በኒው ዮርክ ሁለት ልጆችን ጨምሮ አራት ግለሰቦች በስለት ተወግተው ተገደሉ

ከ 5 ሰአት በፊት በኒውዮርክ ኩዊንስ በተባለ ቦታ በደረሰ የስለት ጥቃት ሁለት ህጻናትን ጨምሮ አራት ሰዎች ሲገደሉ ሦስት ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል። እሑድ ጠዋት ሮክዌይ ከሚባል ሰፈር የስልክ ጥሪ የደረሰው ፖሊስ ተጎጂዎቹን በእሳት በተያያዘ ቤት ውስጥ ቤት ውስጥ አግኝቷቸዋል። ተጠርጣሪው ግለሰብ ሁለት ፖሊሶች ላይ ጉዳት ቢያደርስም፣ ጉዳት ከደረሰባቸው ፖሊሶች አንዱ ተኩሶ አቁስሎታል። ተጠርጣሪው ወደ ሆስፒታል ቢወሰድም፣ […]

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

እኔ የምለዉ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ አንባቢ ቀን: December 3, 2023 በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ ኅዳር 21 ቀን 2016 ዓ.ም. በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ያጡ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን እንዘክራለን:: በዚህ አጋጣሚ በአፅኖት ማስታወስ ያለብን ባለፉት ሃያ ዓመታት በጋራ ባደረግነው ከፍተኛ ጥረት ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ውጤት […]

ሰሊጥ ላኪዎች የሽያጭ ውል ማረጋገጫ ሳይዙ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲገበያዩ ተፈቀደ

በሔለን ተስፋዬ December 3, 2023 ካለፈው ዓመት ታኅሳስ 9 ቀን 2015 ዓም. ጀምሮ ለሰሊጥ ላኪዎች የኤክስፖርት  የሽያጭ ውል ማረጋገጫ የማግኘት ግዴታ የነበረው አሠራር ላልተወሰነ ጊዜ መቆሙን፣ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ምርት ገበያ አስታወቁ፡፡ ለዚህ አሠራር መነሻ የሆነው በወቅቱ የምርት እጥረት ስለነበረ፣ ላኪዎች ያገኙትን ሰሊጥ ከሸጡ በኋላ ሌላ ምርት ለማግኘት በመቸገራቸውና አንዳንዶች ምርት በማከማቸት እጥረት […]

የሙስናን አስከፊነት ከማነብነብ ለተግባራዊ ፍልሚያ መነሳት ይቅደም

አስተያየት Byአንባቢ December 3, 2023 በምንትዋብ ሰርፀ ስለሙስናም ሆነ የመልካም አስተዳደር ዕጦት ወይም ፀረ ዴሞክራሲያዊነት መነጋገር ጤናማነት ነው፡፡ ለአገር ግንባታም ወሳኝ ከመሆኑ ባሻገር ስለልማትና ሰላም ከመወያየትም በላይ ነው፡፡ ለምን እንደሆነ ባይገባኝም የመንግሥት የትኩረት ከፍታ ነጥብ ግን አልሆነም፡፡ በአንድ ወቅት በዚሁ ጋዜጣ ላይ አንድ ጸሐፊ ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ አስተዳደር የሙስና ገጽታዎች ላይ ያነሷቸውን አንዳንድ የመወያያ […]

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

December 3, 2023 በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ ዱቄት ሆኗል” ሲባል፣ “የለም አፈር ልሼ ተነሳሁ” ብሎ እንደ አዲስ ተደራጅቶ መቀሌን በእጁ ያስገባው የትግራይ መከላከያ ኃይል (ቲዲኤፍ) ጦር ተፈጽሞብኛል ባለው ግድያ፣ ጥቃትና ዝርፊያ ሳቢያ “ሒሳብ ለማወራረድ” አጎራባች ክልሎችን ጥሶ ለመግባት ፋታ አልፈጀበትም። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የቲዲኤፍን ሱናሚ ሊያመክነውም ሆነ ሊገዳደረው እንደማይችል እርግጠኛ የነበሩት የትግራይ ኃይሎችና ደጋፊዎቻቸው ብቻ አልነበሩም። አጥብቀው የሚኮንኗቸው ተንታኞችም […]

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

ተሟገት ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች አንባቢ ቀን: December 3, 2023 በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ ኅብረተሰብ ባሉ የቀጥታና የተዘዋዋሪ አስተዋፅኦዎች ይወሰናል፡፡ በአስተናነፃችን ውስጥ እያንዳንዳችን ዕንቢ እሺ የምንለው፣ ወደንና ደስ ብሎን የምናደርገውና የምንታገለውም ነገር ይኖራልንና በሰብዕና ግንባታችን ውስጥ የእያንዳንዳችን ንቁ ተሳትፎ ድርሻ አለው፡፡ በዕድሜና በዕውቀት እያደግን […]

ዓለም አቀፍ ትኩረት የተሰጠው የምርመራ ጋዜጠኝነት

PreviousNext PreviousNext 19ኛው የአፍሪካ የምርመራ ጋዜጠኛነት ጉባዔ ላይ የመጀመርያውን ሽልማት ያሸነፈው ኬንያዊው ጋዜጠኛ ቶም ኦዱላ ማኅበራዊዓለም አቀፍ ትኩረት የተሰጠው የምርመራ ጋዜጠኝነት ዓለም አቀፍ ትኩረት የተሰጠው የምርመራ ጋዜጠኝነት ታምሩ ጽጌ ቀን: December 3, 2023   Share የምርመራ ጋዜጠኝነት/ዘገባ ከሌሎች የዘገባ ዓይነቶች ይለያል፡፡ ከዜጎች ወይም ማንኛውም መረጃው እንዲነገርና እንዲተላለፍ ከሚፈልግ አካል የሚለቀቅ ወይም በፍጥነት ተሠርቶ የሚሠራጭ ‹‹Leak […]

ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ለተጠራቀመበት ዕዳ ፖለቲካዊ መፍትሔ እንዲሰጥ ተጠየቀ

ዜና ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ለተጠራቀመበት ዕዳ ፖለቲካዊ መፍትሔ እንዲሰጥ ተጠየቀ ሲሳይ ሳህሉ ቀን: December 3, 2023 የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የተጠራቀመበት ዕዳ በአፋጣኝ ፖለቲካዊ መፍትሔ ካላገኘ፣ በመጪዎቹ አምስት ዓመታት የዕዳ መጠኑ ወደ 250 ቢሊዮን ብር እንደሚያሻቅብ፣ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ቋሚ ኮሚቴ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሪፖርት አቀረበ፡፡ በቢሊዮን ዶላሮች የሚቆጠር ዕዳ አለበት የተባለው ኮርፖሬሽኑ፣ በአሁኑ ጊዜ […]

ለማዳበሪያ ግዥ 930 ሚሊዮን ዶላር መፈቀዱን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ

በሰላማዊት መንገሻ December 3, 2023 የግብርና ሚኒስቴር የኢንቨስትመንትና የግብይት ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ ሶፊያ ካሳ (ዶ/ር) ለ2016/17 ዓ.ም. የምርት ዘመን የማዳበሪያ ግዥ 930 ሚሊዮን ዶላር መፈቀዱን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ለማዳበሪያ ግዥ የተፈቀደው 930 ሚሊዮን ዶላር (71.4 ቢሊዮን ብር) በመሆኑ በዕቅድ ከተያዘው 23.3 ሚሊዮን ኩንታል ውስጥ 19.4 ሚሊዮን ኩንታል ብቻ የመግዛት አቅም ያለው መሆኑን፣ የግብርና ሚኒስቴር የኢንቨስትመንትና […]