March 28, 2019 – Konjit Sitotaw
“ ሃገራችን ውስጥ የተፈጠረው የፖለቲካ ዓየር ውጥረት ይታይበታል። በዚህ ውስጥ አንድ ሰው አስርም ቢሆን ተከታይ ያለው፤ ቤተሰቡን ብቻ የሚመራ ቢሆን በጣም በጥንቃቄ መራመድ አለበት። እያንዳንዳችን ከአንደበታችን የሚወጣው ነገር እሳት እየጫረ እንደሆነ መረዳት አለብን። እያንዳንዳችን በምንጽፈውና በምንናገረው ነገር ሳቢያ በሃገራችን ላይ ለሚመጣው ጥፋት አስተዋጾ እንዳለን ማወቅ አለብን እላለሁ።” አርቲስት ታማኝ በየነ የዲሲ ግብረ ኃይል ሊቀ መንበር።
በምዕራብ ጉጂና ጌዴዖ ዞኖች ግጭት ቀዬውን ጥሎ እንዲበተን የተገደደው ቁጥሩ የበዛ ሕዝብ ዛሬም ደራሽ ዕርዳታ ይሻል።ለግጭቶቹ ዘላቂ መፍትሔና ተፈናቃዩን ሕዝብ መልሶ ለማቋቋም የአካባቢውና የፌድራል መንግስት ሊወስዱ ከሚገቡ እርምጃዎች ባሻገር ዜጎች በሕይወት አድኑም ሆነ በሃገር ደረጃ ብጥብጥን በሚያርቁና ሰላም በሚያመጡ ጥረቶች ዜጎች ያላቸውን ሁነኛ ድርሻ የሚያመላክት ምግባር ነው።የዋሽንተን ዲሲው “ዓለምቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት” የተሰኘው የጋራ ግብረ-ኃይል መሰንበቻውን ለጌድዎ ተፈናቃዮች እርዳታ አሰባስቧል።
