ምዕራብ ጎጃም ለሁለት ተከፈለ
May 23, 2023 – Konjit Sitotaw ቀደም ሲል የምዕራብ ጎጃም ዞን በ14 የገጠር ወረዳዎችና በስምንት የከተማ አስተዳደሮች ተዋቅሮ ማዕከሉን ፍኖተ ሰላም አድርጎ ሲተዳደር ነበር። ሆኖም አንዳንድ ወረዳዎች ከማዕከሉ የራቁ በመሆናቸው አስተዳደራዊ ሥራዎችን ለማከናወን ነዋሪዎቹ ተቸግረው እንደቆዩና «ዞን ይከፈልልን» ጥያቄያቸውን በተደጋጋሚ ሲያቀርቡ እንደ ነበር ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል። ሆኖም ከብዙ ጊዜ በኋላ ጥያቄው ቢመለስም ማዕከሉ ባሕር ዳር መሆኑ ተገቢ […]
በኮሌራ መስፋፋት የተቆጡ የደቡብ አፍሪካዋ ከተማ ነዋሪዎች ከንቲባቸውን አሳደዱ
May 23, 2023 – BBC Amharic ከ 4 ሰአት በፊት በኮሌራ መስፋፋት እጅግ የተቆጡ ደቡብ አፍሪካውያን ሰኞ ዕለት ከንቲባቸውን መንገድ ለመንገድ ሲያሳድዷቸው ታይተዋል። ነዋሪዎቹ፤ ከንቲባው ንፁህ ውሃ ማቅረብ ተስኗቸዋል ሲል ወቀሳቸውን ያሰማሉ። ከደቡብ አፍሪካ ግዛቶች በርካታ ሕዝብ ይኖርባታል በምትባለው ጋውቴንግ በኮሌራ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 15 ደርሷል። የሺዋኔ ከተማ ከንቲባ ሲሊዬርስ ብሪንክ ከብሔራዊው መንግሥት ከሚመጡ ባለሥልጣናት ጋር ለመምከር […]
ህወሓትን በድጋሚ ለማስመዝገብ ማመልከቻ እንደማይገባ የፓርቲው ሊቀመንበር አስታወቁ
May 23, 2023 – VOA Amharic ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ(ህ.ወ.ሓ.ት) ሊቀ መንበር ዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል፣ የድጋሚ ምዝገባ ለማድረግ፣ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማመልከቻ እንደማያስገባ አስታወቁ። “50 ዕድሜ ያለውን ሰው እንደ ዐዲስ አኹን ጀምር እንደማለት ነው” ያሉት ሊቀመንበሩ “ረዥም ዕድሜ ያለው ፓርቲ በሌላ መንገድ ራሱ ካልፈረሰ ይቀጥላል” ብለዋል።ፓርቲያቸውም ኾነ ጊዜያዊ አስተዳደሩ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሰጠውን የህጋዊነት […]
በትግራይ ያለው ሰብአዊ ቀውስ እጅግ አሠቃቂ ደረጃ ላይ መድረሱ ተገለጸ
May 23, 2023 – VOA Amharic የኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት፣ በትግራይ ክልል ያለው ሰብአዊ ቀውስ፣ እጅግ አሠቃቂ ደረጃ ላይ በመድረሱ፣ የሚመለከታቸውን አካላት ትኩረት እንደሚሻ አስታወቀ፡፡ ምክር ቤቱ በአወጣው መግለጫ፣ የአሜሪካ የዓለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ/USAID/ እና የዓለም ምግብ ፕሮግራም/WFP/ ለትግራይ ክልል ሲያቀርቡት የነበረውን ሰብአዊ ርዳታ በማቋረጣቸው፣ ተረጅዎች ጭንቀት ውስጥ መግባታቸውን ገልጿል፡፡ በትግራይ ያለው ሰብአዊ ቀውስ እጅግ […]
ከሱዳን በቀን እስከ 800 ፍልሰተኞች በመተማ በኩል ይገባሉ
May 23, 2023 የሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ ድጋፍ ሰጪ ኃይሎች፣ ካለፈው ወር ሚያዝያ ሰባት ቀን ጀምሮ፣ በካርቱም እና በሌሎች አካባቢዎች በሚያካሒዱት ግጭት ምክንያት፣ 25ነጥብ7 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች፣ አስቸኳይ ሰብአዊ ርዳታ ፈላጊዎች ኾነዋል። ዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት(IOM)፣ ረቡዕ ዕለት ያወጣው መረጃ እንደሚያሳየው፣ በመላው ሱዳን ቢያንስ 843ሺሕ130 ሰዎች ሲፈናቀሉ፣ ወደ 259ሺሕ የሚደርሱ ሰዎች ደግሞ ወደ ጎረቤት […]
በጋዜጠኛና የታሪክ ምሁሩ አቶ ታዲዎስ ታንቱ የክስ ሂደት ላይ ሲካሄድ የነበረው ምስክር የመስማት ሂደት ተቋረጠ
May 23, 2023 በጋዜጠኛና የታሪክ ምሁሩ አቶ ታዲዎስ ታንቱ የክስ ሂደት ላይ ሲካሄድ የነበረው ምስክር የመስማት ሂደት ተቋረጠ! ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ጀነራል አበባው ታደሰ ፍርድ ቤት አንቀርብሞ ብለዋል በዛሬው ችሎት አቃቤ ህግ “የሰነድ ማስረጃዎች ከቀረበው ክስ ጋር ግንኙነት የላቸውም እንዲሁም እንዲመሰክሩ የተጠሩት ምስክሮች ተከላከሉ ከተባሉበት አግባብ አንፃር ትክክለኛና ቀጥተኛ የሆኑ ስላልሆኑ ሊሰሙ አይገባም” ሲል በፅሁፍ […]
ግብፅ አረብ ሊግን በመጠቀም ጫና ለማሳደር እየሞከረች ነው ስትል ኢትዮጵያ ወቀሰች
May 23, 2023 – BBC Amharic ከ 5 ሰአት በፊት ግብፅ የአረብ አገራት ሊግን በመጠቀም በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማሳደር የምታደርገው ጥረት በአባይ ወንዝ አጠቃቀም ላይ የተገባውን የመርሆዎች ስምምነትን የጣሰ ነው ስትል ኢትዮጵያ ወቀሰች። የግብፅንም አካሄድ “ቀናነት የጎደለው’ ሲልም የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰኞ ግንቦት 14/ 2015 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ ተችቷል። የአረብ ሊግ አገራት ምክር ቤት ባለፈው ሳምንት […]
መንግሥት ገለልተኛ ተቋማትን በገዢው ፓርቲ አባሎች ጠፍሮ በመያዝ ሚናቸውን እንዳይወጡ እና በሕግ አግባብ እንዳይሠሩ ማድረጉን ቀጥሏል!
May 23, 2023 መንግሥት ገለልተኛ ተቋማትን በገዢው ፓርቲ አባሎች ጠፍሮ በመያዝ ሚናቸውን እንዳይወጡ እና በሕግ አግባብ እንዳይሠሩ ማድረጉን ቀጥሏል! የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ከግጭት አዙሪት እንድንወጣ እና የሀሳብ የበላይነት አሸናፊ ሆኖ እንዲወጣ የመገናኛ ብዙኀን ያላቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑን በጽኑ ያምናል። መገናኛ ብዙኀኑ ሙስናና ብልሹ አሰራርን በማጋለጥ፣ ዜጎች በመረጃ የበለፀጉ እንዲሆኑ በማድረግ በሥልጣን መባለግ እንዳይኖር […]
“ተለያይቶ ትዳርን” ምንድን ነው? ጥንዶች ስለምን ይህንን ይመርጣሉ?
May 23, 2023 – BBC Amharic በትዳር ውስጥ ሆነው ነገር ግን ተለያይተው መኖር የሚባል ነገር በምዕራቡ ዓለም እየተስፋፋ ነው። ለዚህ ምርጫቸው ደግሞ ጥንዶቹ ብዙ ምክንያቶችን ያቀርባሉ። አንደኛው ምክንያት ‘ትዳርንም ላጤነትንም አንድ ላይ ለማስኬድ’ ነው ይላሉ። በሌላ በኩል የበለጠ ነጻነት ይሰጣልም የሚሉ አሉ። ጃፓን ውስጥ እንዲህ አይነቱ ሃሳብ በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት እያገኘ ነው። ለመሆኑ በእንዲህ አይነት የትዳር ዘይቤ […]
የሰላም ስምምነቱ ትግበራ ቅኝት በትግራይ
May 23, 2023 – DW Amharic የትግራይ ኃይሎችን ከ85 እስከ 90 በመቶ የሚሆን ትጥቅ የማስፈታት ሥራ መፈፀሙን በአፍሪካ ሕብረት የሰላም ስምምነቱ ተቆጣጣሪ ልዑክ ገለፀ። … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ