በመጀመሪያ ከልብ የሆነ ጥያቄዎቼን እያነሳሁ መሆኑ ይታወቅልኝ፡፡ በአገርና ሕዝብ ጉዳይ ምንም አይነት መለሳለስ አያስፈልግም፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ያለምንም አጋዥ በራሱ ታግሎ አሁን ላይ ነጻነቱን እየተቀዳጀ ነው፡፡ ወያኔና አጋሮቹ ለ27 ዓመት የወንበዴ መዋቅር በአገራችን አዋቅሮ ሕዝብን ከሕዝብ እያጋጨ አገርን ሲያፈርሱ ለኢትዮጵያና ሕዝቦቿ አንድም የደረሰላቸው የለም፡፡ ይልቁንም አጋጣሚውን ለመነገጃነት እያዋሉ በኢትዮጵያውያን ደምና እምባ በኢትዮጵያ ውድቀት ላይ ኑሮአቸውን እያደለቡ መኖሪያ ያደረጉ አያሌ ቡድኖች ተነስተው ታዘብን እንጂ፡፡ በግልጽ ከምናውቃቸው የወንበዴው አጋሮች ባልተናነሰ በሕቡዕ ወንበዴው ወያኔን በመተባበር ብዙ ሴራ የሚያሴሩብንና ለወያኔ ጉልበት የሆኑ በርካቶች ናቸው፡፡ ዛሬ ላይ ከትላልቅ ሚዲያዎች እስከ የፌስቡክ አክቲቪስት ነን ባዮች ብዙዎች የወያኔ የክት ሥራ አስፈጻሚዎች እንደሆኑ እንታዘባለን፡፡ ብዙው ሕዝብ ይህን አይረዳም፡፡
ዛሬ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿ ነጻነታቸውን እየመለሱ በአለበት በአሁኑ ወቅት ብዙዎች የክት የወያኔ ሥራ አስፈጻሚዎችና በኢትዮጵያና ሕዝቦቿ መከራ ላይ ኑሮአቸውን የገነቡ የወያኔ መፍረስ አስደንግጧቸዋል፡፡ የሚይዙት የሚጨብጡትንም አሳጥቷቸዋል፡፡ ለኢትዮጵያውያን ያስተውሉ ዘንድና እነዚህ ጥያቄዎችን በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ከወያኔ እጅ እንዳትወጣ እየተሯሯጡ ላሉ ሁሉ ሊጠይቅ ይገባዋል
- ግንቦት 7 ኢሳትና ሌሎች ሚዲያዎች አላማቸው ምንድነው? ግንቦት 7 ለበርካታ አመታት የዋሸው አንሶ ዛሬም እንዲዋሽ እድል ሊሰጠው ይገባል ወይ? በሻቢያ በኩል የሚሄድ ሁሉ የወያኔ አጋር እንደሆነ ግልጽ ነው ግንቦት 7 እዚህ ላይ ምን መልስ አለው? አንዳርጋቸው ጽጌ የተያዘበት ቀመርና ድራማስ ምን ነበር? ከዛ በኋላ እነ ብርሀኑ እንደልባቸው ኤርትራ ሲመላለሱ ነበር፡፡ እንዴት? የታጠቀው ደምህት የወያኔ ደጀን ወይስ የነጻነት ታጋይ?
- ኢሳት ውዥንብር ፈጣሪ መረጃዎችን በመልቀቅ ወያኔን በሕቡዕ እያገለገለ አደልም ወይ? የኢሳቱ ባልደረባ የቀድሞው የወያኔ ባለስልጣን ኤርምያስ ለገሰ በተምታታ መረጃ ው ዲያስፖራን ውዥንብር ውስጥ እንዲከትና ለአገርና ሕዝቡ በትኩረት እንዳይወግን ለማድረግ ሆን ተብሎ ከወያኔ የተላከ ሰላይ አደልም ወይ? ከዚህ በፊት ብዙ ጉዳዮችን አንስቻለሁ አሁን አልደግመውም፡፡ ግን እንዚህ ጥያቄዎች ኢሳት መመለስ ይችላል ወይ? ኢሳት ውስጥ ጥሩ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ ግን ኢሳት በዋናነት እየተመራ ያለው በማን ነው?
- በአሁኑ ወቅት ዶላር ወደኢትዮጵያ እንዳይሄድ በሚል የሚጮሁት እነማን ናቸው?በወያኔ ዘመን ይህን ሳያደርጉ በአሁኑ ወቅትስ እዚህ ላይ እንዴት ትልቅ ትኩረት ሰጡ? ከሰጡት አማራጭ ደግሞ ዶላሩን እዚህ ለእኛ ስጡን እኛ አገርቤት ከአለው ገንዘባችን ለዘመዶቻችሁ እንሰጣለን የሚል ነው፡፡ ዲያስፖራ ይህ ቁማር የገባው አልመሰለኝም፡፡ አገር ቤት ውጭ ያለ በሚልከው ግንዘብ መጠን ለሌሎች እየሰጡ እዚህ ዶላር የሚያስቀሩ እነማን ናቸው ለመሆኑ?
- ለሁሉም፡- ለመሆኑ ኢትዮጵያ ሰላም ብትሆን በውጭ ስንቶቻቸው ንግዳቸው እንደሚቆም ታዝባችኋል፡፡ ለምሳሌ የተቃዋሚ ነን የሚሉ ሚዲያዎች ምን ተስፋ አላቸው? እነ ግንቦት 7ስ? የዩቱብና ፌስቡክ አክቲቪስት ነን ባዮችስ?
ልብ ያለው ልብ ይበል!
ልዑል እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይታደግ! አሜን!
ሰርፀ ደስታ