የመከላከያ አቅሞችን የምናጎለብተው “ለመዋጋት አይደለም” – ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ  – ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

March 9, 2025 ኢትዮጵያ የመከላከያ አቅሟን የምታጎለብተው “ትናንሽ አቅም ይዘው ለሚሳሳቱ ኃይሎች ብዙ ጊዜ [ሰጥተው] እንዲያስቡ ለማስቻል” እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ “እነዚህን አቅሞች የምናጎለብተው ለመዋጋት አይደለም። ውጊያን ለማስቀረት ነው” ብለዋል። አብይ ይህን ያሉት “ስካይ ዊን ኤሮኖቲክስ ኢንዱስትሪ” የተባለ የሰው አልባ አውሮፕላኖች (ድሮኖች) ማምረቻ ትላንት ቅዳሜ የካቲት 29፤ 2017 በመረቁበት ወቅት በሰጡት ገለጻ […]