የፍኖተ ዴሞክራሲ ራድዮ ፍካሬ ዜና: ወያኔ የእርስ በእርስ ግጭቶችን በመቆስቆስ ግጭቶችን እያራገበ መሆኑ ተጋለጠ * የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ቁጥር እየተመናመነ መሆኑ ተነገረ

November 20, 2017 የመቱ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የፍኖተ ዴሞክራሲ ራድዮ ፍካሬ ዜና ህዳር 10 ቀን 2010 ዓ.ም #ወያኔ የእርስ በእርስ ግጭቶችን በመቆስቆስ ግጭቶችን እያራገበ መሆኑ ተጋለጠ ▪ በሐረር የተከሰተው ግጭትን ተከትሎ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ወያኔ-ህወሀት ሆን ብሎ ውስጥ ውስጡን ባሰለጠናቸው ካድሬዎች ግጭት እያቀጣጠለ ሲሆን በሕዝቡ አርቆ አስተዋይነት እየከሸፉ መሆናቸው እየታየ ነው፡፡ በዚህ ባሳለፍነው ሳምንት በዝዋይ ኦሮሞዎችንና […]
ኢትዮጵያ በየካቲት 1966 ዓም እና በመስከረም 2010 ዓም መካከል ያለፈው ስህተት እንዳይደገም፤ ምን መደረግ አለበት ?

ከአያሌ ዘመናት የግፍ አገዛዝ በኋላ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለመጀመሪያ ጊዜ ገዥዎቹን፤ ያለ ማንም ርዳታ በገዛ እጁ ከሥልጣን ያወረደበት ዘመን 1966 ዓም ነው ። ይኽንን ድል የተቀዳጀው ከአፅናፍ እስከ አፅናፍ ሁሉም ዜጋ ተባብሮ በአንድ ላይ በመቆሙ ነበር ። ይኽ የጋራ ሀገራዊ ድል የተገኘው፤በጎሣ፤ በቋንቋ ፤ በሃይማኖትና በርዕዮት ሳይከፋፈል፤በአንድ ልሳን በመጮኽ፤ በአንድ ልብ በማመንና፤ አንድ ራዕይ በማየት መሆኑ […]
አቶ ማሙሸት አማረ ዐቃቤ ሕግ ባቀረበባቸው የሰነድ ማስረጃ ላይ ያቀረቡት ትችት

By ሳተናው November 20, 2017 06:56 “በደህንነት ሪፖርቱ ተዘጋጀ የተባለው፣ ተከሳሽ ሲጠቀምባቸው ነበሩ የተባሉ ሰባት የሚደርሱ ተንቀሳቃሽ ስልክ ቁጥሮች ተጠልፈዋል በሚል ነው፤ ነገር ግን እነዚህ በማስረጃነት ቀረቡ የተባሉት ስልክ ቁጥሮች በእርግጥም በተከሳሽ ስም ስለመመዝገባቸው ከኢትዩ-ቴሌኮም ጋር የተደረገ የደንበኝነት ውል ማስረጃ አልቀረበም፣ የማን እንደሆኑም አይታወቅም፣ ይበልጡኑ ደግሞ፣ የደህንነቱ ሪፖርቱ ከምክንያታዊ ጥርጣሬ የጸዳ ሆኖ ትክክለኛ ፍትህ መስጠት […]
የኦሮማራ ጥምረት የህወሃትን አፓርታይድ ለማስወገድ ነው! ( ስዩም ተሾመ )

November 20, 2017 07:28 ከህወሃት ባለስልጣናት እንደ አቦይ ስብሃት የሚገርመኝ ሰው የለም፡፡ ሰውዬው ፊት-ለፊት ስለሚናገሩ ግልፅነታቸው ይመቸኛል፡፡ ነገር ግን፣ በግልፅነታቸው ውስጥ ቅጥ-ያጣው የህወሃት ግብዝነት ስለሚንፀባረቅ ንግግራቸው ያበሳጨኛል፡፡ ለምሳሌ ትላንት በጎንደር በተካሄደው ስብሰባ ላይ “…ከኦሮሞ ጋር ለምን ግንኙነት መሰረታችሁ? አላማው ምን ነበር? ምንስ ታስቦ ነው? አሁንም ብታስረዱን…” ማለታቸው ተሰምቷል፡፡ ይህን ማለታቸው የእሮማራ ጥምረት ለህዋህቶች ምን ያህል […]
የጉናው ሰው!! አንዱዓለም አራጌ ማነው?

By ሳተናው November 20, 2017 08:10 የትውልድ አካባቢና የልጅነት ጊዜ አቶ አንዱዓለም አራጌ በጎንደር ክ/ሀገር በደብረታቦር አውራጃ በፋርጣ ወረዳ ጉና ተራራ ሥር ወይንም ግርጌ ክምር ድንጋይ ከተባለ ቦታ በ65 ዓ.ም ጥቅምት 25 ቀን ተወለደ፡፡ የኢትዮጵያ አብዮት ሊፈነዳ ሁለት ዓመት ሲቀረው በምጥ ዋዜማ ማለት ነው፡፡ “ሰው አካባቢውን ይመስላል” እንደሚባለው አንዱዓለም አራጌ በክ/ሀገሩ ከራስ ዳሽን ተራራ ቀጥሎ በሁለተኛ […]
የምመኘው በአንድነታችን ተዋደንና ተከባብረን በኢትዮጵያዊነታችን እንድንኖር ነው-BBC

20 ኖቬምበር 2017 አጭር የምስል መግለጫዶር ፍቃዱ ከበደ በሥራ ገባታ ላይ ስሜ ፍቃዱ ከበደ ይባላል አሁን ወዳለሁባት ከተማ ከመምጣቴ በፊት ለ14 ዓመታት ያህል ተሰድጄ በመጣሁባት በፊንላንዷ ሄልሲንኪ ከተማ እኖር ነበር። በዩክሬን ክሪም በተሰኘው የሕክምና ተቋም የሕክምና ሳይንስ ብማርም የትምህርት ማስረጃዬ በፊንላንድ ሕጋዊ እንዲሆን ያደረኩትም ከብዙ ልፋትና ድካም በኋላ ነበር። ከዚያም ለልጆቻችን የተሻለ የትምህርትም ሆነ ማሕበራዊ […]
በጀርባቸው የሚተኙ ነፍሰጡሮች ልጃቸው ሞቶ የመወለድን ዕድል በእጥፍ ይጨምራሉ -BBC

ሴቶች በመጨረሻ እርግዝናቸው ሶስት ወራት ፅንሱ ሞቶ እንዳይወለድ በጎን በኩል መተኛት እንዳለባቸው አዳዲስ ጥናቶች እያሳዩ ነው። በአንድ ሺ እርጉዞች በመጨረሻ እርግዝናቸው ወቅት በተደረገ ጥናት በጀርባቸው መተኛታቸው ፅንሱ ሞቶ የመወለዱን አደጋ እጥፍ እንደሆነ ያሳያሉ። ይህ ጥናትም 291 ሞተው የተወለዱ ፅንሶችንና 735 በህይወት የተወለዱ ፅንሶች ላይ ምርምር አድርጓል። ተመራማሪዎቹ የእርጉዝ ሴቶች አተኛኝ ለፅንሳቸው ደህንነት በጣም ጠቃሚ እንደሆነና […]
ኢትዮጵያና ኤርትራን ለማደራደር የተነሳው የምሥራቅ አፍሪካ ማኅበር ፕሬዚዳንት ኤርትራ እንዳይገቡ ታገዱ

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ብርሃነ ኢየሱስ ሱራፌል ኢትዮጵያና ኤርትራን ለማደራደር የተነሳው የምሥራቅ አፍሪካ ማኅበር ፕሬዚዳንት ኤርትራ እንዳይገቡ ታገዱ 19 November 2017 ዘመኑ ተናኘ ኢትዮጵያና ኤርትራን ለማደራደር የተነሳው የምሥራቅ አፍሪካ የካቶሊክ ጳጳሳት ጉባዔዎች ማኅበር (አሜሰያ) /Association of Member Episcopal Conferences in Eastern Africa (AMECEA)/፣ ፕሬዚዳንትና የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ ሱራፌል ኤርትራ […]
አቶ ግርማ ሰይፉ፤ በወቅታዊ ፖለቲካ ዙሪያ-አዲስ አድማስ

Sunday, 19 November 2017 00:00 Written by አለማየሁ አንበሴ • እዚህ መ ተንፈስ ካልተቻለ፣ ነፃ ሀገር መምረጥና እዚያ መ ተንፈሱ ሰብአዊ ነው • የፓርቲዎች ዓላማ መሆን ያለበት፣ ተተኪ መሪዎችን ማፍራት ነው • የሀገራችን ጉዳይ ያገባናል የምንል ሰዎች ተሰባስበን ልንወያይ ይገባል • አሁንም የተሻለ የፌደራል ስርዓት መገንባት የሚቻልበት ዕድል አለ በቅርቡ “የተከበሩት!” የተሰኘ በተወካዮች ም/ቤት (ፓርላማ) […]
በውጥረት የሰነበተው የመቱ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት መልቀቂያ ጠየቁ – አዲስ አድማስ

Sunday, 19 November 2017 00:00 Written by አለማየሁ አንበሴ በዩኒቨርሲቲው በተፈጠረ ውጥረት ተማሪዎች ከግቢው እየወጡ ነው ከትግራይ ክልል የመጡ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው መውጣታቸውን ተከትሎ ለሣምንታት በውጥረት የሰነበተው የመቱ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት፣ የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤ ያስገቡ ሲሆን ተማሪዎች ግቢውን ለቀው እየወጡ ነው ተብሏል፡፡ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በበኩሉ፤ ተማሪዎች ተረጋግተው ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ጥረት እያደረገ መሆኑን አስታውቋል፡፡ ከሦስት ሣምንት […]