማሸነፉ ቀዳሚ ያደርገዋል።
ቀጣዩን ቦታ ለመያዝ ሊቨርፑል፣ ማንቸስተር ዩናይትድ፣ አርሰናል፣ ቶተንሃም እና ቸልሲም በተቀራራቢ ነጥብ ይከተላሉ።
ዌስት ሃም፣ ኤቨርተን እና ክሪስታል ደግሞ ላለፉት ዓመታት በሊጉ መካከለኛ ሊግ ላይ በተደጋጋሚ ለመጨረስ ችለዋል።
አንድ ዓመት በሻምፒዮን ሺፑ ያሳለፈው ሌስተርም እስከ 10 ባለው ደረጃ ውስጥ ለማጠናቀቅ በቅቷል። ለዚህ ደግሞ የሊጉን ዋንጫ ያነሱበት ዓመት ትልቅ እገዛ አድርጎላቸዋል።
ሴልቲክ እና ሬንጀርስ በዚህ ዝርዝር ውስጥ ኣልተካተቱት በሊጉ ስለማይሳተፉ ነው። ሴልቲክ ካለፉት 10 የስኮትላንድ የሊግ ውድድር ዓመታት በዘጠኙ አሸናፊ ሆኗል።