ከዲያስፖራው ጋር የሚደረገው ውይይት ትርጉም እና ፋይዳ ይኖረው ዘንድ በእውነተኛ የለውጥ እርምጃዎች የታጀበ ይሁን!!

ጁን 1 ቀን 2018 ዓ.ም. ከዲያስፖራው ጋር የሚደረገው ውይይት ትርጉም እና ፋይዳ ይኖረው ዘንድ በእውነተኛ የለውጥ እርምጃዎች የታጀበ ይሁን!! ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድ በመጭው ነሀሴ ወር 2010 ዓ.ም. ወደ አሜሪካን አገር እንደሚመጡ እና ከዲያስፖራው ማህበረሰብ ጋር የመወያዬት እቅድ እንዳላቸው በስፋት እየተነገረ ይገኛል። በአገር ውስጥም ይሁን በውጭ አገር ያሉ ኢትዮጵያዊያንን ማወያዬት የሚደገፍ ሀሳብ ቢሆንም፣ የሚደረጉት […]

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ ወሰነ   

02/06/2018   ፋና ብሮድካስቲንግ አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ዛሬ መደበኛ ስብሰባውን ያደረገው የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ ወሰነ። ምክር ቤቱ በስብሰባው የሀገሪቱን የፀጥታ ሁኔታ ገምግሟል። አሁን ላይም በሀገሪቱ ስርዓት ሰፍኖ ሰላምና መረጋጋት በመመለሱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ መወሰኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍፁም አረጋ አስታውቀዋል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ […]

ህውሃት የቆመችበት ምድር እየራደባት ነው !!! (ቬሮኒካ መላኩ)

02/06/2018 ህውሃቶችን ለዚህ ያበቃቸው የእነሱ ሴራ የመጠንሰስ አቅማቸውና ፍጥነታቸው እንደ ኤሊ ቀርፋፋ በመሆኑና የአቢይ አህመድ የተግባራዊ እርምጃ  ፍጥነት ደሞ  እንደ አለም ሻምፒዮኑ የመቶ ሜትር ሯጭ ሁሴይን ቦልት የፈጠነና የሚወረወር በመሆኑ ነው። ለዚህ የአቢይ አህመድ ፈጣንና ፍርሃት አልባ ርምጃ  የሲአይኤና የ MI6  የመረጃ ግብአት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደረገለት ይመስላል።  ህውሃቶች ተሰብስበው ሴራቸውን ጨርሰው ለመተግበር ፊሽካ ከመንፋታቸው በፊት […]

ጀነራሎቹ እና የህወሀት ወታደራዊ ሳይንስ (የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰራዊት)

02/06/2018   በ1990/1991 ሁለተኛው የጭንቀት ጊዜ መጣ። ሻዕቢያ ባድመንና ሽራሮን ወረረ ተባለ። አዲሱ የኢፌዴሪ መከላከያ ሀይል ወራሪውን ከተያዙት ቦታዎች መነቅነቅ ተሳነው። በባድመ ግንባር የተደረገው ውጊያ በድል ቢጠናቀቅም በዚህ ግንባርና በጾረና ግንባር ብቻ ህወሓቶች ለ17 ዓመታት የትጥቅ ትግል ሲያደርጉ ካጡት ሰው ጋር የሚስተካከል ሰራዊት አለቀ። ያለአቅማቸውና ያለአንዳች ወታደራዊ ሳይንስ“ጄኔራል”፣ “ኮሎኔል”፣“ሻለቃ” እየተባሉ የተሾሙት የቀድሞ ነፃ አውጪዎች ኮንቬንሽናል አርሚ መርተው ማዋጋት […]

በአሜሪካን የሚገኝ የትግራይ ተወላጆች ማህበር መንግስት ለኢሳት ቴሌቪዢን ምህረት ማድረጉን ተቃወመ!

02/06/2018 መቀመጫውን በሰሜን አሜሪካ ያደረገና የትግራይ ተወላጆች ማህበር የተሰኘ አንድ ድርጂት ኢሳት ቴሌቪዢን ላይ ተመስርቶ የነበረው የሽብርተኝነት ክስ መነሳቱ እንዳሳዘነው በመግለጽ ለጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ደብዳቤ ጽፏል። ማህበሩ በዚሁ ደብዳቤው ላይ እንዳሰፈረው መንግስት ኢሳት ቴሌቪዥን ወደ ሀገር ገብቶ መስራት እንዲችል ጥሪ ማቅረቡ አግባብ አይደለም ብሏል። ከሁለት አመታት በፊት ኢሳት ባሰራጨው አንድ ዘገባ በትግራይ ህዝብ ላይ […]

አሁን ነው ትልቁ ፈተና!! ከስሜት ህክምና ወደ ተቋማት ህክምና!!! (ሀብታሙ አያሌው)

02/06/2018  ዶ/ር አብይ አህመድ የተረከቧት ሀገር ላለፉት 27 ዓመታት የስሜትና የተቋማት ቁስለት የደረሰባትን ሀገር ነው። በመሆኑም፣ ዘመኑ የጣለባቸው ኃላፊነት የስሜትና የተቋማት ህክምና በማድረግ ልትፈርስ የነበረችውን ሀገር ማዳን ነው። ይሄ ምን ማለት ነው? የኢህአዴግ ፖለቲካ ከሚገለፅባቸው ባህሪዎቹ ውስጥ ድብቅነት፣ ሴረኛነት፣ አደርባይነት፣ ስግብግብነት፣ ግለኝነት፣ ትዕቢተኛነትና ማን አህሎኝነት ዋና ዋናዎቹ ናቸው። በእነዚህ ባህሪዎቹ የተነሳ የኢህአዴግ ፖለቲካ ሰብዓዊነት የማይሰማውና […]

ተቃዋሚዎች እና ዘጠኙ ቂሎች (ወሰን ሰገድ ገ/ኪዳን)

02/06/2018 ዶ/ር አቢይ የጠቅላይ ሚኒስትርነት ስልጣን ከተቆናጠጡ ዛሬ (ግንቦት 24) ስድሳ ቀን ሞላቸው፡፡ እኛም የዶ/ር አቢይን እርምጃ አንዳንዴ በጥርጣሬ፣ አንዳንዴ በመገረም፣ አንዳንዳንዴም በመደነቅ እየተመለከትንና እያስተዋልን 60 ቀናት ያህል በዝምታ ቆየን፡፡ አሁን የተቃዋሚዎች ቅዋሜ ደርዝ የለሽ እየሆነ መሄዱን በታዘብን ጊዜ ዝምታችንን ሰብረን ብቅ አልን፡፡ . እዚህ ላይ ዶ/ር አቢይ ወደ ሥልጣን ከመጡ ወዲህ የከወኑትን ደግመን አንዘረዝርም፡፡ […]

አማራዎች ይፈናቀላሉ፣ ልሂቃኑ ይጠላለፋሉ፣ የህወሓትን ግብ ያሳካሉ! | ስዩም ተሾመ

June 2, 2018  ባለፉት ሦስት ሳምንታት ከተለያዩ የኦሮሚያ አከባቢዎች ስለተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች ጉዳይ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በስፋት እየተነገረ ይገኛል። ብዙ ተስፋ የተጣለበት አዲሱ የዶ/ር አብይ አመራር፣ በተለይ ደግሞ ወደ ባህር ዳር በመሄድ በኢትዮጲያዊነት መንፈስ የኦሮሞና አማራ ሕዝቦች አንድነትና አብሮነት መልሶ እንዲያሰራራ ያደረጉት ኦቦ ለማ መገርሳ በፕረዜዳንትነት በሚመሩት ክልል ውስጥ የአማራ ብሔር ተወላጆች መፈናቀላቸው ለብዙ የአማራ […]

የህዋሓት በአዴን መሪዎች ለውጡ አይዋጥላችሁምን? በቃሬዛ ላይ ሆናችሁ ዘልኣለማዊ አገዝዝ ልትገዙን ነው ?

June 2, 2018 አስገደ ገብረስላሴ የህወሓት በአዴን መሪዎች ጠ/ ምኒስቴር አብይ አህመድ አሊ የእናንተ አባታውያን መሪዎች አጥር ሰብሮ ጥሶ ከወጣ እኖሆ ከ60 ቀናት በላይ አሰቆጥሯል ። በነዚህ 60 ቀናት ውስጥ ከኢህአደግ አባታዎውያን aመሪዎች አስተሳሰብ ያፈነገጠ የሚመስል ከገመቱት በላይ እጅግ ቡዙ አመርቂ ስራዎች ሰርቷል ።እነዚህ አመርቂ ሰራዏች ግን ለህወሓት ኢህአደግ ነባር መሪዎች ፣የነሱ ጥገኞች ተከታዮች አክራሪ […]