እያሽቆለቆለ ለመጣው የተማሪዎች ውጤት እና የትምህርት ጥራት መፍትሄ ይኖረው ይሆን?

September 23, 2024 – DW Amharic  በኢትዮጵያ ባለፉት ተከታታይ ሶስት ዓመታት በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ላይ እየተመዘገበ ያለው ውጤት ብዙዎችን እያሳሰበ ነው። በስርዓተ ትምህርቱ ፣በትምህርት ጥራት እና አሰጣጥ ላይም ጥያቄ እንዲነሳ እያደረገ ነው። ታዲያ የችግሩ መንስኤ ምንድነው? ተማሪዎች መምህራን ወይስ ስርዓተ ትምህርቱ?መፍትሄውስ?… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

የአንጋፋው ጋዜጠኛ ጌታቸው ኃይለማሪያም የ30ኛ ዓመት ህልፍተ ህይወት መታሰቢያ ተካሔደ

September 22, 2024 – DW Amharic  ጋዜጠኛ ጌታቸው ኃይለማርያም በኢትዮጵያ ራዲዮ እና ቴሌቭዥን በተለያዩ ኃላፊነቶች ያገለገለ የዶይቼ ቬለው ነጋሽ መሐመድን ጨምሮ አንጋፋ ባለሙያዎች በክብር የሚያስታውሱት ባለሙያ ነበር። በዜና አጻጻፍ እና አቀራረብ የተለየ ክህሎት እንደነበረው የሚነገርለት ጌታቸው ጋዜጠኞች የመስክ ዘገባ እንዲሰሩ በማድረግ ላቅ ያለ አስተዋጽዖ አርክቷል።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

‘አስቀያሚ አጨዋወት’ እና ‘ተአምር’ የታየበት የማንቸስተር ሲቲ እና የአርሰናል ጨዋታ ምን አስመለከተን?

ከ 3 ሰአት በፊት ማንቸስተር ሲቲ በሜዳው አርሰናልን አስተናግዶ 2 ለ 2 በተጠናቀቀው ጨዋታ አንድ ቡድን ለመጫወት ወደ ሜዳ ገብቷል ሲል በርናንዶ ሲልቫ መድፈኞቹን ወቅሷል። የለንደኑ ክለብ “አስቀያሚ አጨዋወትን” መርጧል ሲሉም የሲቲ ተጫዋቾች ወቅሰዋል። የአርሰናል አሰልጣኝ ማይክል አርቴታ በበኩሉ ሁለተኛውን አጋማሽ በ10 ተጫዋች ተጫውተው ለድል አፋፍ መድረሳቸውን ‘ተአምር’ ብሎታል። አርሰናል ሦስት ነጥቡን በእጁ አስገብቶታል ተብሎ […]

ግለሰቦችን፣ ቡድኖችን፣ ተቋማትን እና አገራትን ዒላማ የሚያደርገው ሞሳድ ማን ነው?

ከ 5 ሰአት በፊት ባለፈው ሳምንት በሊባኖስ ከተፈጸሙት በሺዎች የሚቆጠሩ ከትንንሽ ነገር ግን ከአደገኛ ፍንዳታዎች ጀርባ በርካቶች የእስራኤል እጅ አለበት ብለው ያምናሉ። ምክንያታቸው ደግሞ እንዲህ ያለውን የረቀቀ እና የተቀነባበረ ጥቃት በዓለም ላይ ከአገሪቱ የስለላ ድርጅት ሞሳድ ውጪ ማንም ይፈጽመዋል ብለው ስለማያስቡ ነው። ፍንዳታዎቹ በዋናነት ኢላማ ያደረጉት በኢራን የሚደገፈው እና እስራኤል መሪዎቹን እንዲሁም አባላቱን እያሳደደች የምትገድልበት […]

በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደርን ጨምሮ ሌሎች ዲፕሎማቶች ላይ የቦምብ ጥቃት ተፈጸመ

ከ 2 ሰአት በፊት በሰሜን ምዕራብ ፓኪስታን በጉብኝት ላይ የነበሩ የኢትዮጵያ አምባሳደርን ጨምሮ ሌሎች ዲፕሎማቶች በነበሩበት በተፈጸመ የቦምብ ጥቃት አንድ የፖሊስ መኮንን መሞቱን የአገሪቱ ባለሥልጣናት አስታወቁ። ሮይተርስ የዜና ወኪል የስዋት ግዛት ፖሊስ ኃላፊን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው የውጭ አገር ዲፕሎማቶቹ በአካባቢው ያለን ቱሪስት ሥፍራ ለመጎብኘት ሲጓዙ ነው መንገድ ዳር በተጠመደ ቦምብ ጥቃቱ የደረሰው። “ዲፕሎማቶቹን እየመራ ሲሄድ […]

ትራምፕ በመጪው ምርጫ ከተሸነፉ ዳግም ለፕሬዝዳንትነት እንደማይወዳደሩ ጠቆሙ

ከ 4 ሰአት በፊት የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንትና የአሁኑ የካማላ ሐሪስ ተፎካካሪ ዶናልድ ጄ ትራምፕ በመጪው ምርጫ ካላሸነፉ በፈረንጆቹ 2028 እንደማይወዳደሩ ጠቆሙ። የ78 ዓመቱ የዕድሜ ባለጸጋ ትራምፕ ላለፉት ሦስት ተከታታይ የፕሬዝዳንታዊ ምርጫዎች ሪፐብሊካንን ወክለዋል። በቅርቡ ባደረጉት አንድ ቃለምልልስ በቀጣይ ምርጫ በካማላ ሐሪስ ከተሸነፉ ከ4 ዓመት በኋላ ዳግም ይወዳደራሉ ወይ ተብለው ሲጠየቁ፣ “አይመስለኝም። አላደርገውም” ብለዋል። ይሁንና መጪውን […]