f የትግራይ መልሶ ማቋቋም ድርጅት (EFFORT) የሃብቱ ባለቤት የትግራይ ህዝብ በመሆኑ ተጠሪነቱ ለትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት እንዲሆን ተወሰነ፡፡


March 25, 2019

Source: https://mereja.com/amharic/v2/103643

No photo description available.

የትግራይ መልሶ ማቋቋም ድርጅት (ትዕምት) የሃብቱ ባለቤት የትግራይ ህዝብ በመሆኑ ተጠሪነቱ ለትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት እንዲሆን ተወሰነ፡፡

የትግራይ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ ወይዘሮ ሊያ ካሳ በሰጡት መግለጫ የትግራይ መልሶ ማቋቋም ድርጅት የተቋቋመበት አላማ የትግራይ ህዝብ ማህበረ ኢኮኖሚውን በማሳደግ ህብረተሰቡ የሃብቱ ባለቤት በመሆን ተጠቃሚ እንዲሆን ነው።

በዚህ መሰረት ድርጅቱ ለማቋቋም በ1987 በወጣው ደንብ መሰረት የድርጅቱ የበላይ ባለቤት የትግራይ ህዝብ የሚል በመሆኑ ተጠሪነቱ ለትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት እንዲሆን ተወስኗል ብለዋል።
የህብረተሰቡን ተሳትፎ ለማሳደግ የክልሉ አፈ ጉባኤ የወረዳና መቐለ ልዩ ዞን እንዲሁም ከወጣቶች ሴቶች ከሲቪክ ማህበራት እና ምሁራን የምክር ቤቱ አባላት እንዲሆኑ ተወስኗል ብለዋል።
ትእምት መሰቦ ሲሚንቶ፣መስፍን ኢንዱስቱሪያል ኢንጂነሪንግ፣አልመዳ ጨርቃ ጨርቅና ሸባ ሌዘር ፋብሪካዎችና ሌሎችንም እንደሚያስተዳደር ይታወቃል፡፡