አዲስ የፌደራሊዝም ችግኝ ማጽደቅ ያሻል! (ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ)

20/11/2017 • ልዩነትን ሲኮተኩት የኖረ ፌደራሊዝም፣ አንድነትንና ፍቅርን ሊያፈራ ያዳግተዋል    • የኮመጠጠውን የፖለቲካውን ዛፍ መግረዝ ወይም ነቅሎ መጣል ይገባል  የኢትዮጵያ ፌደራሊዝም ጉዞውን የጀመረው ከ80 በላይ ብሄረሰቦችን በ9 ክልል ከልሎ ነው። እዚህ ላይ ‹‹ክልል›› የሚለው ቃል በራሱ ችግር አለው፡፡ (የከሳቴ ብርሀን ተሰማ የአማርኛ መዝገበ ቃላት፣ ‹‹ከለለ›› የሚለውን ቃል፣‹‹ወሰንን፣ ድንበርን ለየ፤ አጥርን አጠረ፤ ጋረደ፤›› በማለት ይፈታዋል፡፡) […]

“በማያዳምጡ ተናጋሪዎች” እና “በማይናገሩ አድማጮች” መካከል መግባባት አይኖርም! (ስዩም ተሾመ)

20/11/2017 ሕወሃት/ኢህአዴግ መስራችና ከፍተኛ አመራር አቦይ ስብሃት ነጋ ከአዲስ ዘመን ጋር ያደረጉት ቃለ-ምልልስከተለመደው ወጣ ያለና በገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ ላይ ጠንከር ያለ ትችት የሰነዘሩበት ነው። አቦይ ስብሃት ከሁሉም ባለስልጣናት በተለየ ሃሳባቸውን በነፃነት ሲገልፁ በተደጋጋሚ ይስተዋላል። አሁንም የገዛ ፓርቲያቸውን ልክ-ልኩን ነገሩት እኮ! መቼም እንደሳቸው የተሰማውን በነፃነት መናገር የማይሻ ሰው ይኖራል ብዬ አላስብም። ይሁን እንጂ፣ አሁን ባለው ሁኔታ ልክ […]

አፋን ኦሮሞ የኢትዮጵያ የሥራ ቋንቋ የመሆን ግዴታነትና የእራሱ በሆነው በኢትዮጵያ ፊደል የመገልገል ተገቢነት

በአብርሃም ቀጀላ (ተሻሽሎ የቀረበ) ከጥንት ጀምሮ አስቀድሞ በሀገረ ኢትዮጵያ ላሉት የህዝብ ቋንቋዎች ሁሉ በምልአት፣ በጥራትና በብቃት ሲያገለግል የነበረው፤ በተለምዶ ግእዝ ፊደል ተብሎ የሚጠራው የሁሉም ኢትዮጵያውያን ፊደል እ.ኤ.አ በ1983 ዓ.ም በመንግስት መለዋወጥ ተፈጥሮ በነበረው ክፍተት ጥቂት ግለሰቦች በፖለቲካ ስሜታዊነትና ግልፍተኝነት ወደፊት በቀጣዩ ህዝቦች ላይ የሚያመጣውን ጣጣ፣ መዘዝ፣ ጉዳት እና ቀውስ ሳያጤኑ የቀድሞ ያለፈው ፓለቲካዊ ችግር በፈጠረው […]

የፍኖተ ዴሞክራሲ ራድዮ ፍካሬ ዜና: ወያኔ የእርስ በእርስ ግጭቶችን በመቆስቆስ ግጭቶችን እያራገበ መሆኑ ተጋለጠ * የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ቁጥር እየተመናመነ መሆኑ ተነገረ

November 20, 2017 የመቱ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የፍኖተ ዴሞክራሲ ራድዮ ፍካሬ ዜና ህዳር 10 ቀን 2010 ዓ.ም #ወያኔ የእርስ በእርስ ግጭቶችን በመቆስቆስ ግጭቶችን እያራገበ መሆኑ ተጋለጠ ▪ በሐረር የተከሰተው ግጭትን ተከትሎ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ወያኔ-ህወሀት ሆን ብሎ ውስጥ ውስጡን ባሰለጠናቸው ካድሬዎች ግጭት እያቀጣጠለ ሲሆን በሕዝቡ አርቆ አስተዋይነት እየከሸፉ መሆናቸው እየታየ ነው፡፡ በዚህ ባሳለፍነው ሳምንት በዝዋይ ኦሮሞዎችንና […]

ኢትዮጵያ በየካቲት 1966 ዓም እና በመስከረም 2010 ዓም መካከል ያለፈው ስህተት እንዳይደገም፤ ምን መደረግ አለበት ?

ከአያሌ ዘመናት የግፍ አገዛዝ በኋላ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለመጀመሪያ ጊዜ ገዥዎቹን፤ ያለ ማንም ርዳታ በገዛ እጁ ከሥልጣን ያወረደበት ዘመን 1966 ዓም ነው ። ይኽንን ድል የተቀዳጀው ከአፅናፍ እስከ አፅናፍ ሁሉም ዜጋ ተባብሮ በአንድ ላይ በመቆሙ ነበር ። ይኽ የጋራ ሀገራዊ ድል የተገኘው፤በጎሣ፤ በቋንቋ ፤ በሃይማኖትና በርዕዮት ሳይከፋፈል፤በአንድ ልሳን በመጮኽ፤ በአንድ ልብ በማመንና፤ አንድ ራዕይ በማየት መሆኑ […]

​አቶ ማሙሸት አማረ  ዐቃቤ ሕግ  ባቀረበባቸው  የሰነድ ማስረጃ ላይ ያቀረቡት ትችት

By ሳተናው November 20, 2017 06:56 “በደህንነት ሪፖርቱ ተዘጋጀ የተባለው፣ ተከሳሽ ሲጠቀምባቸው ነበሩ የተባሉ ሰባት የሚደርሱ ተንቀሳቃሽ ስልክ ቁጥሮች ተጠልፈዋል በሚል ነው፤ ነገር ግን እነዚህ በማስረጃነት ቀረቡ የተባሉት ስልክ ቁጥሮች በእርግጥም በተከሳሽ ስም ስለመመዝገባቸው ከኢትዩ-ቴሌኮም ጋር የተደረገ የደንበኝነት ውል ማስረጃ አልቀረበም፣ የማን እንደሆኑም አይታወቅም፣ ይበልጡኑ ደግሞ፣ የደህንነቱ ሪፖርቱ ከምክንያታዊ ጥርጣሬ የጸዳ ሆኖ ትክክለኛ ፍትህ መስጠት […]

የኦሮማራ ጥምረት የህወሃትን አፓርታይድ ለማስወገድ ነው! ( ስዩም ተሾመ )

November 20, 2017 07:28 ከህወሃት ባለስልጣናት እንደ አቦይ ስብሃት የሚገርመኝ ሰው የለም፡፡ ሰውዬው ፊት-ለፊት ስለሚናገሩ ግልፅነታቸው ይመቸኛል፡፡ ነገር ግን፣ በግልፅነታቸው ውስጥ ቅጥ-ያጣው የህወሃት ግብዝነት ስለሚንፀባረቅ ንግግራቸው ያበሳጨኛል፡፡ ለምሳሌ ትላንት በጎንደር በተካሄደው ስብሰባ ላይ “…ከኦሮሞ ጋር ለምን ግንኙነት መሰረታችሁ? አላማው ምን ነበር? ምንስ ታስቦ ነው? አሁንም ብታስረዱን…” ማለታቸው ተሰምቷል፡፡ ይህን ማለታቸው የእሮማራ ጥምረት ለህዋህቶች ምን ያህል […]

የጉናው ሰው!! አንዱዓለም አራጌ ማነው?

By ሳተናው November 20, 2017 08:10 የትውልድ አካባቢና የልጅነት ጊዜ አቶ አንዱዓለም አራጌ በጎንደር ክ/ሀገር በደብረታቦር አውራጃ በፋርጣ ወረዳ ጉና ተራራ ሥር ወይንም ግርጌ ክምር ድንጋይ ከተባለ ቦታ በ65 ዓ.ም ጥቅምት 25 ቀን ተወለደ፡፡ የኢትዮጵያ አብዮት ሊፈነዳ ሁለት ዓመት ሲቀረው በምጥ ዋዜማ ማለት ነው፡፡ “ሰው አካባቢውን ይመስላል” እንደሚባለው አንዱዓለም አራጌ በክ/ሀገሩ ከራስ ዳሽን ተራራ ቀጥሎ በሁለተኛ […]

 የምመኘው በአንድነታችን ተዋደንና ተከባብረን በኢትዮጵያዊነታችን እንድንኖር ነው-BBC

20 ኖቬምበር 2017 አጭር የምስል መግለጫዶር ፍቃዱ ከበደ በሥራ ገባታ ላይ ስሜ ፍቃዱ ከበደ ይባላል አሁን ወዳለሁባት ከተማ ከመምጣቴ በፊት ለ14 ዓመታት ያህል ተሰድጄ በመጣሁባት በፊንላንዷ ሄልሲንኪ ከተማ እኖር ነበር። በዩክሬን ክሪም በተሰኘው የሕክምና ተቋም የሕክምና ሳይንስ ብማርም የትምህርት ማስረጃዬ በፊንላንድ ሕጋዊ እንዲሆን ያደረኩትም ከብዙ ልፋትና ድካም በኋላ ነበር። ከዚያም ለልጆቻችን የተሻለ የትምህርትም ሆነ ማሕበራዊ […]