
በሃሣብ ተለያይተን ተሟግተናል አልፎም ተዋግተናል። ከእኔ ዘር ካልሆነ ጋብቻ ይፍረስ ግብይት ይቁም የሚል ትርክት የተሰማዉ ግን አሁን ነዉ። ዘራችንና ቋንቋችንን ካጨነገፈና ካበላሸ ህብረተሰብ እራሳችንን እንለይ የተባባልነበት አግባብ የሰማሁት ከነበቀለ ገርባ ነዉ። የተገነጠለችዉ ኤርትራ እንኳን ይኸንን ዓይነት ጫፍ የረገጠ የስብዕና ክሽፈት አላወጀችም ። ሰዋዊ የሆነ አይደለምና።
በቀለ ገርባ የተባለ ጽንፈኛ ገና ከጠዋቱ ፖሎቲከኛ አይደለሁም ብሎን ነበር። አልሰማነዉም እንጂ እዉነቱን ነዉ !። እርሱ ዘረኛ ብቻ ነዉ። የፖሎቲከኝነት ብቻ ሳይሆን የምሁርነት ስብእና ለማሳደግ እስከዛሬ አልቻለም»
እንደ ጃዋር መሃመድ አወዛጋቢ ለመሆንና ነገር ጥሎ ለመታወቅ ይፈልጋል። እኔ እንደተገነዘብኩት (ስህተት ሊሆን ይችላል)ጅዋር መወያየትም ማወዛገብም የሚችል መስማትም ማሰማትም የሚችል ማሴርም ከፈለገ ማስታረቅም የሚችል ሶሲዮ – ሴንንተሪዝም (sociocenterism) ላይ የተመሰረተ ስብእና አዳብሯል። እዉቅና የሚወድና ያንን ማድረግ የሚያስችለዉ ሁኔታ የፈጠረ አደገኛ ሰዉ ነዉ። ነገር ግን ችሎታዉን ለመልካም ነገር ሊያውለዉም ይችላል።
በቀለ ገርባ ግን ከምኑም የሌለ ነገር ግን በዘረኝነ ብቻ የታመመ ሰዉ ነዉ። ተናግሮ አልተናገርኩም መለያየትና የዘር ጥላች አዉጆ አላልኩም የሚል ሰዉ ነዉ። የሚናገረዉን የማያዉቅ ያወቀዉንም በቅጡ የማይተገብር የመታወቅ አባዜ ያለበት ህልመኛ ነዉ።
አሸባሪዎች ቤተመንግስት ሲጠሩ እኛ ለለዉጡ የታገልነዉ ተረሳን አለ። ከእስር ሲፈታ ዉጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን አክብረዉት የጀግና አቀባበል ሊያደርጉለት ተዘጋጅተዉ እያለ እኔን የሚቀበለኝ የእኔ የሆነ ዘዉግ ብቻ ነዉ ብሎ ፈቃደኛ ሳይሆን ቀረ።አዲስ አበባ የእኛ ናት የሚልም ማኒፌስቶም አነበበ።
ሰሞኑን ደግሞ የዘረኝነቱን የመጨረሻ እርከን አወጀ። ኦርጋኒክና(organic) አርተፊሻል(artificial) ኦሮሞ እንዳለ ነገረን። ከአማራ ከትግሬ ወይም ከወላይታ ወይም ከሌላ ዘር የተደባለቀ ኦሮሞ ሁሉ አርቴፊሻል ኦሮሞ ነዉ አለ። ቋንቋችን እንዳያድግ ያደረጉ ናቸዉና ጋብቻም ቢሆን ካሁን ወዲህ ኦሮሞ ከኦሮሞ ጋር ብቻ መሆን እንዳለበት በዘዴ ነገረን። ኦሮምኛ ከማይናገር እንዳንጎራበትና እንዳንገበያይ አወጀ።
ማንን እንዳስታወሰኝ ታውቃላችሁ!! የናዚ ፕሮፖጋንዳ ሃላፊ የነበረዉን ጆሴፍ ጎብልስን።
ጆሴፍ ጎብልስ በዘመኑ የሰበከዉ ልክ እንደበቀለ ገርባ ነበረ። እንሰሶች ከማይመሳሰሉ ዝርያዎች ጋር አይጋቡም አብረዉም አይኖሩም ፡፤ ከተዳቀሉና አብረዉ ከኖሩ ዘር ያበላሻሉ ቋንቋ ያኮላሻሉ ብሎ ነበረ የሰበክዉ።
የአይሁዳዋያን ጭፈጨፋ መሰረቱ ይኸ ነበረ። መዘዙ የስልሳ ሚልዮን ህዝብ ህይወት የቀጠፈዉን የሁለተኛ ዓለም ጦርነትንም አስከትሏል።
በቀለ ገርባም ቋንቋችንን አበላሽተዋል አጨንግፈዋል ስለዚህ ካሁን ወደያ ለቋንቋችን እድገት ስንል ከሌላዉ ዘር ጋር አንደባለቅ፤ አንጋባ፤ አንገበያይ እያለን ነዉ። ዛሬ ከዘራችሁ ዉጭ አትናገሩ አትጋገሩ ብሏል። ነገ ደግሞ የናንተ ያልሆነዉን እምቢ ካለ አንገቱን ቀንጥሱት የማይልበት ምነም ዋስትና የለም።
ልብ ያለዉ ልብ ይበል ጆር ያለዉም ይስማ !! ሂትለር በአገራችን ዉስጥ እያቆጠቆጠ ነዉ። ይኸ ተረት አይደለም አግጦ የመጣ እጅ እግር ያወጣ እዉነት ነዉ። ናሽናሊስቱ በቀለ ፖሎቲከኛዉ በቀለ አስተማሪዉና ምሁሩ በቀለ ኢትዮጲያዋያን እንዲለያዩ እንዲፋጁ አዉጇል ።
በቀለ ጤናማ አዕምሮ ቢኖረዉ ስለቋንቋ እድገት አወንታዊ በሆነ መንገድ ተመራምሮ ምን ማድረግ እንደሚቻል ባሰበና በነገር ነበረ። ለምሳሌ አይሪሾች ቋንቋቸዉ በእንግሊዘኛ እየተተካና እየመነመን በመሄዱ ብዙ ዘዴዎችን በመጠቀም መልሰዉ ለማሳደግ እየጣሩ ነዉ። ከአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እስከኮሌጅ ድረስ አዲስ የቋንቋ ፕሮግራም ዘረጉ። አዳዲስ የቲቭ ቻናሎች፡ መጽሄቶች፤ ጋዜጦች ቋንቛዉን እንዲያስምተሩ ማበረታቻ ሰጡ። ማንም ሰዉ በቀላሉ ኮፒዉተሩ ላይ በነጻ ጭኖ ለመማር እንዲችል የአይሪሽ ቋንቋ ሶፍትዌር አዘጋጁ። በሁሉም የትምህርት ደረጃ ቋንቋዉን እንደ ዋና ትምህርት ለሚወሰዱ ተማሪዎች ማበረታቻ የገንዘብ ድጋፍ ፕሮግራም አዘጋጁ፤ በአዉሮፓ ህብረት ቻርተር ላይ ጭምር ቋንቋዉ እዉቅና እንዲያገኝ አስደረጉ ። ሌሎችንም ማበረታቻዎች በማድረግ ማንም ሰዉ በፈቃደኝነት እንዲማርና ቋንቋዉን እንዲጠቀም እያስቻሉ ነዉ። ከዚያ ዉጭ ቋንቋዉን ከማይናገር አትጋቡ አትገበያዩ አብራችሁ አትኑሩ የሚል የድንቁርናና የጥላቻ ዘመቻ አልከፈቱም።
ለቋንቋዬ ይቅርታ ፡እጠይቃለሁ ። በቀለ ገርባ ከሰዉነት ስብዕና ወርዶ የሰዉ ገራባ ሆኖ ታይቶኛል። ሁሉም ነገር አልቆበት ዘረኝነት ብቻ የቀረዉ የሰዉ ገራባ!
በራሱ እዉነት በራሱ ህልም በራሱ ትርክት ዉስጥ የሚኖር እራሱን ብቻ የሚያዳምጥ ሚስኪን ነገር ግን ግን አደገኛ ሰዉ ነዉ ።
በቀለ በዘረኝነት የናወዘዉ ህይወቱ ፍጻሜ የሚያገኘዉ የቋመጠዉን ስልጣን ሲያገኝ ብቻ ነዉ። ነገር ግን በቀለ ገርባ ለጉዞዉ የቋጠረዉን መርዝ በህዝቡ ዉስጥ ሳይረጭ እንደ ጆሴፍ ጎብልስ ሁሉ እራሱ ተጎንጭቶ ያበቅለታል። ኢትዮጲያዊያን ግን በአንድነትና በፍቅር ለዘላለም ይኖራሉ።
ዛሬም ነገም ክብር ለኢትዮጲያ አንድነት ለታገሉና ለሚታገሉ ሁሉ ይሁን!
