የትግራይ ክልል መስተዳድር የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በድሎናል ሲል አነጋጋሪ ደብዳቤ ጻፈ

June 14, 2018 /ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- የትግራይ ክልል መስተዳድር በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን (ETV) ላይ የቅሬታ ደብዳቤ ፃፈ። የክልሉ  መንግስት ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ወይም ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢብኮ) ዛሬ በፃፈው የቅሬታ ደብዳቤ ላይ የቴሌቪዥን ጣቢያው “የትግራይ ህዝብን አንድነት የሚጎዱና ማንነቱን የሚያጎድፉ ዘገባዎች እየሰራ በመሆኑ ከድርጊቱ  እንዲታቀብ ሲል ጠይቋል። በደብዳቤው ላይ ሦስት ዘገባዎች ለአብነት የተጠቀሱ ሲሆን፦ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር […]

የህወሓት መግለጫ እና አፀፋዉ

የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ማዕከላዊ ኮሚቴ የኢህአዴግ ሥራ አፈፃሚ ኮሚቴ ባሳለፋቸዉ ዉሳኔዎች ብዙ ስሕተትን ፈጽሞአል ሲል መግለጫ ማዉጣቱን አሳሳቢ ሲሉ የፖለቲካ አቀንቃኞች ተቃወሙት። «ህወሓት እየታየ ያለዉን ለዉጥ እንደማይቀበለዉ ያሳወቀበት ነዉ»   የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ማዕከላዊ ኮሚቴ የኢህአዴግ ሥራ አፈፃሚ ኮሚቴ ባሳለፋቸዉ ዉሳኔዎች ብዙ ስሕተትን ፈጽሞአል ሲል መግለጫ ማዉጣቱን አሳሳቢ ሲሉ የፖለቲካ አቀንቃኞች […]

አገሪቷ ወደ ብረት ትግል መግባትዋ አይቀሬ ነው ስላችሁ አላመናችሁኝም ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)

  WEDNESDAY, JUNE 13, 2018 እንዲህ ብየ ስል ብዙ ወዳጆቼ አላመኑኝም። ወደ ብረት መግባትዋ አይቀሬ ነው ብቻ ሳይሆን ላንድ የቅርብ ወዳጄ ያወያየሁት ‘ለምስኪኑ አብይ እጅግ እሰጋለታለሁ” ነበር ያልኩት።እንደ ቁም ነገር አልወሰደውም። እኔ ግን  በጣም ነው ያሳሰበኝ። እኔ እና አብይ የለያየን የአማራ መፈናቀል ያለማቀሙ በሚመለከት እንደሆነ ደጋግሜ ተናግሬአለሁ። ችግሬ ያ ብቻ ነው። አብይ ገጽታው ስመለከተው ኢትዮጵያዊነት የተላበሰ ሆኖ […]

ከመቀሌው ዱለታ በስተጀርባ ያሉ እውነታዎች – ክንፉ አሰፋ | በጽሁፍና በቪዲዮ የቀረበ

June 14, 2018 የህወሃት መግለጫ በመስመሮች መካከል ሲነበብ በተቀማ ጩኸት ሊመሰል ይችላል። ከመቀሌው ዱለታ በስተጀርባ የነበሩ እውነታዎችን ለመዳሰስ የፖለቲካ ሊቅ መሆንን አይጠይቅም። ህወሃቶች አብረው ወስነው ያስተላለፉትን ጉዳይ እንደመጋዣ አኝከው ሲያበቁ፤ ከብዙ ገጽ የክስ ቻርጅ ጋር ብቅ ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩን ለማስጠቆር የሄዱበት ርቀት ግልጽ እና መሳጭ ነው። ሰማይ ወጥተው ቁልቁል ቢወርዱም ግን ከቶውንም የህዝብ ቀልብ ሊስቡ […]

“አንዳርጋቸው ይለቀቅ አለበለዚያ ሥልጣኔን እለቃለሁ”

14 ጁን 2018 BBC HARDTALK ማክሰኞ ግንቦት 21 2010 ዓ.ም ከእስር የተፈቱት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ነፃ ከወጡ በኋላ በቤተሰቦቻቸው መኖሪያ ከተደረገላቸው ሞቅ ያለ አቀባበል ባሻገር ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተገናኝተው ከአንድ ሰዓት ተኩል በላይ መወያየታቸውን ለቢቢሲ ሃርድ ቶክ ተናግረዋል። አቶ አንዳርጋቸው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ስላደረጉት ውይይት ለየትኛውም የሀገር ውስጥና የውጭ መገናኛ […]

የደቡብ ክልል የፌዴራል መዋቅር፡ የህወሃት ቁማርና ቀመር (መንግስቱ አሰፋ)

June 14, 2018 በኢትዮጲያ የፌዴራል ስርአት ትልቁ አጨቃጫቂ ጉዳይ የደቡብ ብ/ብ/ህ/ክልል ጉዳይ ነው፡፡ የደ/ብ/ብ/ህ ክልል ከአጠቃላይ በሀገሪቱ ከሚገኙ 80 በላይ ብሔረሰቦች ከ70 ፐርሰንት በላይ የሚሆኑ ብሔረሰቦችን የያዘ ክልል ነው፡፡ የክልሉን አወቃቀር በተመለከተ ኢህአዴግ ላለፉት አመታት አጥጋቢ ምክንያት መስጠት አቅቶት በፕሮፖጋንዳ ብቻ የታጠረ መልስ ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ ዶ/ር መራራ ጉዲና ‘’Ethiopia competing ethnic nationalism and the quest […]

Why landlocked Ethiopia wants to launch a navy

June 14, 2018 By Dickens Olewe BBC News H H Commodore Prince Alexander Desta was Deputy Commander of the Imperial Ethiopian Navy in 1971 When Eritrea gained independence in 1993, Ethiopia suddenly found itself without a coastline and so it took the logical step of disbanding its navy. Now, it is reconsidering its decision and […]

ሽፈራው ሽጉጤ የጨምበላላ ቀን፤ “ዓመት ዓመቱ አያድርስህ” – የሲዳማ ሽማግሌዎች፤

14/06/2018 ሽፈራው ሽጉጤ የጨምበላላ ቀን፤ “ዓመት ዓመቱ አያድርስህ”የሲዳማ ሽማግሌዎች፤ ውብሸት ሞላ ሲዳማ ከነበሩት የደቡብ ክልል ርእሰ መስተዳደሮች መካከል ሲዳማዎች ወደዋቸው መንግሥት የጠላቸው አቶ አባተ ኪሾ ናቸው። በመንግሥት ተወድዶ በሲዳማዎች የተጠሉት ደግሞ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ናቸው። መቼም የሲዳማ ሕዝብ በጀግንነቱም በብልሃተኛነቱም የሚገርም ሕዝብ ነው። በአጼ ምኒልክ ዘመን “ራስ ተሰማ ናደው በደሉን” ብሎ ሽማግሌ ተመርጦ አዲስ አበባ […]

አገር ለድጋፍ ነቅሎ ቢወጣስ? (ደረጄ ደስታ)

14/06/2018 የወያኔ ሃርነት ትግራይን መግለጫ አነበብኩት። የተስፋ ብርሃን የፈነጠቀበት አገር ይህን ሲያይ ምን ይል ይሆን? ንድድ አለኝ። አደባባይ እማልጽፈውን ይህን ቁጣ በውስጤ አጉተመተምኩ። ደግሞ አሁን ምን ሆን ልትሉ ነው? ኢትዮጵያ እሚለው ስም ደጋግሞ መጠራት አንገሸገሻችሁ? የእስረኞች መፈታት እናንተን መልሶ አሰራችሁ? የሰላም የእርቅና የይቅርታ ጥሪው የጦርነት ነጋሪት መስሎ ታያችሁ? እናንተ ተዋግታችሁ ተሰውታችሁ ያስገነጠላችሁትን ህዝብ ሌላው በፍቅር […]