July 20, 2017 21:52

የቀድሞው አንድነት ፓርቲ አመራር አባል አቶ ዳንኤል ሺበሺ እና በጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ በ50 ሺህ

ብር ዋስ እንዲፈቱ ፍርድ ቤት ትእዛዝ ሰጠ። የፍርድ ቤቱ ሂደት እስኪጠናቀቅ ከሀገር እንዳይወጡ የተሰጠው ትዕዛዝ ለፍርድ ቤት መድረሱ ሲረጋጥም እንዲፈቱ ትዕዛዝ ተሰቷል።

በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ ሥር ከታሰሩ ስምንተኛ ወራቸውን ያስቆጠሩትና ከሽብርተኛ ድርጅት ጋር ግንኙነት በማድረግ፣ የተለያዩ የሽብርተኛ ድርጅቶችን ሐሳብ የሚገልፁ ጹሑፎችን እንዲሁም ምስሎችን ይዛችሁ ተገኝታችኋል በሚል የወንጀል ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳያቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙት የቀድሞው አንድነት ፓርቲ አመራር አባል አቶ ዳንኤል ሺበሺና ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ በዋስ እንዲፈቱ ትዕዛዝ ተሰጥቷል።የተከሳሾቹ ጠበቃ አቶ ሽብሩ በለጠ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፤ በተከሰሱበት ጉዳይም ዐቃቤ ሕግ አንድ ምስክር በዝግ አሰምቷል። ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ እና አቶ ዳንኤል ሺበሺ፥ እያንዳንዳቸው የ50ሺህ ብር ዋስትና እንዲያቀርቡ ተጠይቀዋል   

ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ እና አቶ ዳንኤል ሺበሺ፥ እያንዳንዳቸው የ50ሺህ ብር ዋስትና እንዲያቀርቡ ተጠይቀዋል

July 17, 2017 17:23

l
ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ እና አቶ ዳንኤል ሺበሺ፥ እያንዳንዳቸው የ50ሺህ ብር ዋስትና እንዲያቀርቡ ተጠይቀዋል

 

July 17, 2017 17:23

ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ እና አቶ ዳንኤል ሺበሺ፥ እያንዳንዳቸው የ50ሺህ ብር ዋስትና እንዲያቀርቡ ተጠይቀዋል።  አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተከትሎ በቁጥጥር ስር የዋሉት እና ክስ የቀረበባቸው ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ እና የቀድሞ የአንድነት ፓርቲ አመራር አቶ ዳንኤል ሺበሺ ዛሬ ሐምሌ 10/2009 ዓ.ም በቦሌ ክፍለ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት ቀርበው ባቀረቡት የይግባኝ አቤቱታ ላይ ብይን አግኝተዋል፡፡ ፍ/ቤቱ እያንዳንዳቸው የ50 ሺህ ብር ዋስትና አቅርበው በዋስ እንዲወጡ ብይን ሰጥቷል፡፡

በሌላ በኩል የቀረበባቸው ክስ በዝግ ችሎት እንዲታይ በተጨማሪነትም የፍርዱ ሂደቱ እስኪያልቅ ከሀገር እንዳይወጡ፣ ማረሚያ ቤቱም የፎቶ መረጃቸውን ለብሔራዊ ደኅንነት እንዲልክ ውሳ ተላልፏል፡፡

ኤልያስም ሆነ ዳንኤል የቀረበባቸው ክስ በዝግ ችሎት ሊታይ አይገባም ብለው አቤቱታ ማቅረባቸው የሚታወስ ነው፡፡ ፍ/ቤቱ ይህን አቤቱታ ሳይቀበለው ቀርቶ ክሳቸው በዝግ እንዲታይ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ በአሁኑ ሰአትም በቦሌ ክፍለከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት መደበኛ ክሳቸው በዝግ እየታየ ይገኛል፡፡

ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩም ሆነ አቶ ዳንኤል ሺበሺ ከሕዳር 08/2009 ዓ.ም ጀምሮ በእስር ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡