በኮዬ ጨፌ የተገነቡ 23 ሺህ የጋራ መኖርያ ቤቶች ግምታቸውን ለወሰዱ “የልማት ተነሽዎች” ሊታደል ነው!!! (ዋዜማ ሬድዮ)

2019-10-07 በኮዬ ጨፌ የተገነቡ 23 ሺህ የጋራ መኖርያ ቤቶች ግምታቸውን ለወሰዱ “የልማት ተነሽዎች”ሊታደል ነው!!! ዋዜማ ሬድዮ *  አርሶ አደር ለነበሩት ተነሺዎች በጊዜው እስከ 500 ሺህ ብር በጥሬ ተሰጥቷቸዋል!!!* ምትክ ቦታም ለአባወራ 500 ካሬ ሜትር ለልጆቻቸው ደግሞ ለእያንዳንዳቸው 250 ካሬ ሜትር ተሰጥቷቸዋል!!!  በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት መርሀ ግብር ነዋሪዎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከተገነቡ 20/80 የጋራ […]

መንግስታዊ የዘር ማጥፋት አዋጅ !! (ሀብታሙ አያሌው)

2019-10-07 መንግስታዊ የዘር ማጥፋት አዋጅ !! ሀብታሙ አያሌው * የኔ ፕሬዝዳንት ልክ ናቸዉ! እሽሩሩዉ ይበቃናል!  – ታዬ ደንደ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ሊቀመንበርነት የሚመራው የኦዴፓ ፓርቲ ክፍተኛ  አመራር አቶ ታዬ ደንደአ በፅሑፋቸው ምንም በማያሻማ መንገድ የብሔረሰብ ስም ለይተው  በመግለፅ በአፄ ምኒልክ ዘመነ መንግስት ተፈፅሟል ለሚሉት አጀንዳቸው ሒሳብ ማወራረጃ ዛሬ የዘር-ማፅዳት የሚያስክትል ፅሑፍ በይፋ ለቅቀዋል። (በነገራችን ላይ በአፄ ምኒልክ […]

በኢሬቻ ቀን የተከሰተው ብሄራዊ አደጋ (አብርሃ በላይ)

2019-10-07 በኢሬቻ ቀን የተከሰተው ብሄራዊ አደጋ አብርሃ በላይ ዋሽንግተን ዲሲ ነው። ጊዜው ደግሞ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ጦርነት እንደተጀመረ። አሜሪካና ሩዋንዳ ጦርነቱን ለማቆም ይሯሯጣሉ። ታድያ አንድ ሬስቶራንት ውስጥ ከአንድ የሩዋንዳ ዲፕሎማት ጋር ስለተቀጣጠለው ጦርነት ወሬ ጀመርን። ወድያው ጦርነቱን ከአሜሪካ ጋር ሆነው ለማስቆም ከሚሯሯጡት አንዱ መሆኑን ገባን። አሜሪካና ሩዋንዳ ሻብያ ጠብ ጫሪ መሆኑን አውቀው፣ ስምምነቱ ለኢትዮጵያ በሚጠቅም […]

ሽመልስ አብዲሣ… ኢጆሌ “እንኳዕ ካባኹም ተፈጢርና!” (ይነጋል በላቸው)

2019-10-07 ሽመልስ አብዲሣ… ኢጆሌ “እንኳዕ ካባኹም ተፈጢርና!” ይነጋል በላቸው  እንኳን ለትዕይንተ ብዙው የመስከረም ወር – 2012ዓ.ም – አደረሳችሁ፡፡ መለስ ዜናዊ እንዳልሞተ ተዓምራዊ በሚመስል የነገሮች አካሄድና ምስስሎሽ እየተረዳን ነው፡፡ ብዙ ግልገል መለሶች ሀገር ምድሩን ሞልተውታል፡፡ መለሳዊ መምህራንም ከየዕድሜ ክልሉ በብዛት አሉ፡፡ ዶ/ር ገመቹ መገርሣ የተባለው ገልቱ አንዱና አንጋፋው ነው፡፡ እነሕዝቅኤል፣ ፀጋየ አራርሣ፣ ጃዋርና ሌሎች ጎልማሣና ታዳጊ […]

“…አግላይ ጠቅላይነት ወደፊትም ቢሆን መሰበሩ አይቀርም!!!” (አቶ ሙሼ ሰሙ)

2019-10-07 “…አግላይ ጠቅላይነት  ወደፊትም ቢሆን መሰበሩ አይቀርም!!! ’‘ አቶ ሙሼ ሰሙ* ” ነፍጠኝነት የመንደረተኝነት ታሪክ የለውም። ነፍጠኝነት ኦሮሞነት ነው፣ አማራነትም ነው፣ ትግራዮ፣ ሱማሌው፣ አፋሩ፣ ጉራጌው ወዘተ…ሳይቀር ሁሉም ኢትዮጵያዊ ነፍጠኛ ነው!!!  —- ነፍጠኛ የሚባል ስርዓትም ሆነ አገዛዝ አልነበረም፣ የለምም። ነፍጠኝነት ኢትዮጵያዊነትን ከኮሎንያሊዝም የታደገ የኢትዮጵያዊነት ከፍታ ነው። ነፍጠኞች በዱር፣ በገደል ከፋሽስት፣ ከወራሪና ከተስፋፊ ጋር ታግለው ሀገራቸውን የታደጉ […]

አብይ ይደምራል፤ ኦዴፓ ይቀንሳል፤ አንድ ወደፊት ሁለት ወደ ኋላ! (ያሬድ ሃይለማሪያም)

2019-10-06 አብይ ይደምራል፤ ኦዴፓ ይቀንሳል፤ አንድ ወደፊት ሁለት ወደ ኋላ! ያሬድ ሃይለማሪያም ዶ/ር አብይ “መደመር” በሚል እሳቤ ከመንግስት ጋር ሆድ እና ጀርባ ሆኖ የኖረውን የኢትዮጵያን ሕዝብ ቀልብ ለመሳብ እና ለውጡን ተስፋ አድርጎ በትእግስትና በጥንቃቄ እንዲከታተል ያደረጉትን ጥረት እና ድካም፤ ድርጅታቸው ኦዴፓ በአክራሪ ብሔርተኞች ተጠልፎ ይመስላል ልፋታቸውን በዜሮ እያበዛ ድምሩን ይንዳል። እሳቸው አዲስ አበባ የሁሉም ኢትዮጵያዊ […]

ሶደሬ–ዛሬና ትናንትና (ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም)

2019-10-06 ሶደሬ–ዛሬና ትናንትና ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም ከሶደሬ ጋር የተዋወቅሁት የዛሬ አርባ አምስት ዓመት ግድም ነው፤ አብሮ አደጌ ጌታቸው መድኅኔ የየረርና ከረዩ አውራጃ ገዢ ነበር፤ እሱ ቤት እያደርሁ ሶደሬ እሄድ ነበር፤ በዚያን ጊዜ ሶደሬ ባዶ ቦታ ነበር፤ የጠበል ሙቅ ውሀ መታጠቢያ ነበረ፤ ባለቤት አልነበረውም፤ የሕዝብ ነበር፤ በጭራሮ ታጥሮ ማንም ሰው ደሀ ሆነ ጌታ ያለምንም ክፍያ […]

ባለቤትህን የተመኘን ልጅህን ወይም እኅትህን ብትድርለት አይመለስም! (አቻምየለህ ታምሩ)

2019-10-05 ባለቤትህን የተመኘን ልጅህን ወይም እኅትህን ብትድርለት አይመለስም! አቻምየለህ ታምሩ አሁን እየሆነ ያለው ነገር ሁሉ አብዲ ኢሌ አንድ የሶማሌኛ አባባል በመጥቀስ የተናገረውን ያስታውሰኛል።  አብዲ የነገረን ሶማሌኛ አባባል «ባለቤትህን የተመኘን  ሰውን ልጅን ወይም እኅትህን ብትድርለት አይመለስም፤ ምክንያቱም እሱ የፈለገው ባለቤትህን ነው» የሚል ነበር። ኦነጋውያንም የሚፈልጉት ከተቀሩት ኢትዮጵያውያን ጋር በእኩልነት መኖር አይደለም። እነሱ ቢፈልጉ እንኳ የሚመጻደቁበት ወታደራዊው […]

የሽመልስ አብዲሳ ሙሉ ንግግር!!! (ትርጉም – ዶክተር አብርሃም አለሙ)

2019-10-05 የሽመልስ አብዲሳ ሙሉ ንግግር!!! ዶክተር  አብርሃም አለሙ በአሜሪካ ሀገር ነዋሪ እና የቋንቋ ተመራማሪ ሲሆኑ አማርኛ እና ኦሮምኛን አቀላጥፈው ይናገራሉ። የሽመልስ አብዲሳ የትላንትናው የኢሬቻ ሙሉ ንግግርን እንዲህ ተርጉመዉታል። “ይኸው ለዚህ በቃን የተከበርከው የኦሮሞ ሕዝብ፣ የተከበራችሁ የገዳ አባቶች፣ የሲቄ እናቶች ፣ ቄሮ እና ቀሬ ፣ የህዝባችን ጋሻዎች፣ እንኳን ድል አደረግን ፣ እንኳንም እዚህ ደረስን ፣ የተከበራችሁ ሚኒስቴሮች […]