ሁሌ እናስታውሳቸው
ተቀብሮ እንዳይቀር
አኩሪ ታሪካቸው!!!!!!!
ታዬ ዳማ ማን ነው??

ታዬ ዳማ ከአባቱ ከአቶ ዳማ ናደሞና ከእናቱ ከወ/ሮ ታመቸሽ ፈተራት በ1950 ዓ/ም በደብረዘይት ከተማ ተወለደ። ከሰፊ ቤተሰብ የተወለደውና የቤተሰቡ 7ኛ ልጅ የነበረው ታዬ ዳማ መጀመርያ ደረጃ ትምህርቱን በአፄ ልብነድንግል ወሰንሰገድ ት/ቤት ከተማረ በኋላ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በኢቫነጀሊካል ሚሽን ትምህርት ቤት ተከታትሏል። በእድገት በህብረት ዘመቻም ከተሰማራ በኋላ፤ ዘመቻውን አቋርጦ በመመለስ በኢሕአፓ ውስጥ ተደራጅቶ ትግሉን ቀጥሏል። ለትግሉም ከፍተኛ አስተዋፅኦ በማበርከት ለህዝቡ፤ ለሀገሩና ለድርጅቱ ያለውን ፍቅር በተግባር በማስመከር በታሪክ ላይ አሻራውን ጥሎ አልፏል።
የደርግ ጭፍጨፋ እያየለ በመጣበትም ወቅት በድርጅቱ የተሰጠውን ተልእኮ በቆራጥነትና በንቃት ከተወጣ በኋላ ሲጠረጠር ወደ አዋሽ አርባ ሔዶ ፎቶ ቤት ከፍቶ ለመኖር ተገዷል። በመጨረሻም የራሱ ጓድ በነበረና ወደ አንጃነት በተቀየረ ከሃዲ ተጠቁሞ፤ ካለበት ቦታ ተይዞ በማስመጣት በአሰቃቂ ሁኔታ በሚየዝያ 2/70 ዓ/ም እንዲገደል ተደርጓል።
በዘውዲቱ ወርቁ እንደተፃፈው፤…….
“እናትና ዘመዶችም ሃዘናቸውን እንዲህ ሲሉ ገልፀዋል፤……
ቆንጆ ታይቶ ነበር
ሸበላ ወጣት
ገና ሳይፈጠር
ታየ ብለውት
አይተን ሳንጠግበው
ቡዳ በላባት
እናትም በመቀጠል፤…
ብርሃን መስሎ ወጥቶ
ታየ ብለነው
አይናችን ሳይጠግበው
ሸኙት አርቀው
እናት ትንሽ ቆይተውም፤……
ደብረ ዘይት ጋራ
ዛሬ ላማክርህ
ልጄን ደብቅልኝ
ቅጠል አልብሰህ
ሮጦ ያልጠገበ
ህፃን ነው ብለህ
ቀን እስክያልፍ
ያለፋል…ታሻግራለህ!!”
ታዬ ዳማ በአሁኑ ሰአት ከወያኔ ጋር እየተዋደቀ ላለው ወጣት ትውልድ አርአያና ምሳሌ ነው። ነፍስ ይማር በጣም እንኮራበታለን!!!!!
አንድነት ሃይል ነው!!!
የተለያዩ የህዝብ ልጆችና ሰማዕታት አጭር ታሪክ (BIO)ይቀጥላል !!
አንድነት ሃይል ነው!!!
የተለያዩ የህዝብ ልጆችና ሰማዕታት አጭር ታሪክ (BIO)ይቀጥላል !!
