Ethiopia: National Security Council Affirms Remarkable Progress in Ethiopia
9 April 2025 Ethiopian News Agency (Addis Ababa) Addis Ababa, — Ethiopia’s National Security Council has announced significant progress in wide-ranging spheres despite the various challenges facing the country. In a statement released today, the council reviewed the national, regional, and global situations of the country, emphasizing notable strides toward prosperity in the face of challenges. […]
ትራምፕ በአገራት ላይ የጣሉትን ከፍተኛ ታሪፍ ተፈጻሚነት ለ90 ቀናት አዘገዩ
ከ 2 ሰአት በፊት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፍተኛ ታሪፍ በተጣለባቸው አገራት ላይ የቀረጡ ተፈጻሚነት ለ90 ቀናት እንዲዘገይ ማድረጋቸውን አስታወቁ። ፕሬዝዳንቱ ከቻይና ጋር የገቡበት የንግድ ጦርነት ግን እየተባባሰ ቀጥሏል። 60 ገደማ በሆኑ የአሜሪካ አጋር አገራት ላይ ተጣለው ቀረጥ ተፈጻሚ መሆን በጀመረ በሰዓታት ውስጥ ትራምፕ አስገራሚ በሆነ የፖሊሲ ለውጥ የከፍተኛ ታሪፍ ተፈጻሚነትን አዘግይተዋል። በዚህ መሰረት ከአገራቱ ጋር […]
መንግሥት የባሕር በር ጥያቄ ጉዳይ “በተጀመረው ግለት እንዲቀጥል” መመሪያ መስጠቱን አስታወቀ
9 ሚያዚያ 2025 የፌደራል መንግሥት “የኢትዮጵያን የባሕር በር የማግኘት መብት” ለማስከበር የሚያደርገው እንቅስቃሴ “በተጀመረው ግለት እንዲቀጥል አቅጣጫ” ማስቀመጡን አስታወቀ። ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ኢትዮጵያ በቀጣናው “ሰላምንና ደኅንነትን ለማረጋገጥ የነበራትንና ያላትን ከፍተኛ ሚና” እንዲረዳም መንግሥት ጥሪ አቅርቧል። ይህ የፌደራል መንግሥት ውሳኔ የተገለጸው የብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት ዛሬ ረቡዕ፣ ሚያዝያ 1/2017 ዓ.ም. ያደረገውን ስብሰባ በተመለከተ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት […]
በምያንማር በታጣቂዎች ሥር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ወሲባዊ ትንኮሳ እየደረሰባቸው እንደሆነ ተናገሩ
ከ 5 ሰአት በፊት በምያንማር የሳይበር ወንጀል ካምፖች በግዳጅ ሲሰሩ የቆዩ እና አሁን ላይ ከካምፖቹ ወጥተው በታጣቂዎች ቁጥጥር ሥር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ወሲባዊ ትንኮሳ እየደረሰባቸው እንደሆነ ለቢቢሲ ተናገሩ። “ታይላንድ ሥራ አለ” በሚል ተታለው ከአገራቸው እንደወጡ የሚገልጹት እነዚህ ሴቶች፣ወደ ምያንማር ተወስደው በሳይበር የወንጀል ካምፖች ውስጥ በግዳጅ ሲሰሩ መቆየታቸውን ይገልጻሉ። ሴቶቹ ‘ማይዋዲይ ኬኬ2’ እና ‘ኬኬ5’ ከተባሉ የወንጀል […]
የፌስቡክ የቀድሞ ሠራተኛ ኩባንያው ከቻይና ጋር ቅድመ ምርመራ በማድረግ ይሠራ ነበር ስትል ወነጀለች
ከ 1 ሰአት በፊት የፌስቡክ እና ኢንስታግራም ማኅበራዊ ሚዲያዎች ባለቤት የሆነው ሜታ ከቻይና ጋር የ18 ቢሊዮን ዶላር የንግድ ስምምነት ለማድረግ ሲል የብሔራዊ ደኅንነትን ችላ ብሏል ስትል የድርጅቱ የቀድሞ ሠራተኛ ሳራ ዋይን ዊሊያምስ ለአሜሪካ ምክር ቤት ተናገረች። ከዚህ በፊት በፌስቡክ የዓለም አቀፍ የፐብሊክ ፖሊሲ ዳይሬክተር የነበረችው ሳራ ዋይን ዊሊያምስ፣ የድርጅቱ ኃላፊዎች ለቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ የአሜሪካውያንን ጨምሮ […]
ዜሌንስኪ በዩክሬን ውስጥ 155 ቻይናውያን ለሩሲያ ጦር እየተዋጉ ነው አሉ
ከ 49 ደቂቃዎች በፊት የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ በዩክሬን ቢያንስ 155 የቻይና ዜጎች ከሩሲያ ጦር ጎን ተሰልፈው እየተዋጉ ነው ብለዋል። የፕሬዝዳንቱ ይህ አስተያየት የተሰማው፣ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ሁለት ቻይናውያን ወታደሮች በዩክሬን ከተያዙ በኋላ ነው ። ይህ ቻይና ለሩሲያ የሰው ኃይል ትሰጣለች የሚለው የኪየቭ ይፋዊ ውንጀላ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰማ ነው። ረቡዕ ዕለት ፕሬዝዳንቱ ለጋዜጠኞች በሰጡት […]
ቻይና በአሜሪካ ምርቶች ላይ የ84 በመቶ ታሪፍ በመጨመር ለዶናልድ ትራምፕ እርምጃ ምላሽ ሰጠች
9 ሚያዚያ 2025 የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ረቡዕ፣ መጋቢት 24/2017 ዓ.ም. ይፋ ያደረጉት የታሪፍ ጭማሪን ተከትሎ ቻይና ከአሜሪካ በሚገቡ ምርቶች ላይ የ84 በመቶ ታሪፍ መጣሏን ይፋ አድርጋለች። ቤጂንግ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰችው ትራምፕ ባስፈራሩት መሠረት በቻይና ላይ ታሪፉን እጥፍ በማድረግ ወደ 104 በመቶ ከፍ ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው። ይህ የንግድ ጦርነት እየተጋጋለ ሄዶ የኢኮኖሚ ድቀት ያስከትላል የሚል […]
የናይጄሪዋ ቦርኖ ግዛት አስተዳዳሪ ቦኮ ሃራም ተመልሶ ሊመጣ እንደሚችል አስጠነቀቁ
ከ 4 ሰአት በፊት የናይጄርያዋ ቦርኖ ግዛት አስተዳዳሪ የቦኮ ሃራም ተዋጊዎች የግዛቲቱ ሰሜን ምሥራቅ አካባቢ ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት መሰንዘር እና የተወሰኑ አካባቢዎችን መቆጣጠራቸውን ተከትሎ አማጽያኑ ተመልሰው ሊመጡ ይችላል የሚል ስጋት እንዳላቸው ገለፁ። የግዛቱ አስተዳዳሪ ባባጋና ዙሉም፤ በአካባቢው አማፂያኑን ለመዋጋት ተጨማሪ ወታደራዊ ድጋፍ እንዲደረግ ለፌደራል መንግሥቱ ጥሪ አቅርበዋል። የናይጄርያ መንግሥት የአስተዳዳሪውን ፍርሃት ቀለል አድርጎ የተመለከተ ሲሆን፣ […]
ከአህያ ወተት የሚገኘው እና አንድ ኪሎ 170 ሺህ ብር የሚሸጠው አይብ
ከ 5 ሰአት በፊት ሰርቢያ ውስጥ ከአህያ ወተት የሚገኝ አንድ ኪሎ ግራም አይብ 1200 ዩሮ ይሸጣል። ይህ ዋጋ ከአማካይ ሰርቢያዊያን ወርሀዊ ደመወዝ ላቅ ያለ ነው። አይቡ የሚሸጠው ዛሳቪቻ በተባለው የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ግቢ ውስጥ ነው። ይህ ግቢ ከዋና ከተማዋ ቤልግሬድ በስተምዕራብ 80 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል። “አንድ ኪሎ ግራም አይብ ለማግኘት 25 ሊትር ወተት […]
እስራኤል በጋዛ መኖርያ ሕንጻ ላይ በፈጸመችው ጥቃት 29 ሰዎች መገደላቸውን የሕክምና ባለሙያዎች ተናገሩ
ከ 2 ሰአት በፊት እስራኤል በምሥራቅ ጋዛ በመኖርያ ሕንጻ ላይ በፈጸመችው ጥቃት ሕጻናትን ጨምሮ 29 ፍልስጤማውያን መገደላቸውን በአካባቢው የሚገኝ ሆስፒታል ገለፀ። በሃማስ የሚመራው የሲቪል መከላከያ ኤጀንሲ በበኩሉ ማክሰኞ ማለዳ የጦር አውሮፕላኖች ሼጃያ በሚባል ስፍራ በሚገኘው አል ሃዋሺ መስኪድ አቅራቢያ የሚገኙ ቦታዎችን ዒላማ አድርገዋል ብሏል። በእስራኤል የአየር ጥቃት መጀመሪያ ላይ 23 ሰዎች መገደላቸው የተገለፀ ቢሆንም፣ የአደጋ […]
