ኤርትራ “ትርጉም የለሽ ውዝግብ ውስጥ ለመግባት ፍላጎት የለኝም” ስትል የኢትዮጵያን ክስ አጣጣለች

ዳታን በመቆጠብ ጽሑፍ ብቻ ለማንበብ 9 የካቲት 2026, 13:05 EAT ኤርትራ የኢትዮጵያ ያቀረበችባትን ክስ “ትርጉም የለሽ” በማለት በዚህ ውዝግብ ውስጥ ለመግባት ፍላጎት እንደሌላት በማስታወቂያ ሚኒስቴሯ በኩል ባወጣችው አጭር መግለጫ አስታወቀች። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት በመግባት የተወሰኑ አካባቢዎችን ተቆጣጥራለች እንዲሁም ታጣቂዎችን ትደግፋለች ሲል ቅዳሜ ዕለት በጻፈው ደብዳቤ ክስ እና የድርድር ጥያቄ አቅርቦ […]

“የወሊድ ምጣኔን ለማሳደግ ከውጭ አገር ሴቶችን እናስገባ” ያሉ የደቡብ ኮሪያ ባለሥልጣን ከፓርቲያቸው ተባረሩ

ዳታን በመቆጠብ ጽሑፍ ብቻ ለማንበብ 9 የካቲት 2026, 16:20 EAT በደቡብ ኮሪያ እያሽቆለቆለ ያለውን የወሊድ ምጣኔ ለመጨመር “ከቬትናም ወይም ከሲሪ ላንካ ወጣት ሴቶችን እናስመጣ” ያሉ ባለሥልጣን ከፓርቲያቸው ተባረሩ። የደቡባዊ ጂንዶ አውራጃ ኃላፊ የሆኑት ኪም ሂ ሶ ይህን አስተያየታቸውን የሰጡት ባለፈው ሳምንት ባካሄዱት ስብስባ ወቅት ነበር። ኪም በንግግራቸው “ሴቶቹ በገጠር አካባቢ የሚገኙ ወጣት ወንዶችን ሊያገቡ ይችላሉ” […]

“ባረፍንበት ሆቴል ክፍል በተደበቀ ካሜራ ተቀርጸን እራሳችንን የልቅ ወሲብ ድረ ገጽ ላይ አገኘነው”

ዳታን በመቆጠብ ጽሑፍ ብቻ ለማንበብ ከ 7 ሰአት በፊት ማስጠንቀቂያ፡ ይህ ጽሑፍ አስጸያፊ አገላለጾች ይዟል። በአውሮፓውያኑ በ2023 አንድ ምሽት ላይ ኤሪክ ማኅበራዊ ሚዲያ እየተመለከተ ነበር። ልቅ ወሲብ ከሚታይባቸው ድረ ገጾች በአንዱ ላይ ፈጽሞ ያልጠበቀው ነገር አየ። ጥንዶች ወደ ሆቴል ክፍል ገብተው ሻንጣቸውን ያስቀምጣሉ። ከዚያም ወሲብ ሲፈጽሙ ይታያል። እነዚህ ጥንዶች እራሱ ኤሪክ እና የፍቅር አጋሩ ነበሩ። […]