ባይደን የግብፁን አል ሲሲ የሜክሲኮ ፕሬዝዳንት ማለታቸው መነጋገሪያ ሆነ

ከ 35 ደቂቃዎች በፊት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የግብፁን ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ አል ሲሲን በስህተት የሜክሲኮ መሪ ብለው በመጥራታቸው በግብፃውያን ዘንድ መነጋገሪያ ሆኑ። ፕሬዝዳንት ባይደን ትናንት ሐሙስ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እስራኤል በጋዛ ላይ እያካሄደች ያለውን ዘመቻ በተመለከተ በተናገሩበት ጊዜ ነው አል ሲሲን የሜክሲኮ ፕሬዝዳንት ብለው የጠቀሷቸው። “እንደምታውቁት መጀመሪያ ላይ የሜክሲኮው ፕሬዝዳንት ሲሲ፣ ወደ ጋዛ […]

ቀይ ባሕርን ያወኩት ሁቲዎች ከባሕር በታች የተዘረጋ የኢንተርኔት መስመርን እንዳይቆርጡ ተሰግቷል

ከ 6 ሰአት በፊት በቀል ዓይነቱ ብዙ ነው። የየመን ሁቲዎች በአሜሪካ እየተመሩ የአየር ጥቃት የሚያደርሱባቸው ምዕራባውያንን ለመበቀል ወደኋላ እንደማይሉ አሳይተዋል። አሜሪካ እና አጋሮቿ ሁቲዎች ሚሳዔል እና ድሮን ለመተኮስ የሚጠቀሙባቸውን ጣቢያዎች ደብድበዋል። ሁቲዎች በጋዛ ያሉ ፍልስጤማውያንን ለመደገፍ ነው ብለው በቀይ ባሕር እና በኤደን ባሕረ ሰላጤ የሚመላለሱ መርከቦችን ዒላማ አድርገዋል። አሁን ሁኔታዎች ተጋግለዋል። የተባበሩት መንግሥታት ዕውቅና የሚሰጠው […]

የእግር ኳስ ዳኞች ተጨዋቾችን ለ10 ደቂቃ ከሜዳ የሚያግዱበት ሰማያዊ ካርድ ሊሞከር ነው

ከ 2 ሰአት በፊት የእግር ኳስ ዳኞች ከተለመደው ቢጫና ቀይ ካርድ በተጨማሪ ሰማያዊ ካርድ መዝዘው ተጫዋቾችን ለ10 ደቂቃ ከሜዳ የሚያሰወጡበት የሙከራ አሰራር በዛሬው ዕለት ይፋ እንደሚደረግ ይጠበቃል። ይህ ሕግ በዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማህብር ቦርድ ሕግ አውጪዎች አማካኝነት የተዘጋጀ ነው። ሰማያዊ ካርድ በቅድሚያ ከዳኞች ጋር አለስፈላጊ ንትርክ ውስጥ የሚገቡ ተጨዋቾችን ለመቀጣት ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን ኳስን […]

ፕሬዝዳንት ባይደን ለቀረበባቸው ትችት “የማስታወስ ችሎታዬ ምንም አልሆነም” ሲሉ መለሱ

ከ 5 ሰአት በፊት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የማስታወስ ችሎታቸው ‘በጉልህ’ ቀንሷል መባሉን ተከትሎ በብስጭት “የማስታወስ ችሎታዬ ምንም አልሆነም” ሲሉ መለሱ። ባይደን ከዓመታት በፊት ምክትል ፕሬዝዳንት ሳሉ ከወታደራዊ እና የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ጋር የተያያዙ ምስጢራዊ ሠነዶች አያያዛቸውን በተመለከተ የወጣ የምርመራ ሪፖርት ላይ የ81 ዓመቱ ፕሬዝዳንት ቁልፍ የሚባሉ ቀናትን ዘንግተዋል ብሏል። የፍትሕ ቢሮ አማካሪ የሆኑት ሮበርት […]

ፕሬዝደንት ዜሌንስኪ የዩክሬን ጦር ዋና አዛዥን አባረሩ

ከ 5 ሰአት በፊት የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ የሀገራቸው ጦር ኃይል ዋና አዛዥ የሆኑትን ጄነራል ቫላሪ ዛሉዢኒ ከስልጣን ሽረዋል። ይህ የፕሬዝደንቱ ውሳኔ ከመሰማቱ አስቀድሞ በዜሌንስኪ እና በጄኔራል ዛሉዢኒ መካከል የተካረረ ልዩነት ተፈጥሯል የሚሉ ‘ወሬዎች’ ሲናፈሱ ነበር። በውጊያ ሜዳ የካበተ ልምድ እንዳላቸው የተነገረላቸው ጄነራል ኦሌክሳንደር ሲሪሲክ የተባበረሩትን ጄነራል መተካታቸው በፕሬዝደንታዊ አዋጅ ይፋ ሆኗል። በ2014 ዓ.ም የካቲት […]

ሱዳናውያን ስደተኞችን ያሳፈረች ጀልባ ሰጥማ ቢያንስ አስራ ሦስት ሰዎች ሞቱ

ከ 5 ሰአት በፊት ሱዳናውያን ስደተኞችን ያሳፈረች ጀልባ በቱኒዚያ ባህር ዳርቻ ሰጥማ ቢያንስ 13ቱ ሲሞቱ ሌሎች 27 ሰዎች መጥፋታቸውን የቱኒዚያ ባለሥልጣን ተናገሩ። በጀልባዋ ላይ ተሳፍረው ከነበሩት ከ40 በላይ ስደተኞች በሕይወት የተገኙት ሁለት ሰዎች ብቻ ሲሆኑ የጠፉት እየተፈለጉ መሆኑን ባለሥልጣኑ ገልጸዋል። አደጋው የደረሰው ጀልባዋ ከስፋክስ ከተማ አቅራቢያ ከምትገኝ ጀቢኒያና ከተባለች አነስተኛ መንደር ተነስታ እየተጓዘች ሳለ ነበር። […]

በመፈንቅለ-መንግሥት የተጠረጠሩት የቀድሞው የብራዚል ፕሬዝዳንት ቦልሶናሮ ፓስፖርታቸውን አስረከቡ

ከ 5 ሰአት በፊት ምርመራ የተከፈተባቸው የቀድሞው የብራዚል ፕሬዝዳንት ጃይር ቦልሶናሮ ፓስፖርታቸውን አስረከቡ። ባለፈው የአውሮፓውያኑ ዓመት ደጋፊዎቻቸው የብራዚልን ኮንግረስን ዘልቀው ገብተው አመፅ ከፈጠሩ በኋላ ነው ቦልሶናሮ ምርመራ የተከፈተባቸው። ቦልሶናሮ በምርጫ በሉዊዝ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሳልቪ ከተሸነፉ በኋላ በግድ ሥልጣን ላይ ለመቆየት አቅደዋል ሲል ፖሊስ ይከሳቸዋል። ቦልሶናሮ ይህ ፖለቲካዊ እርምጃ ነው እንጂ እኔ ይህን አላደርግኩም ሲሉ […]

Ethiopian Satellite Network Television (Esan TV) launched – Borkena 

borkena Former Ethiopian Satellite Television (ESAT) journalists on Wednesday announced that they are working together again under the Ethiopian Satellite Network Television (ESAN TV) brand.  Journalists who worked for ESAT have been running their news channel on YouTube after they left ESAT following a dispute.  Messay Mekonnen (Anchor Media), Dereje Habtewold (Dere News), Tamagne Beyene […]

Egypt slams recent statements from Ethiopian Prime Minister on Renaissance Dam  – Egypt Independent 

 Egypt Independent February 8, 2024 Egyptian Foreign Ministry Spokesperson Ahmed Abu Zeid commented on statements made by Ethiopian Prime Minister Abiy Ahmed before the parliament regarding the negotiations on the Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD). Abiy Ahmed confirmed Ethiopia’s readiness to negotiate on the GERD during the inquiries of the House of People’s Representatives in its […]