ሰሜን ኮሪያ ከስድስት ዓመታት በኋላ የመጀመሪያውን ዓለም አቀፍ የማራቶን ውድድር አካሄደች

ከ 2 ሰአት በፊት ሰሜን ኮሪያ ከስድስት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የፒዮንግያንግ ኢንተርናሽናል ማራቶን አካሄደች። በዚህ ውድድር ላይ ከ200 የተለያዩ አገራት የመጡ ሯጮች እንዲሳተፉ ማድረጓ ተገልጿል። እአአ በ1981 የተጀመረው ይህ የማራቶን ውድድር በየዓመቱ በሚያዝያ ወር የአገሪቱን መስራች የሆኑትን ኪም ኢል ሱንግ ልደት ለማክበር ይካሄዳል። ከእሁዱ የማራቶን ውድድር በፊት ውድድሩ ለመጨረሻ ጊዜ የተካሄደው እአአ በ2019 ሲሆን […]

ዚምባብዌ በአሜሪካ ምርቶች ላይ የተጣለውን ታሪፍ ልታነሳ ነው

ከ 4 ሰአት በፊት የዚምባብዌ ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋዋ ከትራምፕ አስተዳደር ጋር “መልካም ግንኙነት” ለመፍጠር በሚል ከአሜሪካ በሚገቡ ምርቶች ላይ የተጣሉ ታሪፎችን እንደሚያነሱ አስታወቁ። ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከዚምባብዌ ወደ አሜሪካ በሚገቡ ምርቶች ላይ 18 በመቶ ታሪፍ ከጣሉ ከቀናት በኋላ ነው የዚምባብዌ መንግሥት እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው። “ይህ እርምጃ ከአሜሪካ የሚገቡ ምርቶችን በዚምባብዌ ገበያ ውስጥ ለማስፋፋት እንዲሁም […]

የትራምፕን ታሪፍ ተከትሎ ከ50 በላይ አገራት ለመነጋገር መጠየቃቸውን የአሜሪካ ባለስልጣናት ተናገሩ

ከ 4 ሰአት በፊት የዶናልድ ትራምፕ የታሪፍ ውሳኔ ተከትሎ ከ50 በላይ አገራት ወደ አሜሪካ ስለሚልኳቸው ምርቶች ለመነጋገር ዋይት ሃውስን መጠየቃቸውን ባለስልጣናት ተናገሩ። የፕሬዚዳንቱን ታሪፍ ተከትሎ የአሜሪካ አክሲዮን ገበያ ከፍተኛ ቅናሽ ያሳየ ሲሆን የዓለም ገበያ ላይም ለውጥ ታይቷል። ይኹን አንጂ የትራምፕ ባለስልጣናት ኢኮኖሚው ላይ የሚኖረውን ዘላቂ ጫና አሳንሰው አቅርበዋል። የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ እና አማካሪዎቻቸው በገቢ […]

100 ዓመት ገደማ የሆናቸው ኤሊዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ወላጆች ሊሆኑ ነው

ከ 2 ሰአት በፊት በአሜሪካ 100 ዓመት ገደማ የሆናቸው ኤሊዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ወላጆች ሊሆኑ ነው። በፊላደልፊያ መካነ አራዊት የሚኖሩት እነዚህ ኤሊዎች ዝርያቸው ሊጠፋ የተቃረበ እና በከፍተኛ ሁኔታ ቁጥራቸው የተመናነመነ ነው። አብራዞ እና ማሚ የተሰኙት ኤሊዎች ከጣሏቸው ውስጥ አራት ዕንቁላሎች ተፈልፍለው ጫጩቶች መሆናቸው በከፍተኛ ሁኔታ እንዳስደሰተው ነው መካነ አራዊቱ የገለጸው። የጫጩቶቹ መገኘት በመካነ አራዊቱ ከ150 ዓመት […]

የስሜት መዋዠቅዎን የሚያስተካክሉ አምስት መንገዶች

ከ 5 ሰአት በፊት አንዳንድ ቀን አለ፤ ጨፍጋጋ፤ ቀርፋፋ፣ ራስን ከአልጋ ውስጥ ጎትቶ ለማውጣት የሚከብድበት። በእንዲህ ዓይነት ጠይም ቀን የተዘጋጀ ምግብ ተነስቶ መብላት፣ ከአልጋ ተነስቶ ተጣጥቦ መውጣት ይጫጫናል። የገዛ አካልን ለማዘዝ ይቸግራል። ድብት፤ ቅዝዝ በሚል በዚህ ቀን የሚደውል፤ ቤት መጥቶ ሊያገኝዎት የሚፈልግ ሰው ባይኖር ይመኛሉ። ስልክ አጥፍቶ ለጥ ማለት ብቸኛ አማራጭ ይመስላል። መጫጫን፤ ከውስጥዎ ያለው […]

በመድኃኒት እስከ 38 ኪሎ ውፍረት የቀነሱ ሴቶች ስለ ልምዳቸው ምን ይላሉ?

ከ 5 ሰአት በፊት ከመጠን በላይ ውፍረት ከስንፍና እና ከአስቀያሚነት ጋር በሚያይዝባት ዓለም በርካቶች በውፍረታቸው ምክንያት ይሸማቀቃሉ፣ መድልዎም ይደርስባቸዋል። ከመጠን በላይ ወፍራም የነበረችው ብራኔይሻ ኩፐር ለየት ያለ ፍጡር ነኝ የሚል ስሜት ይሰማት ነበር። አካሏም ሌሎችን ይማርካል የሚል ሃሳብ አልነበራትም። ከጓደኞቿ ጋር አብረው ለመዝናናት በሚወጡበት ወቅት ሌሎች በሰዎች ትኩረቶችን ሲያገኙ እሷን ዘወር ብሎ የሚመለከታት አልነበሯም። የሚመለከቷትም […]

የአማራ ክልል የሀገራዊ ምክክር የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ተጀመረ  – ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

April 5, 2025 በተስፋለም ወልደየስ በመጪው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ከአማራ ክልል የሚቀርቡ አጀንዳዎችን የማሰባሰብ ሂደት፤ ዛሬ ቅዳሜ መጋቢት 27፤ 2017  በባህርዳር ከተማ በይፋ ተጀመረ። የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎችን ወክለው በባህርዳር ከተማ የተሰባሰቡ ከ4,500 በላይ ተሳታፊዎች፤ ክልሉን በመወከል በሀገር አቀፉ ጉባኤ የሚሳተፉ ተወካዮችን ይመርጣሉ። በባህርዳር ዩኒቨርስቲ ስቴዲየም በተካሄደው በዛሬው የመክፈቻ ስነ ስርዓት ላይ የተገኙት የማህበረሰብ ክፍሎቹ ተወካዮች፤ […]