ትራምፕ በኢራን የግድያ ሙከራ ሊደረግባቸው እንደሚችል የአሜሪካ ደኅንነት እንዳስጠነቀቃቸው ተገለጸ

25 መስከረም 2024 የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን የግድያ ሙከራ ሊደረግባቸው እንደሚችል የአሜሪካ ደኅንነት እንዳስጠነቀቃቸው ተገለጸ። እጩው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከኢራን “እውነተኛና ግልጽ የግድያ ሙከራ ሊደረግባቸውና በዚህም አሜሪካን ቀውስ ውስጥ የመክተት ፍላጎት እንዳለ” በአገሪቱ ደኅንነቶች እንደተነገራቸው የትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ቡድን አስታውቋል። ይህ የግድያ ሙከራ ስጋት የቆየ ይሁን አዲስ በግልጽ አልተቀመጠም። የኢራን መንግሥት እስካሁን በጉዳዩ ላይ […]

ሞት ተፈርዶባቸው ከ50 ዓመታት በላይ በእስር ላይ የቆዩት ጃፓናዊ ነጻ ተባሉ

ከ 1 ሰአት በፊት ሞት ተፈርዶባቸው ከ50 ዓመታት በላይ በእስር ቤት የቆዩት የ88 ዓመቱ ጃፓናዊ አዛውንት ለተፈረደባቸው ወንጀል የቀረበባቸው ማስረጃ የተቀነባበረ ነው በሚል በነጻ እንዲለቀቁ ፍርድ ቤት ወሰነ። ኢዋኦ ሃካማዳ በአውሮፓውያኑ በ1968 አለቃቸውን፣ ሚስቱን እና ሁለት ልጆቹን ገድለዋል ተብለው በፍርድ ቤት ሞት ተፈርዶባቸው ከአምስት አስርት ዓመታት በላይ እስር ቤት ቆይተዋል። ለግለሰቡ ነጻ መውጣት እንደምክንያት የቀረበው […]

ባለፉት 3 ወራት በግጭት ውስጥ ባሉ አካባቢዎች ከ200 በላይ ሲቪሎች ተገድለዋል – ኢሰመኮ

ከ 48 ደቂቃዎች በፊት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በግጭት አውድ ውስጥ በሚገኙ አካባቢዎች ባለፉት ሦስት ወራት ውስጥ ብቻ ከ200 በላይ ሲቪል ሰዎች መገደላቸውን ይፋ አደረገ። ኮሚሽኑ አሃዙን ይፋ ያደረገው ረቡዕ መስከረም 15/2017 ዓ.ም. ይፋ ባደረገው በግጭት ዐውድ ውስጥ ያሉ አካባቢዎች የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ የሩብ ዓመት ሪፖርት ነው። የኢሰመኮ ሪፖርት ካለፈው ዓመት ሰኔ ወር እስከ […]

በወላይታ ዞን በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የሁለት ሕጻናትን ጨምሮ የ28 ሰዎች ሕይወት አለፈ

ከ 49 ደቂቃዎች በፊት ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን ተነስቶ ወደ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ዳውሮ ዞን ሲጓዝ በነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ አደጋ የሁለት ሕጻናትን ጨምሮ 28 ሰዎች ሕይወታቸው አለፈ። የመኪናውን አሽከርካሪ ጨምሮ 19 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸው በህክምና ላይ መሆናቸውን የወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ ገልጿል። ትናንት ረቡዕ መስከረም 16/2016 ዓ.ም. ከሶዶ ከተማ የተነሳው […]

አሜሪካ እና አጋሮቿ በሊባኖስ እና በእስራኤል ድንበር ላይ ለ21 ቀናት የሚቆይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥሪ አቀረቡ

ከ 4 ሰአት በፊት በእስራኤል እና በሄዝቦላህ መካከል ያለው ጦርነት መባባሱን ተከትሎ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና የአውሮፓ ህብረት እና ሌሎች አጋሮቻቸው በሊባኖስ ጊዜያዊ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥሪ አቀረቡ። 12 አገራት “ለዲፕሎማሲያዊ መፍትሔ ዕድል ለመስጠት” እና በጋዛ የተኩስ አቁም ለማድረግ እንዲያስችል ለ21 ቀናት አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ሃሳብ አቅርቧል። አገራቱ በጋራ ባወጡት መግለጫ፣ ጦርነቱ የእስራኤልንም […]