ከያሬድ ሀይለ ማሪያም ፌስ ቡክ የተወሰደ

Image may contain: 5 people, people standing and outdoor

በአማራ ክልል ከቅርብ ግዜ ወዲህ እየታየ ያለው ጽንፍ የያዘ ብሄረተኝነት ከብሶት አቀንቃኝነት ወደ ጥቃት ሰንዛሪነት መሸጋገሩ ሌላው የአደጋ ምልክት ነው። ዛሬ ጠዋት በደሴ ከተማ በ አቶ ብሩክ አበጋዝ እና #BrookAbegazMegassa እና ከታች በፎት የሚታየው ጓደኛው ላይ የተፈጸመው ድብደባ በጠባብ ብሔረተኝ ስሜት ናላቸው የዞረ የክሉ አክራሪ ቡድኖች የፈጸሙት መሆኑን አካባቢ ላይ ካሉ ሰዎች ለማረጋገጥ ችያለሁ። ይህ በአማራ ክልል እየታየ ያለው አደገኛ አዝማሚያ ከዚህ በፊትም በተለያዩ መልኩ ስገለጽ ተስተውሏል።

+ ከወራት በፊት በደሴ የተለየ የፖለቲካ አቋም ባራዱ ሰዎች ላይ ድብደባ ተፈጽሞ ማውገዛችን ይታወሳል፣
+ በደብረ ማርቆስ ከተማ አቶ በረከትን አድናለው ያለ መንጋ የግለሰብ ንብረት አውድሟል፣
+ አንዳንድ ከክልሉ ውጭ ያሉ የፖለቲካ ድርጅቶች በአንዳንድ የክልሉ ከተሞች ስብሰባ እንዳያደርጉ እና ጽ/ቤቶች እንዳይከፍቱም ዛቻ፣ ማስፈራሪያ እና ጥቃትም ተሰንዝሮባቸዋል፣
+ በጎንደር ዩንቨርሲቲ በተደረገ የውይይት መድረክ ላይ አቶ ብሩክ አበጋዝ እና አቶ Seyoum Teshome እንዳይገኙ መደረጉም ይታወሳል።

ይህ አይነቱ ሕግን የተላለፈ እና የሌሎች ዜጎችን የመደራጀት፣ ሃሳብን የመግለጽ እና በነጻነት የመንቀሳቀስ መብት የሚጥሱ ተግባራት በክልሉ ውስጥ እንዳዲስ እየተንሰራፋ በመጣው የአክራሪ ብሔረተኝነት ስሜት እና ጽንፈኞች አድራጎት ተደጋግሞ መታየቱ በክልሉ ውስጥ የሚታየውን አንጻራዊ ሰላም አደጋ ውስጥ ይጥለዋል።

የክልሉ መንግስትም ሆነ የፌደራል መንግስቱ እነዚህን በዜጎች ነጻነት እና መብት ላይ እገዳ የሚጥሉ እና ከዛም አልፈው አካላዊ ጥቃት የሚሰነዝሩ አክራሪ ብሔረተኞችን ለፍርድ ማቅረብ ይኖርበታል። ከዚህ የወንጀል አድራጎት ጀርባ ያለ የተደራጀ አካል ይሁን የፖለቲካ ፓርቲ ካለ በሕግ ሊጠየቅ ይገባል።

ብሔረተኝነት እንኳን አክርረነው በለስላሳውም ቢያዝ እንካ የግለሰቦችን መብት አደጋ ላይ የሚጥል አግላይ፣ ገዳቢ እና አጥፊ መንፈስ ነው።