ሩሲያ ወደተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተቃጡ በርካታ የድሮን ጥቃቶችን መክቻለሁ አለች

ከ 5 ሰአት በፊት የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ወደ ስምንት የሀገሪቱ ክፍሎች የተቃጡ በርካታ የድሮን ጥቃቶችን ማክሸፉን አስታወቀ። ከተሰነዘሩት ጥቃቶች ትልቁ የሚባለው በሩሲያዋ ክራስኖዳር የተከሰተው ሲሆን በሥፍራው የነበረ የነዳጅ ማጣሪያ ጉዳት ደርሶበታል። ስላቭያንስክ-ኦን-ኩባን በተባለው የነዳጅ ማጣሪያ ላይ በተሰነዘረው ጥቃት የሞተ ሰው እንደሌለ የተዘገበ ሲሆን በጥቃቱ ምክንያት የተነሳው እሣትም በቁጥጥር ሥር ውሏል። ሩሲያ ጠቅላላ ምርጫ እያካሄደች ሲሆን […]

በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ዕጦት እስከ መቼ ፈተና ሆኖ ይቀጥላል?

እኔ የምለዉ በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ዕጦት እስከ መቼ ፈተና ሆኖ ይቀጥላል? አንባቢ ቀን: March 17, 2024 በአውግቸው ኪዳኑ ይህንን ርዕስ ይዤ ስነሳ የኢትዮጵያ ታሪክ፣ ያለፈችባቸው ውጣ ውረዶችና አሁን እየገጠሟት ያሉ ፈተናዎች ሁላችንንም ያሳስቡናል ብዬ ስለማምን ነው፡፡ ኢትዮጵያ በብዝኃነት ብቻ ሳይሆን በሕዝብ ቁጥርም በአፍሪካ ትልቅና ሰፊ የምትባል አገር ነች፡፡ ከ80 የማያንሱ የየራሳቸው ባህል፣ ቋንቋና ማንነት ያላቸው ብሔር […]

ለዘመናዊው ኢኮኖሚ አዲስ የንድፈ ሐሳብ ዕይታ አስፈላጊነት

እኔ የምለዉ ለዘመናዊው ኢኮኖሚ አዲስ የንድፈ ሐሳብ ዕይታ አስፈላጊነት አንባቢ ቀን: March 17, 2024 በፍጹም በላይሁን ኢኮኖሚ ማለት ማምረት፣ ማሠራጨትና መጠቀም (Production, Distribution and Consumption) ማለት ሲሆን፣ በዚህ ሒደት ውስጥ ዋና ተዋናዮች አምራችና ሸማች ወይም ሻጭና ገዥ ናቸው። እነዚህ ተዋናዮች በሚያደርጉት የምርት ልውውጥ ውስጥ  የምርቱን ዋጋ ማን ይተምን የሚለው ጥያቄ መመለስ ይኖርበታል።  በዚህም  መሠረት ታዋቂው […]

‹‹እንኳን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መገንባት የአገሪቱ ህልውናም እንዴት ነው ተጠብቆ የሚቀጥለው የሚለው ጉዳይ ጥያቄ እየሆነ መጥቷል›› መላኩ ተገኝ (ዶ/ር)፣ አንጋፋ ፖለቲከኛና ጸሐፊ

ዮናስ አማረ March 17, 2024 ቆይታ የአለማያ ኮሌጅ ተማሪዎች ማኅበር ምክትል ፕሬዚዳንት ነበሩ፡፡ ያኔ እነ ጥላሁን ግዛው የተገደሉበትና ለውጥ ጠያቂ ወጣቶች የታፈነ እልህና ቁጭት የሚንጣቸው ጊዜ ነበር፡፡ በጊዜው አለማያ ኮሌጅ ከሦስተኛ ክፍለ ጦር የተወሰነ ጦር መጥቶ ግቢውን በመክበብ ለ15 ቀናት ተማሪዎች ሳይንቀሳቀሱ መቆየታቸውንም ያስታውሳሉ፡፡ የትግል መንፈሳቸው መነቃቃት የጀመረው እዚሁ አገር ቤት ኔዘርላንድስ ከመሄዳቸው በፊት መሆኑን ይናገራሉ፡፡ ‹‹እኔን የመሳሰሉ ሰዎች ወደ ውጭ የሄድነው እኮ ለመማርና ለመሥራት አይደለም፣ ተደራጅቶ አብዮታዊ ትግል ለማድረግ ይጠቅማል በሚል ነበር፤›› ሲሉም ይናገራሉ፡፡ በኔዘርላንድስ ኢንስቲትዩት ኦፍ ሶሻል ስተዲስ የፖስት ግራጁዌት ዲፕሎማ ተምረዋል፡፡ በዚሁ ጊዜ ጎን ለጎን ደግሞ የኦልተርኔቲቭ ፖለቲክስ ትምህርት ተከታትለው ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ተቀብለዋል፡፡ ከደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ በዴቨሎፕመንት ሶሺዮሎጂ ሦስተኛ ዲግሪያቸውን (ፒኤችዲ) ወስደዋል፡፡ በሥራ ረገድ የፋኖስ ኢትዮጵያ ዳይሬክተር ሆነው ሠርተዋል፡፡ የናይል ተፋሰስ ዲስኩር ዳይሬክተርም ነበሩ፡፡ በአፍሪካ ኅብረት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የነባር ሕዝቦች ጥናት ቡድን ውስጥ አገልግለዋል፡፡ በተመድ የሰብዓዊ መብቶች ድርጅት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሊቀመንበር፣ እንዲሁም በወሰን አካባቢ ሕዝቦች መብት ተሟጋች ዓለም አቀፋዊ ካውንስል አባልም በመሆን አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡ ከተማሪዎች የፖለቲካ ንቅናቄ እስከ ኔዘርላንድስ የደረሰ የፖለቲካ ትግል አድርገዋል፡፡ መላኩ ተገኝ (ዶ/ር) ‹‹ከሰንጋ ተራ እስከ አምስተርዳም›› የተባለ ግለ ታሪካቸውን ያሰፈሩበት መጽሐፍ አበርክተዋል፡፡ የአብዮቱን 50ኛ ዓመት በተመለከተ ሰፊ ጉዳዮችን ያነሱበት ዮናስ አማረ ከእሳቸው ጋር ያደረገው ቆይታ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡ ሪፖርተር፡- አብዮቱ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ትርጉም ያለው ለውጥ ማምጣቱን፣ የመሬት ጥያቄን ደርግ መመለሱን፣ እንዲሁም የብሔሮችን ጥያቄ ኢሕአዴግ ፈቶታል ቢባልም አብዮቱ ያነሳቸው ጥያቄዎች አሁንም አልተመለሱም የሚሉ አሉ፡፡ የመሬት ጥያቄ፣ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት፣ የሰብዓዊና የዴሞክራሲ መብቶች ጥያቄ የመሳሰሉት በአብዮቱ ወቅት የተነሱ በርካታ ጉዳዮች አልተመለሱም ስለመባሉ ምን ይላሉ? መላኩ (ዶ/ር)፡- በእኔ ግምት የየካቲት አብዮት እኮ ተሸንፏል፡፡ ተሸነፈ ማለት ደግሞ የተነሳበትን ዓላማ አላሳካም ማለት ነው፡፡ ከሕዝባዊ መንግሥት ይቋቋም ጀምሮ እስከ ሴቶች መከበር ድረስ በርካታ በርካታ ጥያቄዎች ነበር ይዞ የተነሳው፡፡ ከእነዚህ ጥያቄዎች ውስጥ ወደ 95 በመቶ አልተመለሱም፡፡ ተድበስብሶ የመሬት አዋጅ ቢታወጅም ይህ […]

የግብይት ሥርዓቱን ለማዘመንም ሆነ መስመር ለማስያዝ ሥር ነቀል ለውጥ ያስፈልጋል!

MARCH 17, 2024 ናታን ዳዊት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ከግብይት ሥርዓት ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ሰሞኑን ማብራሪያ ሰጥተው ነበር፡፡ በዚህ ማብራሪያዎች የግብይት ሥርዓቱን ለማሻሻል የተወሰዱ ዕርምጃዎችንና ተገኘ ያሉትንም ውጤት ምሳሌዎችን በመጥቀስ ጭምር ገልጸዋል፡፡  ካነሷቸው ነጥቦች መካከል ከግማሽ ምዕት ዓመት በኋላ የአገሪቱ የንግድ ሕግ መሻሻል የግብይት ሥርዓቱን እያዘመነው ነው የሚለው ይገኝበታል፡፡ በእርግጥ የግብይት ሥርዓቱን ለማዘመን የንግድ […]

ጠንካራ ተቋማት ሲኖሩ ሕገወጦች በዜጎች ሕይወት ላይ አይቀልዱም!

March 17, 2024 ርዕሰ አንቀጽ ሰሞኑን አምስት መንግሥታዊ ተቋማት ማለትም የግብርና ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ ኢትዮጵያ ፖስታና ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የስኬት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡ በሥራቸው የተመሰከረላቸው ተቋማት ሲሸለሙ መልካም የሆነውን ያህል፣ ሽልማቱም የበለጠ ለመሥራት የሚያነሳሳ መሆን ይገባዋል፡፡ የግብርና ሚኒስቴር በስንዴ ልማት ፕሮግራም ከተሸላሚዎች ተርታ የተገኘ ብቸኛ የሚኒስቴር […]

ከመቅደላ የተዘረፉ የኢትዮጵያ ቅርሶች

አስተያየት By አንባቢ March 17, 2024 በዲ/ን ተረፈ ወርቁ ከጥቂት ዓመታት በፊት ‹‹ራዕየ ዮሐንስ የዓለም መጨረሻ›› በሚል ርዕስ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ባስነበበው መጽሐፉ ገጽ 18  ላይ፣ ከመቅደላ ዝርፊያ ጋር በተያያዘ የሚከተለውን መረጃ አጋርቶን ነበር፡፡ እቴጌ ምንትዋብ ራዕይ መጽሐፍን አስጽፈው ለጎንደር ደረስጌ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ለራሳቸውና ለልጃቸው ለኢያሱ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ መስጠታቸውንና ይህም መጽሐፍ በመቅደላው ወረራ ጊዜ እንግሊዞች ዘርፈው ወስደው አሁንም ድረስ በብሪትሽ ቤተ መጻሕፍት በMSOr. 533 ተመዝግቦ ይገኛል፡፡ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ሀብትና ኩራት የሆኑ ቅርሶቻችንና የቤተ ክርስቲያናችን ጥንታዊ የብራና መጻሕፍትና ንዋያተ ቅድሳት ወደ አውሮፓ እንዲሻገሩ ምክንያት ከሆኑት መካከል የመቅደላው ጦርነት […]

የፕሪቶሪያ ስምምነት ትግበራ ሊፈጥረው የሚችለው የፖለቲካ ኃይል አሠላለፍ ልዩነት

ተደራዳሪዎች የፕሪቶሪያ ስምምነት ከተፈራረሙ በኋላ ፖለቲካ የፌዴራል መንግሥትና የሕወሓት ተደራዳሪዎች የፕሪቶሪያ ስምምነት ከተፈራረሙ በኋላ በዮናስ አማረ March 17, 2024 የሰላም ጥረት ገና ሲጀመር ጀምሮና ወደ ፕሪቶሪያ ስምምነትም ሲገባ አርቆ አሳቢ ወገኖች ሒደቶቹ ሁሉንም ወገን አቃፊ እንዲሆኑ ሲወተውቱ ነበር፡፡ በጦርነቱ ተሳታፊ የነበሩ ሁሉም ኃይሎች የሚያነሱት የየራሳቸው ጥያቄ መኖሩን በመጥቀስ፣ ይህ ጥያቄያቸው በተቻለ መጠን በተመጣጣኝ ሁኔታ የሚስተናገድበት […]

በፓርላማ በተፎካካሪ ፓርቲ ተይዞ የነበረው የመንግሥት ወጪ ቁጥጥር ሰብሳቢነት ለብልፅግና ተሰጠ

የቀድሞ የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ክርስቲያን ታደለና አዲሷ የመንግሥት ወጪ አስተዳደር ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሺመቤት ደምሴ (ዶ/ር) ዜናበፓርላማ በተፎካካሪ ፓርቲ ተይዞ የነበረው የመንግሥት ወጪ ቁጥጥር ሰብሳቢነት ለብልፅግና ተሰጠ ሲሳይ ሳህሉ ቀን: March 17, 2024 በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለረዥም ዓመታት በምርጫ አሸንፈው ፓርላማውን ለተቀላቀሉ ተፎካካሪና አጋር የፖለቲካ ፓርቲ […]