ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: ማንነት እና የወጣቶች ምልከታ
October 19, 2024 – DW Amharic ማንነት: በዚህ ጉዳይ ላይ የየራሳቸውን ምልከታ የገለፁልን ተማሪ ሩሃማ ታዲዮስ እና ተማሪ ናሮቤ ስዩም ናቸው። ተማሪ ሩሃማ ማንነት በህይወታችን ውስጥ የተለየ ቦታ ልንሰጠው ይገባል ትላለች ፡፡ ተማሪ ናሮቤ በአንጻሩ ማንነት አሥፈላጊ ቢሆንም ብዙም ቅድሚያ ወይንም ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ ሊሆን አይገባም» ስትል ሞግታለች።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ
“ዩክሬንን መርዳታችንን አናቆምም” ፕሬዚደንት ባይደን
October 19, 2024 – VOA Amharic በተቃረበው ምርጫ ዋዜማ በጀርመን የመሰናበቻ ጉብኝት የጀመሩት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት አባል ሀገሮች ከሩሲያ ጋር ጦርነት ላይ ያለችውን ዩክሬይንን መርዳታቸውን መቀጠል እንዳለባቸው አሳሰቡ። ዩክሬይን ውጊያው ውስጥ ከገባች ሦስተኛ የክረምት ወቅት ልትይያዝ እየተቃረበች ከመሆኑም ሌላ በምስራቅ ግዛቷ ሽንፈት እያስተናገደች መሆኑ ተጠቁሟል። በዩና… … ሙሉውን ለማየት ወይም […]
በዓለም ዙሪያ ከአንድ ቢሊዮን የሚበልጥ ሕዝብ በከባድ ድሕነት ውስጥ እንደሚኖር ተመለከተ
October 19, 2024 – VOA Amharic የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም እና የብሪታኒያው ኦክስፈርድ ዩኒቨርስቲ ያወጡት ሪፖርት ሲሆን ከመካከላቸው ከግማሽ የሚበልጡት ሕጻናት መሆናቸውን አስታውቋል። አርባ ከመቶ የሚሆኑት የሚኖሩት በጦርነት በሚታመሱ እና በአስተዳደር እና በምጣኔ ሀብት ደካማ በሆኑ ሀገሮች መሆኑን ሪፖርቱ ጠቁሟል። የመንግሥታቱ ድርጅት ተቋም እና የኦክስፈርድ ዩኒቨርስቲው የድህነት እና የሰብዓዊ ዕድገት… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ
በአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ልደታ ቅርንጫፍ የተከሰተ እውነተኛ ክስተት።
October 19, 2024 – Konjit Sitotaw በአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ልደታ ቅርንጫፍ የተከሰተ እውነተኛ ክስተት። አለምነሽ የመኪና ቦሎ ለማደስ ወደ ልደታ ቅርንጫፍ ትራንስፖርት ቢሮ በማለዳ ተገኘች። አስፈላጊዎቹን ሰነዶች በሙሉ ይዛ እና ትክክለኛውን ክፍያ ከፍላ ቁጥር ወስዳ ለመጠበቅ ተቀመጠች። ሰዓታት አለፉ። ከእርሷ በኋላ የመጡ ሰዎች እንዴት እንደሆነ ሳይታወቅ ከእርሷ በፊት ወደ ቆጣሪው ተጠሩ። በመጨረሻም ቁጥሯ ተጠራ። ተስፋ በማድረግ […]
በኢንተርኔትን ነፃነት ኢትዮጵያ ከአፍሪካ የመጨረሻ ደረጃ ላይ ትገኛለች
October 19, 2024 – VOA Amharic በዲጂታል፣ ወይም በአጠቃላይ በኢንተርኔት አጠቃቀም ላይ ያለው ነፃነት ለተከታታይ 14 ዓመታት ማሽቆልቆሉን ‘ፍሪደም ሃውስ’ የተሰኘው ተቋም ባወጣው ዓመታዊ ሪፖርት ላይ አመልክቷል። በጥናቱ ከተካተቱ ሃገራት ውስጥ 41 በሚሆኑት በያዝነው ዓመት ምርጫ የሚካሄድ በመሆኑ ሁኔታውን አሳሳቢ እንደሚያደርገውና፣ ነጻና ክፍት የሆነ የኢንተርኔት አገልግሎት ዲሞክራሲ እውን እንዲሆን ወሳኝ መሆኑን የዘርፉ … … ሙሉውን ለማየት ወይም […]
ከሐማሱ መሪ ግድያ በኋላ የእስራኤል ጦር በጋዛ ባደረሰው ጥቃት 21 ሴቶች መገደላቸው ተገለጸ
ከ 4 ሰአት በፊት የሐማሱ መሪ ግድያን ተከትሎ እስራኤል በሰሜናዊ የጋዛ ሰርጥ በሚገኝ የስደተኞች መጠለያ ላይ ባደረሰችው የአየር ጥቃት 21 ሴቶችን ጨምሮ ቢያንስ 33 ሰዎች መገደላቸውን የሐማስ ባለስልጣናት ገለፁ። እስራኤል ጦሯ በከበበው ጃባሊያ ስላደረሰው ጥቃት ያለችው ነገር የለም። የሐማስ መሪ ያህያ ሲንዋር በዚህ ሳምንት መገደሉን ተከትሎ ጦርነቱ ሊያበቃ ይችላል የሚል ተስፋ የጫረ ቢሆንም፣ የቡድኑ ምክትል […]
በኦሮሚያ ‘የሽማግሌዎችን ትዕዛዝ አላከበረችም’ የተባለች እናት በተፈጸመባት ግርፋት ተጎድታ ሆስፒታል ገባች
ከ 1 ሰአት በፊት በምስራቅ ቦረና ዞን ዋጪሌ ወረዳ ‘የሽማግሌዎችን ትዕዛዝ አላከበረችም’ በሚል ከዛፍ ጋር ታስራ በባለቤቷ የተደበደበችው እናት በአስጊ ጤና ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ የቤተሰብ አባሏ ተናገሩ። በአሁኑ ወቅት በሐዋሳ ሆስፒታል በህክምና ላይ የምትገኘው ኩሹ ቦናያ የተባለችው እናት በደረሰባት ግርፋት ክፉኛ ተጎድታ “የአካሏ ግራ ክፍል አይሰራም። የራስ ቅሏ ተሰብሯል” በማለት የቤተሰብ አባሏ ለቢቢሲ ገልጸዋል። የአካባቢው […]
በኩባ በተፈጠረ የኤሌትሪክ መቋረጥ 10 ሚሊዮን ዜጎች ጨለማ ውስጥ መሆናቸው ተገለጸ
ከ 3 ሰአት በፊት በኩባ በመላ አገሪቱ ኤሌትሪክ ተቋርጦ 10 ሚሊዮን ሰዎች በጨለማ ውስጥ መሆናቸው ተገለፀ። በአገሪቱ የኤሌትሪክ መቋረጥ የተፈጠረው የአገሪቱ ዋነኛ ኃይል ማከፋፈያ በመበላሸቱ እንደሆነ ተገልጿል። አርብ ዕለት ከምሽቱ አምስት ሰዓት ጀምሮ የአገሪቱ ኃይል መቆጣጠርያ መበላሸቱን የኃይል ሚኒስትር በማህበራዊ ድረገጹ ላይ አስታውቋል። የኃይል መቆጣጠርያው ኃላፊዎች በበኩላቸው ብልሽቱን ጠግኖ ዳግም ስራ ለማስጀመር ምን ያህል ጊዜ […]
ሰሜን ኮሪያ ከሩሲያ ጋር ወግና ለመዋጋት ወታደሮቿን መላኳ ተነገረ
ከ 4 ሰአት በፊት ሰሜን ኮሪያ በዩክሬን ከሩሲያ ጋር ወግና ለመፋለም ወታደሮቿን መላክ መጀመሯን የደቡብ ኮሪያ የስለላ ድርጅት አስታወቀ። ይህንን የሰሜን ኮሪያ እርምጃ “ከፍተኛ የደህንነት ስጋት” ስትል ደቡብ ኮሪያ ፈርጃዋለች። ይህ የተሰማው የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ 10 ሺህ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ጦርነቱን ሊቀላቀሉ እንደሚችሉ የደህንነት መረጃዎች ተገኝቷል ካሉ ከአንድ ቀን በኋላ ነው። የደቡብ ኮሪያው ፕሬዚዳንት […]
ለቤተሰብ ሲባል በርካቶች ባለቁበት አደገኛ የባሕር መስመር ደጋግሞ ለመጓዝ መወሰን
ለቤተሰብ ሲባል በርካቶች ባለቁበት አደገኛ የባሕር መስመር ደጋግሞ ለመጓዝ መወሰን ከ 4 ሰአት በፊት ከምዕራብ አፍሪካ በመነሳት በአትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ ወደ አውሮፓ የሚደረገው ጉዞ አደገኛ እና የብዙ ሰዎችን ሕይወት ከሚቀጥፉ መስመሮች መካከል አንዱ ነው። በዚህ አደገኛ የባሕር ላይ ጉዞ ሰዎች ከእንጨት በተሠሩ ጀልባዎች ታጭቀው ለቀናት እንዳንዴም ለሳምንታት ይጓዛሉ። በዚህ የአውሮፓውያን ዓመት ብቻ ከ70 ሺህ በላይ […]