በአገር ውስጥ የአውሮፕላን መለዋወጫዎችን ለማምረት የሚያስችል ስትራቴጂ እየተዘጋጀ መሆኑ ተገለጸ

በናርዶስ ዮሴፍ September 8, 2024 የኢትዮጵያ አቪዬሽን ኢንዱስትሪ በአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ብቻ ተከልሎ ከቆየበት፣ ወደ አውሮፕላን መለዋወጫዎች አምራችነት እንዲስፋፋ የሚያስችል የዘርፍ የሽግግር ፕሮግራም ይፋ ተደረገ። የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ተወካዮች፣ ከግብርና ሚኒስቴርና ከትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ደኤታዎች፣ ከግል አቪዬሽን ተቋማትና ከዘርፉ ባለሙያዎች ጋር ባካሄደው የግማሽ ቀን የምክክር ወቅት ነው ፕሮግራሙ […]

ኢዜማ ለሌሎች ፓርቲዎች ጭምር የአመራር ሥልጠና መስጠት የሚያስችል አካዴሚ መገንባቱን ይፋ አደረገ

ዜና ኢዜማ ለሌሎች ፓርቲዎች ጭምር የአመራር ሥልጠና መስጠት የሚያስችል አካዴሚ መገንባቱን ይፋ አደረገ ዮናስ አማረ ቀን: September 8, 2024 ለአባላቱ የአመራር ሥልጠና የሚሰጥ አካዳሚ መገንባቱን ይፋ ያደረገው የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ)፣ ለሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶች አባላትም ቢሆን ሥልጠና እንደሚሰጥ ገለጸ፡፡ የኢትዮጵያን ፖለቲካ በዕውቀት፣ በእውነት፣ በስክነትና በምክንያት እንዲመራ ለማድረግ የበኩሉን እየተወጣ እንደሆነ የተናገረው ኢዜማ፣ የራሱን የማሠልጠኛ […]

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከዓለም ባንክ የ545 ሚሊዮን ዶላር ብድር ማግኘቱን አስታወቀ

በፅዮን ታደሰ September 8, 2024 ሽፈራው ተሊላ (ኢንጂነር) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ጋር በመሆን ለሚያከናውናቸው የመልሶ ግንባታና የአቅም ማሻሻያ ሥራዎች የሚውል 545 ሚሊዮን ዶላር ብድር ከዓለም ባንክ መገኘቱን አስታወቀ፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ይህንን ያስታወቀው የ2016 ዓ.ም. አፈጻጸምንና በ2017 ዓ.ም. የትኩረት መስኮች፣ እንዲሁም አዲሱን የኤሌክትሪክ ታሪፍ ማሻሻያ አስመልክቶ ነሐሴ 29 ቀን 2016 ዓ.ም. ጋዜጣዊ […]

በጉራጌ ዞን የተከሰተው ችግር ከፀጥታ ኃይሉ አቅም በላይ መሆኑ ተገለጸ

ዜና በጉራጌ ዞን የተከሰተው ችግር ከፀጥታ ኃይሉ አቅም በላይ መሆኑ ተገለጸ ፅዮን ታደሰ ቀን: September 8, 2024 ጎጎት ለጉራጌ አንድነትና ፍትሕ ፓርቲ በወሰን ማስከበርና በሌሎችም ምክንያቶች በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የተከሰተው የፀጥታ ችግር ከዞኑ የፀጥታ ኃይል አቅም በላይ በመሆኑ፣ አብዛኛዎቹ አካባቢዎች በመከላከያ ሠራዊት ሥር አንደሚገኙ ተገለጸ። ጎጎት ለጉራጌ አንድነትና ፍትሕ ፓርቲ (ጎጎት) በዞኑ ያለውን […]

የአፍሪካ ቀንድ የፖለቲካ ትኩሳት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ የፈጠረው ጫና

September 8, 2024  የአፍሪካ ቀንድ የፖለቲካ ትኩሳት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ የፈጠረው ጫና ባለፈው ሃምሌ ወር የኤርትራ ሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አስመራ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከመስከረም 20 ጀምሮ እንዲያቆም የሚያዝ አንድ መስመር ደብዳቤ ከላከ በኋላ በአስመራ የሚገኘው የአየር መንገዱ የባንክ ሂሳብ በመታገዱ አየር መንገዱ በረራውን ለማቋረጥ እንደተገደደ አስታውቋል። በ1990 ዓ/ም ግንቦት ወር […]

የኮሪያ መንግሥት ለኢትዮጵያ ፕሮጀክቶች የሁለት ቢሊዮን ዶላር ፋይናንስ ለማቅረብ ተስማማ

በኢትዮጵያ የኮሪያ አምባሳደር ጁንግ ካንግ ዜና የኮሪያ መንግሥት ለኢትዮጵያ ፕሮጀክቶች የሁለት ቢሊዮን ዶላር ፋይናንስ ለማቅረብ ተስማማ ናርዶስ ዮሴፍ ቀን: September 8, 2024 የኮሪያ መንግሥት ኢኮኖሚያዊ ልማት ትብብር ፈንድ አስፈጻሚ ኤጀንሲው በሆነው ኤግዚም ባንክ በኩል፣ ለኢትዮጵያ ስምንት ፕሮጀክቶች በሁለት ዓመታት ውስጥ ሁለት ቢሊዮን ዶላር ፋይናንስ ለማቅረብ መስማማቱ ታወቀ። የገንዘብ ሚኒስቴር ባለፈው ሳምንት ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚያሳየው፣ […]

ግብጽን ያንደረደረው ውጥረት በሶማሊያና ኢትዮጵያ መካከል

September 8, 2024 – DW Amharic  ግብጽ ከሰሞኑ የጦር መሣሪያዎችን በወታደራዊ አውሮፕላን ጭና ሞቃዲሾ ማስገባቷ ይፋ ከሆነ በኋላ በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል ወታደራዊ ፍጥጫው እጅግ አይሏል ። ሁኔታዎች ወደየት እያመሩ ይሆን?… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

ኢትዮጵያን በፓሪስ የፓራሊምፒክስ ውድድር በወርቅ ያደመቀችው አትሌት ትዕግሥት ገዛኸኝ

ከ 8 ሰአት በፊት ኢትዮጵያ በዘንድሮ ፓራሊምፒክስ ውድድር ላይ አራት አትሌቶችን አሰልፋ ሦስት ሜዳልያዎችን አግኝታለች። በፈረንሳይ ፓሪስ አዘጋጅነት በተካሄደው የ2024 ፓራሊምፒክ በ1500 ሜትር በከፊል ማየት በተሳናቸው፣ ሙሉ በሙሉ ማየት በተሳናቸው፣ የእጅ ጉዳት ባለባቸው አትሌቶች ነው ኢትዮጵያ ተወክላ የነበረው። አትሌት ያየሽ ጌጤ በቲ 11 ምድብ፣ ሙሉ በሙሉ ዓይነስውር፣ የዓለም ክብረ ወሰንን በማሻሻል ወርቅ ስታገኝ፤ ትዕግሥት ገዛኸኝ […]

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ሶማሊያ “ከታሪካዊ ጠላት ጋር” በመሆን ያልተገባ እንቅስቃሴ እያደረገች ነው አሉ

ከ 4 ሰአት በፊት የኢፌድሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ጎረቤት አገር ሶማሊያ ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላት ጋር በመሆን በቀጠናው ያልተገባ እንቅስቃሴ እያደረገች ነው ሲሉ ወቀሱ። ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ቅዳሜ ጵጉሜ 2/2016 ዓ.ም. በምስራቅ ዕዝ 47ኛ ዓመት የምስረታ ክብረ በዓል የመዝጊያ ሥነ ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር “የኢትዮጵያ መልማት የሚያንገበግባት ታሪካዊ ጠላታችን […]

ባይደን ከሰሜኑ ጦርነት ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያና ኤርትራ ባለሥልጣናት ላይ ማዕቀብ የሚያስጥለው ትዕዛዝ እንዲራዘም ወሰኑ

ከ 7 ሰአት በፊት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ጋር በተያያዘ ባለሥልጣናት ላይ ማዕቀብ መጣል የሚያስችለው ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ ለተጨማሪ አንድ ዓመት እንዲራዘም ወሰኑ። ፕሬዝዳንቱ አርብ ጳጉሜ 1/2016 ዓ.ም. በጻፉት ደብዳቤ “የኢትዮጵያን ሰላም፣ ደኅንነት እና መረጋጋትን አደጋ ላይ ጥሎ የቆየው በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ አሁንም የአሜሪካ ብሔራዊ ደኅንነት እና የውጪ ፖሊስ ላይ የማይገመት አደጋ […]