ውሾቹ ይጮሃሉ፤ ግመሎቹ ግን መንገድ ቀጥለዋል

Saturday, 20 March 2021 11:56 ከእለታት አንድ ቀን በርካታ ጅቦች  የተራቡና  የሚበላ ነገር ለማግኘት ዞር ዞር ሲሉ፣  አንድ እጅግ ግዙፍ ዝሆን ገደል ወድቆ ገብቶ አገኙ። እርቧቸዋልና አንደኛው፡– “እጅግ እድለኞች ነን። ልክ በሰዓቱ የተገኘ መና ነው። ከሰማይ የተላከልን ጸጋ ነው።” ሁለተኛውን፡– “ዘለን እንግባና ዝሆኑን እንቀራመተው” አለ። ሶስተኛው፡– መግባቱንስ  ገባን መብላቱንስ በላን፤ ከጠገብንና ሆዳችን ከሞላ በኋላ እንዴት […]

6ኛው አገራዊ ምርጫ 2013 “ከምርጫው ብንወጣም በሰላማዊ ትግል እንቀጥላለን”

13 March 2021 13:19 አለማየሁ አንበሴ ከሁሉም በፊት ብሔራዊ መግባባት መፍጠር ይገባናል በምርጫው ባለመሳተፋችን መቼም ቢሆን አይቆጨንም ከተመሰረተ ከ25 ዓመታት በላይ ያስቆጠረው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ (ኦፌኮ)፤ ከዘንድሮው አገራዊ ምርጫ ራሱን ማግለሉን ባለፈው ሳምንት ይፋ አድርጓል፡፡ ከምርጫው ለመውጣት ያስገደደውም የጽ/ቤቶቹ መዘጋትና የአመራር አባላቱ ለአስር መዳረግ መሆኑን ይገልፃል፡፡ መንግስት በቅድሚያ  ለብሔራዊ መግባባትና ምክክር ጊዜ ቢሰጥ ኖሮ፣ አሁን […]

በየመን ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በጅምላ ያቃጠሉት የሁቲ አማፅያን መሆናቸው ተነገረ

13 March 2021 11:46   “በቃጠሎው ከ180 በላይ ኢትዮጵያውያን ሞተዋል”            ባለፈው እሁድ በየመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን በጅምላ በእሳት አቃጥለው የገደሉት የሁቲ አማፂያን ናቸው ሲሉ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችና  የየመን የመንግስት ቃል አቀባይ ተናገሩ፡፡ በኢራን የሚደገፈው የሁቲ አማፂያን፣ ኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች ወዳሉበት ቦታ በመግባት፣ ውጊያውን እንዲቀላቀሉ እንደጠየቋቸውና  ፍቃደኛ አለመሆናቸውን ተከትሎም፣ አማፂያኑ በእሳት አቃጥለው እንደገደሏቸው የየመን  መንግስት ቃል […]

ጠ/ሚኒስትሩ ህወኃት ለአፍሪካ አደገኛ ድርጅት እንደነበር ገለፁ

13 March 2021 11:52 አለማየሁ አንበሴ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ በትግራይ ስላለው ሁኔታ ለአፍሪካ ህብረት የሰላምና ደህንነት ም/ቤት በላኩት የፅሁፍ መልዕክት ህወኃት ኢትዮጵያውያንን በዘርና በሃይማኖት ከፋፍሎ  ሲያባላ የኖረና ለአፍሪካም  አደገኛ የነበረ ድርጅት እንደሆነ ገለፀ፡፡ ጠቅላይ ሚንስትሩ ከለውጡ አስፈላጊነት ጀምሮ  በለውጡ ውስጥ ስለታቀዱ የፖለቲካ ማሻሻያዎች በሰፊው በዘረዘሩበት  ህውኃት ከኢትዮጵያም አልፎ ለምስራቅ አፍሪካም ብሎም ለአፍሪካ  ጠቃሚ […]

በምዕራብ ወለጋ የሚፈጸም ዘር ተኮር ጥቃት እንዲቆም ፓርቲዎች ጠየቁ

Saturday, 13 March 2021 11:55 አለማየሁ አንበሴ “የዘር ማጥፋት ወንጀሉ የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ አመራሮች የአደባባይ ፍረጃ ውጤት ነው”             በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ በተደጋጋሚ እያጋጠመ ያለው ዘር ተኮር የንጹሃን ሞትና ሰቆቃ እንዲያበቃ፣ መንግስት ሃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት ፓርቲዎች አሳሰቡ። በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ሻንቡ ጃርቴ ወረዳ ዴቢስ በተባለ ቀበሌ እንዲሁም በደቡብ ክልል አማሮ ልዩ ወረዳ በፅንፈኛ ብሔርተኞች፣ […]