ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ) ባለፈው ሰሞን “የአለም አቀፍ ትበብር ለኢትዮጵያዉያን መብት (Global alliance for the right of Ethiopians) የቦርድ አባል ነኝ ብለው በአማርኛ ድምጽ ራዲዮ በ1/25/2018 (ፈረንጅ አቆጣጠር) በሳይንስና ቴክኖሎጂ ክ/ጊዜ የተጋበዙት አቶ ዳኛቸው ተሾመ የተባሉት ‘የሰውን ማንነት’ (እሳቸው በሳይንሳዊ ጥበብ የታገዘ ሰዎችን በድምፅ የመለየት ጥበብ ተመርቄበታለሁ ይላሉ) ድምጽን የመለየት ጥበብ (ሳይንሳዊ ኢንቬንሸን) የተማርኩበትና የፈጠራ ውጤትም አድርጌአለሁ በማለት በዚህ ቴክኖሎጂ በማስተዋወቅ ስራ እንዳሉ ይናገራሉ። ለዚህ መስክ እንዲሰለፉ ምን አነሳሳዎት ተብለው ሲጠየቁ፤ ሕዝባችን እያሰቃዩ ወደ እዚህ ዓለም የሚመጡትን ወንጀለኞች ፎቶግራፍ፤የመሳሰሉት “የመረጃ ማከማቻ” ውስጥ በማስቀመጥ ተፈላጊ ሰው ሲኖር በቀላሉ ማስያዝ እንዲቻል በበኩሌ አስተዋጽኦ ለማድረግ ነው፡ ይላሉ።
ለመሆኑ እንናተ እነማን ናችሁ? ተብለው ሲጠየቁ “የኢትዮጵያዉያንን በደል ለማስቆም” የተቋቋምን፤“የአለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዉያን መብት (Global alliance for the right of Ethiopians) የቦርድ አባል ነኝ” ሲሉ ለጋዜጠኛ ሰለሞን ክፍሌ ጥያቄ መልስ ሰጥተዋል። ግሎባል አላያንስም ይህንን ጥናት እንዳደርግ ታዝዤ ነው፤ በዛ መሰረት ነው ይህን ለማድረግ የገባሁት እና ይህንን ለማስታወስ እፈልጋለሁ” በማለት ተናግረዋል። እኚህ ሰውየ ……የቦርድ አባል ነኝ እያሉን ያሉት ድርጅት የተፈናቀሉት ወገኖችን ለመርዳት ያደረገው በጎ ተግባር እንደሰራ ባውቅም፡ ያንን በጎ ጐኑ እንዳለ ሆኖ፤“የአለም አቀፍ ትበብር ለኢትዮጵያዉያን መብት (Global alliance for the right of Ethiopians የተባለው ድርጅት ሊያደርጋቸው የሚፈልገውን የድርጅቱ ተልዕኮ http://www.defendethiopians.org/about/ የሚለው ድረገጹን ስንጐበኝ የሚነግረን የመጻፍ፤የመናገር፤የመከራከር የተነፈገው የዜጋችን መብት እንዲከበር በጽናት ይሠራል ይላል። ይህንን ሳነብ ትንሽ “ያዝ አደረገኝ”። ሦስት ምክንያቶችን ላቅረብ (በጥቂቱ ማለት ነው)
“የአለም አቀፍ ትበብር ለኢትዮጵያዉያን መብት (Global alliance for the right of Ethiopians (GARE)” የተባለው ድርጅቱን በግምባር ቀደም የሚያንቀሳቅሱት ደግሞ “የግንቦት7 አባሎች እና ከግንቦት 7 በጎ ቅርበት ያላቸው ሰዎች ” እነ ንአምን ዘለቀ፤ታማኝ በየነ፤ ሉሊት፤ እነ ሜሮን…………እንዲሁም እነ አክሎግ ቢራራ፤ እነ አል ማርያም…….ወዘተ የመሳሰሉ ናቸው። ግንቦት 7 የተባለው ድርጅት ደግሞ በሰብአዊ መብት ጥሰት በታጋዮቹ በኩል ብዙ አቤቱታ እና ቅሬታ የደረሰበት ድርጅት መሆኑን ጋዜጠኛ ሰለሞን ክፍሌም ሆነ አቶ ዳኛቸው ተሾመ አያውቁም ተብሎ አይገመትም። ለዚህ ነው አቶ ሰለሞን ክፍሌ ጠለቅ ብሎ ስለ ድርጅቱ ምንነትና እነማን እንደሚመሩት ፤ድርጅቱ በሰብአዊ መብትም ሆነ በመናገር ነፃነት ያላቸው ማሕደር ምን እንደሚመስል አልወጠራቸውም ብየ ይህ የቅሬታ ደብዳቤ እንደጽፍ የተገደድኩት። ይህ ድርጅት ስለ መናገር፤ስለመከራከር፤ስለመጻፍ ነጻነት አምናለሁ ለዚህም የቆምኩኝ ነኝ፤ የሚለን ድርጅት በመሪነት የሚመሩት ሰዎች አነ ታማኝ
በየነ፤ እነ ንአማን ዘለቀ….ናቸው። ንአምን እነ ሉሊት….ወዘተ ተወቃሽ የድርጅት አባሎች ስለሆኑ እዚህ አልጠቅሰውም። ታማኝ ጋር ነው የማተኩረው። ይህ አቶ ዳኛቸው በቦርድ አባልነት አለሁበት የሚሉትንም ጭምር በጥቂት ማስረጃ ልተች።
“የአለም አቀፍ ትበብር ለኢትዮጵያዉያን መብት (Global alliance for the right of Ethiopians የተባለው ድርጅት በ2014 ዓ.ም አንዳርጋቸው ጽጌ የተባለው የግንቦት 7 ምክትል መሪ (ኤርትራ በረሃ የሻዕቢያ እርሻ በማልማት ስራ የተሰማራ ተዋጊ ሃይል ሲመራ የነበረ) በወያኔ ሲታፈን ድርጅቱ የተቃውሞ መግለጫ በማውጣት የአንዳርጋቸው መብት በወያኔ መጣሱ ቅሬታውን በማስሰማት በየመን መንግሥት ላይ የቅሬታ ‘መግለጫ’ አውጥቷል። ማውጣቱ ሓጢያት የለውም; ከዚህ ጋር የተያያዘ ቅርታ ግን እንፈትሻለን። በወቅቱ አንዳርጋቸው ጽጌ ከሰንዓ አየር-ፖርት በወያኔዎች ሲታፈን ያወጠው መግለጫ እንዲህ ይነበበባል፡-
Ethiopian-Americans are outraged by news of the illegal detention on June 23, 2014 of Mr. Andargachew Tsege, Secretary General of Ginbot 7, Movement for Justice, Freedom and Democracy while in transit at Sanaa International Airport in Yemen………….እያለ ለየመን መንግሥት ተባባሪነት ተቃውሞ አሰምቶ ነበር። በአንጻሩ ግን ተመሳሳይ “ማሲቭ ኪድናፒን” በርካታ ሰዎች የሰው ልጆች ጠለፋ (ኢሌጋል ሁማን ትራፊኪንግ) ወንጀል በኤርትራኖችና አንዳርጋቸው ጽጌና መስከረም አታላይ ሲመራው በነበረው የግንቦት 7 ተዋጊ ሃይሎች ሰላማዊ ድሃ የትግሬዎች በጠመንጃ አፈሙዝ ከትግራይ ተጠልፈው ወደ ኤርትራ ለውትድርና ተገድደው ሲጠለፉ “ግሎባል አላያንስ” ውሃ ውስጥ እንደገባች አይጥ’-ድምፃቸው-አልተሰማም። አንደኛ ፤
ግንቦት 7/አርበኞች የተባለው ኤርትራ የመሸገው በብርሃኑ ነጋ የሚመራው ድርጅት ‘የእለት እንጀራቸውን ለመፈለግ’ ሲሉ በራሳቸው አነሳሽነት በመላው አፍሪቃ እና መሰል የድሃ አገሮች ዜጎች እንደሚያደረጉት በባህላዊ ቁፋሮ ወርቅ ፍለጋ ሲደክሙ የነበሩ ድሃ ወጣት ትግሬዎች “ወደ ትግራይ ድምበር ጥሶ በመግባት እነዚህ ወጣቶች አፍኖ በመውሰድ እየደበደበ በግድ እንዲታገሉ ተጠይቀው በትግራይ ሕዝብ እና አክቲቪስቶች ጩኸትና ግፊት ምክንያት የተደናገጠው ወያኔ በግፊቱ ተነሳስቶ (ነገሩን ደብቆ ጀሮ ዳባ ብሎት እንደነበር ይታወሳል) ሻዕቢያን ካልለቀቅካቸው መጥቼ እርምጃ እወስድብሃለሁ ሲል ስላስፈራራው፤ በዚህ ዛቻ የተደናገጠው ሻዕቢያ እና ግንቦት7/አርበኞች ‘እድል’ ያደረጉት ግማሾቹ ከተለቀቁ (ሌሎች እዛው በግድ የተያዙ አሉ ብለው የተለቀቁ ሰዎች ተናግረዋል) በሗላ ብዙ እንግልት እንደደረሰባቸው ለአሜሪካ ድምጽ ትግርኛ ክ/ጊዜም ሆነ በወያኔ መገናኛዎች ተናግረዋል።
የጠለፋው ትዕዛዝ የተከናወነው ደግም ምርኩዝ ተደግፎ አንከስ እያለ በበሽታ የሚሰቃየው የግንቦት/7 አርበኞች ግምባር ከፍተኛ አመራር ነው ሲባልለት የነበረው “መስከረም አታላይ” የተባለው አደገኛ የሻዕቢያ ቅጥረኛ ግንቦት7ም ሆነ ሌሎቹ ተቃዋሚዎችን በቅርብ የሚቆጣጠራቸው የሻዕቢያው ኮለኔል ፍጹም እንደነበሩ
ነግረውናል። ሁለቱ ሹሞች ተጠላፊዎቹን ሲያነጋግሯቸው ምን እንዳላቸው እና እንግልት፤ ስድብ እና የሕሊና ጭንቀት እንደደረሰባቸው በዜናዎች የተሰራጨው ቃለ መጠይቃቸው ሰምተናል። እነዚህም ልክ እንደ አንዳርጋቸው ኢትዮጵያውያን ናቸው። በሻዕቢያም፤ በግንቦት7ም በወያኔም አንድ ሰው መብቱ ተገፍፎ ተደብድቦ ሳይወድ ታፍኖ ወደ ሌላ ድምበር “ በሁማን ትራፊኪንግ/ ሰውን በሕገ ወጥ በማዘዋወር” ዜጎች ላይ ወንጀል ሲፈጸም <<ግሎባል አላያንስ..> ለአንዳርጋቸው ያደረጉለትን ጩኸት ያህል እኩል ለነዚህ ድሆችም ማውገዝ ይጠበቅባቸው ነበር (አሁንም የታፈኑ ሰዎች አሉ)። ሆኖም እነ ታማኝ በየነም ሆነ አቶ ዳኛቸው ተሾመ የሚያካሂዱት ይህ የግሎባል አላያንስ የተባለው ድርጅት በዚህ ጉዳይ የኮነነበት መግለጫ አንድም የለም። ምክንያቱም በጠለፋው ወንጀል የተካፈለው (ተከሳሹ) ግንቦት 7 ስለሆነ።
“የአለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዉያን መብት (Global alliance for the right of Ethiopians የተባለው ድርጅት በርካታ በጎ ድርጊቶች ያደረገ መሆኑን በጎ ጐኑ እንዳለ ሆኖ፦ ድርጅታቸው ስለ ሚናገረው ስለ ዜጎች የመናገር የመጻፍ፤የመከራከር መብት ማክበር ስለሚናገሩት ‘በግብር የማይፈጸመው ባዶ ጩኸታቸው’ ድርጅቱን በግምባር ቀደም አስተባባሪነት የታወቁት እነ ንአምን ዘለቀ እና ታማኝ በየነ ስለ ሰው መብት እና አብሬ መዳሰስ የግድ ነው። እነዚህ ግለሰቦች የሚመሩት“የአለም አቀፍ ትበብር ለኢትዮጵያዉያን መብት (Global alliance for the right of Ethiopians) የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አባሎች ነን እያሉን ያሉት እነ ታማኝ ኢሳት ቴ/ቪዥን ጣቢያን ይመራሉ/የጣቢያው ቦርድ አመራር አባሎችም ናቸው። ግን በዚህ ድርጅት “ተልዕኮ” የሚነግሩን እና ኢሳትን ሲያንቀሳቅሱ የሚከተሉት የመናገር፤የመጻፍ፤የመከራከር መብት ማክብር ማሕደራቸው ….ሲፈተሽ እውን እነሱን ወይንም ግንቦት 7ን የሚከስስ/የሚቃወም/ የመናገር፤የመጻፍ፤የመሞገት ምብቱ በቴ/ቪዥን ጣቢያቸው ያከብራሉ/ይከበራል? የሚለው ጥያቄ ጭሮብኛል።
ሁለተኛ-
በግንቦት 7 ስር ሆነው ሲታገሉ የነበሩ ዜጎቻችን በሻዕቢያና በግንቦት7/አርበኞች ቅንብር ወደ የሻዕቢያ ‘እስርቤት ገራፊዎች’ ተላልፈው የተሰጡ መሆናቸው እና እነሱም በአንዳርጋቸው ጽጌ እውቅና እና ሃለፊነት እንግልት እንደደረሰባቸው ከዚያም አልፎ አብዛኛዎቹ አማራዎች ስለነበሩ ‘ብርሃኑ እና አመራሩ’ በአማራ ያላቸው ጥላቻ በማስረጃ ለማስረዳት ታማኝ በየነ ‘ሌት ተቀን’ በሚለፋለት እና በሚመራው <ኢሳት> በተባለው ቴ/ቪዥን/ራዲዮ ውስጥ ቀርበው (አንዳንዶቹ ኤርትራ ተዋጊ ውስጥ በልዩ ልዩ ዘርፎች በአመራር ደረጃ የነበሩ ናቸው) እንዲናገሩ እንዲፈቀድላቸው ደብዳቤ ለኢሳት ቢጽፉም፦ የጓዳቸው ብርሃኑ ነጋ እና የጓዳቸው አንዳርጋቸው ጽጌ ገበና እንዳይጋለጥ ሊጋብዙዋቸው አልተፈቀደም።
እነኚህ ልጆች ሲሉት የነበረው ቀላል ጥያቄ ነበር። ሁለታችንን ወገኖች በመጋበዝ አቅርባችሁ ሕዝብ እንዲፈርደን ኢሳት ውስጥ ጋብዙን እያሉ ደብዳቤም ሆነ በቃል “ኢሳትን” ቢወተውትዋቸውም “ሁላችንም ያንጫጫ አስገራሚ የሆነ “ጀሮ ዳባ” የተላበሰ መልስ ነበር። ይባስ ተብሎ እነዚህ በግንቦት’7 አመራሮች ላይ እሮሮ ሲያስሰሙ የነበሩ የግንቦት 7 ታጋዮች ‘ወያኔዎች’ ናቸው እያሉ በማጥላላት በአድማጭ ፊት ስለ ግንቦት 7
ውክልና ቆመው ለበርካታ ቀናት እና ረዢም ሰዓት የሸፈነ “ወገናዊነት” እንዳሳዩ ይታወቃል (የሚገርመው ግን እነ ስብሓት እና በርካታ ወያኔዎችን እየጋበዙ ኢሳት ውስጥ ሲያነጋግሯቸው እነዚህ ምስኪኖች ግን ‘ወያኔዎች’ ናቸው ሲሉ እነ ብርሃኑ እና አንዳርጋቸውን እንዳያጋልጡ ፈርተው አድልዎት ሰሩባቸው)። ኢሳትን የጠየቁት ቃል ጥያቄ ነበር፦ ጋብዙን እና እናንተንም ሆነ (ኢሳት ጋዜጠኞች እነ መሳይ እና ሲሳይ አገና..) አንዳርጋቸው ወይንም ብርሃኑን እንከራከራችሁ ብለው ለኢሳት ጋዜጠኞች ለነሲሳይ አገና ለነፋሲል ቢጠይቁም አስገራሚ አድሎአዊ ጋዜጠኛነት ብቻ ሳይሆን ያሳዩት፤ የነዚህ ተበድለናል ሰብአዊ መብታችን ተጥሷል፤ተደብድበናል፤ታስረናል፤የጠፉ የተረሸኑ አሉ፤…… ብለው የመናገር መብት ፍቀዱልንና ‘እውነቱን ሕዝቡ ይፍረድ’ ቢሉም የመናገር መብታቸው እንዲታፈን ተደርጓል። ይህ ሲፈጸም ደግሞ “ለዜጎች የመነጋር መብት እና ዜጎች ግፍ ሲደርስባቸው እነ ታማኝ የሚመሩት <<የትም ይሁን የትም ዜጎች ሲታፈኑ፤ ለዓለምም ይሁን ለሕዝባችን ጀሮ እንዲደርስ በማድረግ ግፈኞችን ለማጋለጥ የተደራጀን ነን የሚሉን የዚህ የግሎባል አላያንስ መሪዎች” እነ ታማኝ በየነ በተጨማሪ በዚህ ድርጅት ብቻ ሳይሆን ኢሳት ውስጥም ከፍተኛ አመራር ሆነው የሚሰሩ ሰዎች ናቸው ይህ አፋና ሲፈጸም ‘ጀሮ ዳባን’ የመረጡ። በዚህ የነተነሳ እኔም ሆንኩኝ በአውሮፓ ‘ብራስል’ ውስጥ የሚኖሮው የሰብአዊ መብት ተሟጋች የሆነው ያሬድ ሃይለማርያም ስለ ጉዳዩ አስመልክቶ እነ ታማኝ በየነ የሚመሩት ኢሳት እና የመገናኛ ብዙሃን የሚባሉትን እንዲህ ሲል ቅሬታውን በማስተጋባት ኮንኖአቸው ነበር-
የግንቦት 7 የግፍ ተግባር እና የመገናኛ ብዙሃን ዝምታ – ያሬድ ኃይለማርያም “በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ፤ የወያኔ ሳያንስ የነፃ አውጪዎቻችን (የግንቦት 7) የግፍ ተግባር እና የመገናኛ ብዙሃን ዝምታ ያሬድ ኃይለማርያም ከብራስልስ ጥር 29 ቀን 2006 ዓ.ም.
በማለት የግንቦት 7 አመራሮች በታጋዮቻቸው ላይ ፈጽመዋል የተባሉት ግፍች በኢሳትም ሆነ በመሳሰሉት ተቋማት እንዳይናገሩ መታገዳቸው አውግዞአቸዋል። የመናገር፤የመጻፍ ፤ የመከራከር መብት የተነፈጉት ወገኖቻችን መብት ለማስከበር ተልእኮ አለን የሚሉን ይህ የግንቦተት 7 አባላት በብዛት የተሰገሰጉበት “ግሎባል አላያንስ…..” በተባለው ድርጅት በግንቦት 7 ታጋዮች ላይ ምን እንደደረሰ እሮሮአቸው ለተዘጋባቸው ታጋዮች ሁኔታ ‘ከትውስታችን ያልረሳነው’ ጸሐፊዎች እንዳለን መታወቅ አለበት። እነ ጋዜጠኛ ሰለሞን ክፍሌ ግን በዳበስ-ዳበስ ‘ድርጅቱን” አቆነጃጅቶ ለማለፍ ከሆነ፤ ትርጉሙ የሳተ ነው። ስለሆነም ቪ ኦ ኤ ለወደፊቱ የተሻለ ስራ እንደሚሰራ ተስፋ አለን።
ሦስተኛ
በትግራይ ሕዝብ ላይ (ባንድ ዘር) ያነጣጠረ፤ካንድ ድርጅት የተላከለት የቅስቀሳ መግለጫ በኢሳት ሲተላላፍ፤ለዚህም ይቅርታ እንዲጠየቅ ታማኝ እና መሰል ጓዶቹ የሚመሩት ይህ የዜና ማሰራጫ በደብዳቤም በትችትም ቢጠየቁ “አሻፈረን” ብለው ይኼው ዛሬም በዩ-ቱብ ላይ ተሰራጭቶ ምን ዓይነት ጉዳት እያስከተለ መሆኑን ጥናት የሚያስፈልገው ይሆናል። እነዚህ ወንድሞች የሰብአዊ መብት ለማስከበር የተነሳን ነን እያሉ በዚህ “ግሎባላ አላያነስ” ቅብጥርጥሮሽ ቢመጻደቁም እውነታው ግን ወገንተኛነት ያጠቃቸው ግለሰቦች የሚመሩት
ድርጅት ስለሆነ ቪ ኦ ኤ ይህንን የቤት ስራውን ሳይሰራ የሳይንስ ክፍለ ጊዜ መሸፈኛ አድርጎ ዳበስበስ ማድረጉ ቅሬታ አድሮብኛል።

አመሰግናለሁ። ጌታቸው ረዳ (ኢትዮፕያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ)

 

getachre@aol.com