March 28, 2019

Source: https://fanabc.com/2019/03/%E1%8D%8C%E1%88%B5%E1%89%A1%E1%8A%AD-%E1%8B%A8%E1%8A%90%E1%8C%AD-%E1%89%A5%E1%88%84%E1%88%AD%E1%89%B0%E1%8A%9E%E1%89%B0%E1%8A%9D%E1%8A%90%E1%89%B5%E1%8A%93-%E1%89%B0%E1%8C%88%E1%8A%95%E1%8C%A3/

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፌስቡክ የነጭ ብሄርተኝነትንና ተገንጣይነተን የሚደግፉ እና የሚያደንቁ አካላትን ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ ከፌስቡክና ኢንስታግራም እንደሚያግድ አስታወቀ፡፡

ግዙፉ የማህበራዊ ትስስር ገፅ የሆነው ፌስቡክ የሽብርተኛ ድርጅቶችን ለመለየት እና የሚጠቀሙባቸውን ነገሮች ለማገድ እራሱን እያደረጃ መሆኑን ነው ያስታወቀው፡፡

በቅርቡ በኒውዝላንድ በሁለት መስጊዶች በአንድ ነጭ ብሄርተኝነት አቀንቃኝ የተፈፀመው ጥቃት በፌስቡክ በቀጥታ በመተላለፉ ኩባንያው ግፊት ሲያደረግበት እንደቆየ ነው የተነገረው፡፡

ከዚህ በፊት ኩባንያው የነጭ ሀገር እንመስርት የሚሉ ሀሳቦችን ጨምሮ የተወሰኑት የነጭ ብሄርተኛ ሀሳቦች በዘረኝነት እንዳይፈረጁ ውሳኔ አሳልፎ እንደነበር ተነግሯል፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ