Image may contain: 1 person, closeup

ሁሌ እናስታውሳቸው
ተቀብሮ እንዳይቀር
አኩሪ ታሪካቸው!!!!!

አስካለ ነጋ ማን ናት??

ማሳሰብያ፤…ስለ አስካለ ነጋ መጨረሻ የምታውቁ አንባቢዎቼ የበለጠ መረጃ ካላችሁ ብታካፍሉኝ ታሪኩን ሙሉ ያደርገዋል።

በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ለመጀመርያ ጊዜ በሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶች በኢሕአፓ ስር ተድራጅተው ከወንድ ጓዶቻቸው ጋር ጎን ለጎን በመቆም የደርግ ፋሺስታዊ ስርአትን ለመጣልና የስርአትን ለውጥ ለማምጣት ታግለዋል፤ እራሳቸውንም አሳልፈው ለትግሉ ሰጥተዋል። ከእነኝህ እንቁና ጀግና ወጣቶች አንዷ አስካለ ነጋ ናት።

አስካለ ነጋን የማወቅ እድል የገጠመኝ በ 1966 ዓ.ም ቀዳማዊ ኅ/ስላሴ በመባል ይታወቅ በነበረው ዩኒቨርሲቲ በአራት ኪሎ ካምፓስ የሳይንስ ፋኩሊቲ የመጀምርያ አመት መጀመርያ ሰሚስተር ተማሪ ሆኜ ነው። በብዙ ጓደኞቿ “አስኩ” በመባል የምታወቀው አስካለ ነጋ ያኔ ሁለተኛ አመትን ጨርሳ ወደ ሶስተኛ እየገባች ነበር። መኮንን ሙሉጌታ በቅፅል ስሙ (murderer) በመባል ይታወቅ የነበረው ጓደኛችን ጋር የቅርብ ግንኙነት ስለነበራትም በሱ ምክንያት እንገናኝ ነበር።

የወይዘሮ አበበች ወልደግዮርጊስና የአቶ ነጋ ቦንገር ልጅ በመሆን የምትታወቀው አስካለ ነጋ በጓደኞቿ በጣም የምትወደድ፤ተግባቢ በጣም ደግና እሩህሩህ እንደነበረች ብዙዎች ይናገራሉ። እኔም በትንሽ ጊዜ ትውውቃችን ምስክርነቴን መስጠት እችላለሁ።

በትምህርቷ በጣም ጎበዝ የነበረችው አስካለ ነጋ የመጀመርያ ደረጃ ትምህርቷን በአፄ ልብነድንግል የሁለተኛ ደርጃ ትምህርቷን ደግሞ በመዳህኒአለም ካጠናቀቀች በኋላ በከፍተኛ ወጤት አልፋና ከቀዳማዊ ኅ/ስላሴ እጅ የወርቅ ቀለበት ተቀብላ፤ ቀዳማዊ ኅ/ስላሴ ዩኒቨርሲቲ ገብታ ተከታትላለች።

አስካለ ነጋ በኢሕአፓነት ስትታገል ቆይታ በ 1970 መጨረሻ አካባቢ በአንጃዎች ጥቆማ ተይዛ ለእስር ስትዳረግ የድርጅቷን ሚስጥር ላለማውጣትና ጓዶቿን ለፋሺስት ደርግ አሳልፋ ላለመስጠት የ cyanide…መርዝ በመዋጥ እራሷን በማጥፋት በጀግንነት ተሰውታለች።

እስካሁን ድረስ ሃዘኑ ያሎጣላቸው እናቷ ለቅሶ በ ዘውዲቱ ወርቁ እንደተገጠመው፤…

የእኔዋ ብሩኬ
የእኔዋ ውብ ሸጋ፤….
ዘመኔን ጨረስኩት
ጠረንሽን ፍለጋ፤….
አንቺ ለሌሎቹ
በከፈልሽው ዋጋ፤….
ዘወትር ፀሎቴ
መሽቶ እስኪነጋ፤….
ምንግዜም አልረሳሽ
ልጄ አስካለ ነጋ!!

አስካለ ነጋ በአሁኑ ሰአት ከወያኔ ጋር እየተዋደቀ ላለው ወጣት ትውልድ አርአያና ምሳሌ ናት። በጣም እንኮራባታለን!!!!!

ነፍስ ይማር ለጀግኖቻችን!!!

የተለያዩ የህዝብ ልጆችና ሰማዕታት አጭር ታሪክ (BIO