ኬንያ በወር በአማካይ 122 ሚሊዮን ኪሎ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል ከኢትዮጵያ ትገዛለች።

September 23, 2024 – Konjit Sitotaw  ኬንያ፣ ባለፈው ዓመት ከጥር እስከ ሰኔ በስድስት ወራት ውስጥ ከኢትዮጵያ የገዛችው ኤሌክትሪክ ኃይል ካለፈው የፈረንጆች ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ88 በመቶ ብልጫ እንዳለው የአገሪቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ኬንያ፣ በስድስቱ ወራት ውስጥ ከኢትዮጵያ የገዛችው ኃይል፣ 672 ነጥብ 26 ሚሊዮን ኪሎ ዋት ሰዓት እንደኾነ ዘገባዎቹ አመልክተዋል። ኬንያ ባሁኑ ወቅት በወር በአማካይ 122 ሚሊዮን ኪሎ […]

በአዲስ አበባ ከፍተኛ የነዳጅ እጥረት ተከስቷል።

September 23, 2024 – Konjit Sitotaw  በአዲስ አበባ ከፍተኛ የነዳጅ እጥረት ተከስቷል። የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን፣ በከተማዋ የነዳጅ እጥረት የተፈጠረበትን ምክንያት በማጣራት ላይ እንደኾነ መናገሩን የመንግሥት ዜና ምንጮች ዘግበዋል። በርካታ ማደያዎች በረጃጅም ሰልፎች ተጨናንቀው ውለዋል። ባለሥልጣኑ፣ ለአዲስ አበባ በቀን እስከ 1 ነጥብ 4 ሚሊዮን ሊትር የሚደርስ ነዳጅ እንደሚያሠራጭና ከጅቡቲ የሚገባው ነዳጅም ከአገሪቱ ፍላጎት ጋር ተቀራራቢ መኾኑን ገልጦ፣ የእጥረቱን […]