March 30, 2019
ዋና ጉዳዮች
- ከ42 የትውልደ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያን ነን በሚል ለጠቅላይ ሚኒስቴሩ ስለ እስክንድር ነጋ የጻፉጽ ደብዳቤ በእርግጥም ከሰዎቹ የተጻፈ ከሆነ በእኔ ግንዛቤ ስህተት ነው፡፡ ከአገርና ሕዝብ ይልቅ ስለአንድ ሰው ሊያውም ምንም ይሄ ነው የሚባል ነገር ባልተፈጠረበት የዚህ ሁሉ ማካበድ ሰዎችን በአላስፈላጊ አስተሳሰብ መበከል ከአልሆነ ከኢትዮጵያዊነት አንጻር አይመጥንም፡፡
- የአዲስ አበባ ባላደራ ማሕበር የመጀመሪያው መንግስትን የሚገስጽና ስለ ሕዝብ መብትና ደህንነት ከፖለቲካ ፓርቲ ውጭ የሆነ የሲቪል ማህበር በመሆኑ ዲሞክራሲ ከታሰበ ይሄ ማህበር ምሳሌ ሊሆን ሲገባው ሊወቀስ ባልተገባው ነበር፡፡ ዝርዝሩን ያንብቡ
- የኤርሚያስ ለገሰ ፉከራ አብይን ሰው እየጠላው ነው በሚል አሳቻ ወቅትን ጠብቆ ለወያኔ የሚያገለግልበትን ሴራ እየተወጣ እንደሆነ ሕዝብ ያስተውል፡፡ ኢሳት ውስጥ ሌሎችም አሉ፡፡ ሕዝቤ ሆይ ንቃ፡፡
- ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ትክክለኛ ኢትዮጵያዊ ደጋፊዎቹን እያጣ ለሴራቸው የተመቸ የመሰላቸው በደጋፊነት እየተቀላቀሉት እንደሆነ ቢያስተውል ጥሩ ነው፡፡ አብይ የሚናገራቸውን ነገሮች ለመንጋ አስተሳሰብና ራሱን ለማስተዋወቀዋወቅ እንዳይጠቀም በጽኑ አሳስባለሁ፡፡ በዝርዝር አለ፡፡
- በሚኒስቴርነት ደረጃ የተዋቀረው የሠላም መሥሪያ ቤት ምን እየሰራ ነው፡፡ በሚዲያ እንኳን ሕዝብን ከሕዝብ የሚያቀራርቡ ፕሮግራሞችን እየሰራና እያቀረበ እንደሆነ አላይም፡፡

በመጀመሪያ አብይ በትላነትናው ዕለት ከጋዜጠኞች ጋር ያደረገው ቆይታ ሰሞኑን ከነበረው ፖለቲካ ጥሩ በሚል ወስጄዋለሁ፡፡ ያም ሆኖ ግን እኔን ያላስደሰቱኝ ብዙ ጉዳዮች አሉ፡፡ አብይ ከጋዜጠኞቹ ውይይት በፊት የነበሩት አቋምና ፖለቲካው እውነት ለመናገር በጣም የሚያናድድ ነበር፡፡ አጋጣሚው ለሴረኞች ተመችቶ ነበር፡፡ ይሄን በማንም ማሳበብ አልፈልግም የራሱ የአብይ ድክመት የፈጠረው ክፍተት ስለሆነ፡፡ በትላንትናው ዕለትም ብዙዎች በንግግሩ ቢደሰቱበትም እኔን ያላስደሰቱኝ ብዙ ነገር አሉ፡፡ ይሄን የምለው አብይ ላይ ነገር ለመምዘዝ አደለም፡፡ በደንብ እንዲያስተውለው እንጂ፡፡ ብዙ የሚስታቸው ነገሮች አሉና፡፡ እያንዳንዱ እሱ የሚፈጥረው ስህተት ምን ያህል ለከፋ ችግር እንደሚዳርግ ተረድቶ ቢመራ ጥሩ ነው፡፡ አገር በመንጋ አትመራም! ወደ አብይ እመለሳለሁ ግን ለኢትዮጵያ ሕዝብና ምን አልባትም ሳታውቁ ለምታጠፉ ቅድሚያ የምለው አለኝ፡፡
ለኢትዮጵያ ሕዝብ፡- ዛሬ ዶ/ር መረራን በቴሌቪዥን መስኮት የተናገረውን የሠላም ማሳሰቢያ ሰማሁ፡፡ እውነት ነው! የተሻለ ሲጠበቅ የባሰ እየመጣ ይሄው 50 ዓመት ሆነ፡፡ በጠም ብዙ ዘመን፡፡ ብዙዎቻችን የተወለድንው እንግዲህ ከዚያ በኋላ ነው፡፡ ብዙ መከራ አይተናል፡፡ አሁን መጣ የተባለውን ለውጥ ብዙ ተስፋ አድርገን ይሄው አሁንም የባሰ የሚመስል ነገር እያየን ነው፡፡ በአለፈው 27 ዓመት በደንብ አገርንና ሕዝብን የማፍረስ ሴራ ሲሰራ መቆየቱንም ውጤቱን እያየን ነው፡፡ ያም ሆኖ አብዛኛው ችግር እየመጣብን ያለው ለእምነት፣ ለስብዕናና ለሕሊና የማንታዘዝ መሆናቸውን ነው፡፡ ሕዝብ ስል እንግዲህ ሚስኪኑ ሁሉ ማለቴ ነው፡፡ ሚስኪኑ ኢትዮጵያዊ ምን ያድርግ ሊባል ይችላል፡፡ ሴረኞች እኮ እንደመንጋ እየነዱ እየተጠቀሙበት ያለው ይሄንኑ ሚስኪን ሕዝብ ነው፡፡ ስለዝህ ሕዝቤ ሆይ እስኪ በየሰፈራችሁ ሽማግሌዎች ተሰባሰቡ፣ የእምነት አባቶችም ተነጋገሩ፡፡ በእምነት በዘር ሳትከፋፈሉ እስኪ ስለ ሀገር በአንድ ላይ ለመናገርና ሕዝብንም ለመገሰፅም ሆነ ለመምከር ወደፊት ውጡ፡፡ ይሄን አለማድረጋችሁ ብቻ ሳይሆን ይባስ እምነትም ሕሊናም የሚጠየፈውን ዘረኝነትና ጥላቻን የምታስፋፉስ ስንት ናችሁ? እርሱት የክርስትናውን ጵጵስና፣ የእስልምናውን ሼክነት፡፡ መጀመሪያ እንደ አንድ ኃላፊነት እንዳለበት ሰው ማሰብ ጀምሩ፡፡ ሕዝቤ ሆይ አስተውል፡፡ ከማንነትህ አዋርደው የእነሱ የአስተሳሰብ ባሪያ እያደረጉህ ያሉትን አስተውል፡፡ እምነት ፍልስፍናሕንና ሕሊናህን አታጉድፍ፡፡ እግዚአብሔርም በማስተዋል ብትጓዝ ይረዳሀል፡፡
ማንም ይሁን ማን በወሬ አይፍታሕ፡፡ ነገሮችን አታድንቅ፡፡ ለአንተ ከአንት በላይ የለም፡፡ ብዙዎች በምሁርነት ሥም እጅግ የወረደና የተዋረደ አስተሳሰብ እያጋቡብህ እንደሆነ አስተውል፡፡ የትኛውንም የትምህርት ደረጃ ቢደረስ ፍልስፍና ላይኖረው ይችላል፡፡ የትምህርት ስኬቱም በአድር ባይነትና የሌሎችን ሀሳብ ስለሚጮህ ሀሳባቸውን የተቀበላቸው ሁሉ እያደነቁ ወደላይ ስለሚያሳድጉት ነው፡፡ መጀመሪይ እሱ ለሌሎች ሀሳብ ባሪያ ይሆንና ይሄን ባርነት ወደ እንተ እየጋባ መሆኑን አስተውል፡፡ የታላቁ ሊቅ አይንሽታይን(አንስታይን) መሠረታዊ ችግር የነበረው ይሄ ነበር፡፡ አይንሽታይን ከሳይንስ አለም ሁሉ ሊጠፋ የሚችልበት ከባድ አደጋ ውስጥ ነበር፡፡ ሆኖም በኋላ ምን እውቀት ቢኖረው የሰዎች ሀሳብ ተገዥ ካልሆነ እውቀቱን ብቻም ሳይሆን እሱንም ከሳይንስ ዓለም እንደሚያጠፉት ታስቦት ብዙ ለፋ፡፡ በጥረቱም ተሳካለት ዛሬም ድረስ በዘመናችን በታላቅ ሊቅነቱ እናነሳዋለን፡፡ አይንሽታይን ግን በምሬት ሁሌ የሚናገረው የበላይ ነን የሚሉትን ሀሳብ ባርነት ሥር መውደቅ ከውድቀት ሁሉ ውድቀት ነው ብሎ ነው፡፡ የበላይ ስል አጋጣሚን ሁሉ ለራሳቸው በማድረግ ከላያችን የተቀመጡት ማለቴ ነው፡፡ በትምህርት፣ በሥልጣን፣ በእምነት፣ በሽምግልናም በመሳሰሉት ሁሉ፡፡ ይሄን ስል ግን በቅንነትና በኃላፊነት የሚሰሩ መሪዎቻችንንና የበላዮቻችንን መተባበርን የዛንው ያህል እንድናስብና እንድንከተለው ነው፡፡ ስለዚህ ማንም ምን ይበል ምን አእምሮ አለህ አስተውል፡፡ ብዙም አታካብድ፡፡ የሚሆነውን ብቻ አስብ፡፡ አሁን እየሆነ ያለው ብዙ ሰው በመንጋ እየተነዳ ይደግፋል በንጋ ይቃወማል፡፡
ሰሞኑን በባሕርዳር ከዛ ቀደም ብሎ በኦሮሚያ በተለያዩ ቦታዎች ራሳቸውን በዘረኝነትና ጥላቻ መረዘው ከስርዓት ውጭ ሲንቀሳቀሱ የነበሩትን እንደምሳሌ እጠቁማለሁ፡፡ ከብዙ መከራ በኋላ ዛሬ በጥጋብ ሠላምን ንቀን ወደ አልተፈለገ አስተሳሰብ በማስገባት የእርግማን ዘሮች ሊያደርጉን የሚሞክሩ ብዙዎች ናቸው፡፡ ሁሉም ያስተውል፡፡
ከዚህ ቀጥሎ በነጥብ በነጥብ አንዳንድ ግለሰቦችንና ቡድኖችን አነሳለሁ
ለአብይ የተላከው መልዕክት፡-እስክንድርን አስመልክቶ 42 ትውልደ ኢትዮጵያውያን ነን ብለው ለአብይ ላኩለት የተባለውን ደብዳቤ አየሁት፡፡ ልክ ግን አደለም፡፡ ስለ እስክንድር ብዙ የምረዳው አለ፡፡ እስክንድር አሁን ለመጣው ለውጥ ትልቅ መስዋዕትነት እንደከፈለ አሁንም ቢሆን ለአገርም ለሕዝብም ስጋት ሊሆን የማይችል እንደሆነ አስባለሁ፡፡ ስለዚህ ጉዳይ አመለሳለሁ፡፡ ሰሞኑን በ42 ሰዎች ተጻፈ የነታበለው ነገር ግን እርግት ትክክል የእነዚህ ሰዎች ከሆነ ልክ አደለም፡፡ ከአገርና ሕዝብ ይልቅ የእስክንድርን ጉዳይ በጣም አካብደውታል፡፡ በዚህም የተለመደውን የመንጋ አስተሳሰብ ሊፈጥሩ እንደሚችሉ በመረዳቴ አልተመቸኝም፡፡ አብይን ስለአጠቃላይ አገር ጉዳይና ሕዝብ መውቀስ በዛውም የእስክንድርንም ጉዳይ ከምሳሌ ባላለፈ ከመትቀስ ይልቅ እነሱ ስለ አንድ ግለሰብ ሊያውም ምንም በአልተፈጠረበት ሁኔታ ይሄን ያህል ትኩረት ሰጥቶ ማካበድ ሰዎችን እኛ ታዋቂ ነንና እስክንድርን እንደግፋለን ስለዚህ የእስክንድር ደጋፊ ሁኑ አይነት ዘመቻ ይመስላል፡፡ እስክንድርን መደገፍ ያለበት እስክንድር በሚለው ሐሳብ ተረድቶና አምኖበት ቢደግፈው ችግር የለውም ይሄ እይነቱ አካሄድ ግን አደገኛ የሆነ ነው፡፡ ይሄ አካሄድ ነው ዛሬ ሁሉም ምንም በአልገባው ሁኔታ ዝም ብሎ የሆነ ቡድን ደጋፊ እየሆነ በራሱ ላይ መከራ የሚጠራው፡፡ ምሁርን ነን የሚል ካለ ከግለሰብ ውጡ ማንም ቢሆን ከአገርና ሕዝብ አይበልጥም፡፡ ያም ሆኖ ምንም በአልተፈጠረበት ሁኔታ ይሄን ያህል ማካበድ ስህተት ነው፡፡
የኢሳቱ ኤርምያስ አብይ ላይ መረጃ አለኝ ማለቱ፡፡ ስለዚህ ግለሰብ በተደጋጋሚ ለመተቆም ሞክሬያለሁ፡፡ ችግሩ አብዛኛው ሰው የመንጋ ደጋፊ እየሆነ ምን እውነት ብትናገር በመንጋ ያደራጁትና የራሳቸው አስተሳሰብ ተገዥ ያደረጉት ደጋፊያቸው ጫጫታ የእውነት ተናጋሪዎችን እያከሰመ ነው፡፡ ኤርሚየስ የወያኔ ሰላይ ሆኖ ኢሳትን እንደተቀላቀለ በብዙ ነገሮች አስባለሁ፡፡ ይሄን ስጋቴን ብዙ ጊዜ ጠቁሚያለሁ፡፡ አሁንም አጋጣሚውን ለመጠቀም አደለም፡፡ የሚገርመው ግን ከአንድ ሳምንት ገደማ ይሄንኑ ግለሰብ ሕዝብ እንዲያስተውለው ጠቁሜያለሁ፡፡ እሱን ብቻም ሳይሆን ሌሎችም ኢሳት ውስጥ አሉ፡፡ ለእኔ ሀብታሙ አያሌውና ተወልደ በየነ ኢሳት ውስጥ በብዙ ነገር የምጠረጥራቸው ናቸው፡፡ ይሄ አናሊቲካል ግንዛቤዬ ነው፡፡ ሪዮት ብዙም በአልገባት ሁኔታ አጫፋሪ ነው የምትመስለኝ እንጂ ሴራ ውስጥ ያለች አልመሰለኝም፡፡ ሌሎችም በአልገባቸው ሁኔታ የሚንቀሳቀሱ አሉ፡፡ ሰሞኑን የአብይ ሆኔታ ተመቻችቶልኛል ጥሩ አጋጣሚ ነው በሚል ነው አብይ ኢንሳ እያለ የሰራውን ጉድ እናወጣለን ብሎ የፎከረው፡፡ ከጀምሩ የአብይ ወደ ስልጣን መምጣት እጅግ ከአስደነገጣቸው ሰዎች አንዱ ነው፡፡ ሌላኛው በግልጽ የሚነበበው ጀዋር ነው፡፡ ኤርሚያስ በበረከት ስምዖነ የተላከበትን ተልዕኮ እያከናወነ ይመስላል፡፡ ብዙ ሰው አያስተውልም፡፡ ሁሌም ሚስጢር አዋቂ በመምሰል የሚናገራቸው ከእነበረከት እንዲህ እንዲናገርና የሕዝብን አስተሳሰብ በተገዥነት ለማኖር ነበር፡፡ አሁንም እላለሁ፡፡ ሕዝቤ ሆይ ማንም ይሁን ማን አያስትህ፡፡ አብይ ኢሕአዴግ ውስጥ ሲሰራ እንደነበር እናውቃለን፡፡ ከደሙ ንጹሕ የሆነም ሰው ነው ብለን አናምንም፡፡ ሆኖም የእኛ የአሁን ችግር ሰዎች በፊት በሰሯቸው ጉዳይ ሳይሆን ዛሬ ምን እየሰሩ ነው ነው፡፡ የአብይ ችግር አሁን የሚያጠፋቸው ወይም ያላወቀባቸው ነገሮች እንጂ በታሪክ ውስጥ ያለው ሕይወቱ አደለም፡፡ ጥያቄያችን ዛሬ አብይ ከዛ ታሪክ የምር ተላቆ አገርንና ሕዝብን ወደ ተሻለ ጊዜ ለማሻገር ከልቡ እየሰራ ነው ወይ ነው፡፡ ኦሮሞነት፣ ማንነት ሌላሌላ ሴራዊ ችግሮች የሉበትም አሉበት ነው፡፡ ከእነዚህ የፀዳ ከሆነ በሥራው እንደሚሳሳትም እናውቃለንና ሆን ብሎ ካላደረገው እንረዳዋለን፡፡ አሁንም ለዛ ነው ከዚህ በኋላ ትንሽ ለእሱ የሚጠቀመውን መናገር የምፈልገው፡፡ በመንጋ አልደግፈውም፡፡ ከዛ ይልቅ የሚጠቀመው ችግሩን መጠቆም ነው፡፡
ለአብይ ምክር፡- መጀመሪያ ተስፋ ከአደረግነው በብዙ ተስፋ እስከመቁረጥ የደረሱ ሰዎች እንዳሉ አንትም ትረዳለህ፡፡ ብዙ ድጋፍ ነበረህ፡፡ ዛሬ ምን ያህል ደጋፊ እንዳለህ አላውቅም፡፡ መጀመሪያ ከልባቸው የደገፉህ ዛሬ ግን በአንተ ተስፋ የቆረጡ ከአሉ ትክክለኛ ደጋፊዎችህ እነሱ እንደነበሩ በደንነብ አስብበት፡፡ እነዚህ ሰዎች ራዕያቸውና ፍላጎታቸውም ታላቅና አገርና ሕዝብን መሠረት ያደረገ እንደሆነ አስተውል፡፡ ከእነዚህ ውጭ እሰካሁንም አንት በደጋፊነት የዘለቀ ሊኖር ይችላል፡፡ አይከፋም፡፡ አሁን ያሉት ብዙ የሚባሉህ ደጋፊዎችህ ግን በፊት እንደጠላት የነበሩት አጥፊ ሆነህ አሁን ግን ከኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በአፈነገጠ እየሰራ ነው የውሸቱን ነበር ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ የሚለው ብለው የሚያስቡ ናቸው፡፡ ዛሬ ኦሮሞ የሆንክላቸው ስለመሰላቸው ዘረኛ ኦሮሞዎች ድጋፋቸው ሲጨምር ከልብ ይደግፉህ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ግን ከአንተ ሸሽተዋል፡፡ ዛሬ ስለ እስክንድር የማይረባ ነገር ስለተናገርክላቸው ደስ ብሏቸው መሪያችን ማለት የጀመሩ አሉ፡፡ ከኢትዮጵያዊነት ያፈነገጥህ የመሰላቸው ብዙ አሁን በደጋፊነት ተቀላቅለውሀል፡፡ እነዚህ ሁሉ አዲስ ደጋፊዎችህ ግን ነጥብ እየመዘገቡ ነው የሚደግፉት፡፡ ነገ አንትን ስለሚፈልጉ ሳይሆን ወደሚፈልጉት አገርንና ሕዝብን እየወሰድክላቸው ስለሚመስላቸው ነው፡፡
የሰሞኑ ንግግረህ እስክንድርንና ሌሎች ጉዳዮችን አስመልክቶ፡- አብይ የእስክንድር ነጋ የባላደራ ማህበር ማቋቋምን ለመንጋ ፖለቲካ ተጠቀምክበት፡፡ አንዳንዶችም ወንጀል ነው ሊሉ በቴሌቪዥን ብቅ አሉ፡፡ ግን ለምን ይሄን አደረገ የሚለውን አንተም ሆንክ ሌሎች ትንፍሽ ሊሏት አትፈልጉም፡፡ ግልጽ ነበር፡፡ ብዙ ኢትዮጵያዊ ደጋፊህም እጅግ ያዘነበትና ይሄ ሰውዬ ተስፋ የለውም ብሎ ተስፋ የቆረጠበትን እውነት አትካደው፡፡ እስክንድር በጠራው ስብሰባ ተገኝው አንትንና ለማን በሥም እየጠሩ የራሳቸውን ምልክት ያሳዩ የነበሩ ወጣቶችን አስተውል፡፡ ተራ ነገር አድርገህ ቆጥረህው ከሆነ አዝናለሁ፡፡ ያንትን ሥም ጠርተው እጃቸውን አፋቸው ላይ ያደረጉበት መልዕክት ድንቅ ነው፡፡ መዝናኛ ቢመስልም በብዙ ኢትዮጵያውያን ስሜት ውስጥ የተፈጠረው ይሄው ነው፡፡ ስምንት ሺ ሰው የተሰበሰበበትን ጉባኤ ብቻ አስብ፡፡ ብዙ ሌላ በሚሊዮን የሚቆጠር በዛ ስብሰባ ቢገኝ እንደሚወድ አስብ፡፡ ይሄን ከነመነሻው አጣጥለህ ሌሎችን ለማስደሰት ዲስኩር በትፈጥርበት የመውጊያውን በረት ብትመታው ለአንተው ይብስብሀል እንደተባለው ነው፡፡ የሆነው ግን እኮ የሲቪል ማሕበራት ይቋሙ ሰዎች መንግስት ቢያፋ የሚጠይቁበት የተደራጀ ሁኔታ ይኑራቸው እያል በምንዘፍንበት ወቅት የመጀመሪያው ይሄው ማህበር መቋቋሙ ነበር፡፡ ተደራጅቶ በሠላማዊ መልክ መቃወምን ብቻም ሳይሆን ማረምን የሚያስችል ማህበር መሆኑ ታስቦ ይበል ሊባል ሲገባው ጭራሽ ዛቻና ማስፈራራት ያው የተለመደው አስተሳሰብ ስላለ ነው፡፡ ሕዝብ በሚያስተዳድሩት አመኔታ ስላጣ ራሱን አደራጅቶ ከሚመቱበት ችግሮች ለመከላከል እኮ ነው የሆነው፡፡ ከተማውን ሰላም፣ ሁሉ ነገር የተመቻቸ ቢሆነ አይደለም 8 ሺ ሰው ስምንትም ሰው አንድ ላይ ባልተሰበሰበ፡፡ የራስህን ችግር ወደ ሌላ ከመውሰድህም በላይ ሌላ አፍራሽ የሆነው ንግግርህ ብዙ ዋጋ ያስከፍላል፡፡ እስክንድር የሰበሰባቸውና የፈጠረው ማህበር ግን በኢትዮጵያዊነትና ሕዝብ ላይ ስጋት እንደማይሆን ራስህም ታውቀዋለህ፡፡ ያንትም ንግግር ሰላማዊ በመሆኑ እንጂ ስለ አሸባሪዎቹማ አንድም ቃል አልተናገርህ፡፡
የኦሮሞነት ስሜት ንግግርህ፡- ይሄን ስህተት ደጋግመህ ትሰራዋለህ ወይም የምታምንበትም ሊሆን ይችላል፡፡ ግን አደገኛ እንደሆነ ብታስተውል ጥሩ ነው፡፡ በዛው ንግግርህ የአዲስ አበቤ ኢትዮጵያውያንን ራሳቸውን በዘረኝነትና ጥላቻ ከተመረዙ ለመከላከል የወሰኑበት አቋም አቃለህ የዘረኞቹን ሐሳብ ማን ያዳምጣቸው? ከእነሱ በኩል ያለውን ለማዳመጥ ዝግጁ አደሉም ኢትዮጵያውያን አይነት ንግግር ሰምቼብሀለሁ፡፡ አብይ በዚህ ጉዳይ ከአንት በላይ በደንብ የማውቅን እውነት እየካደክና ለጸረ-ኢትዮጵያውያን ከለላ እየሆንህ እንደሆነ አሰጋለሁ፡፡ ላለፉት 5 ምናምን ዓመታት ስለኦሮሞ ፖለቲካ እጽፋለሁ፡፡ አነባለሁ፣ የእድሜየን ይበልጠውን ደግሞ በተግባር አይቼዋለሁ፡፡ ሌላ ምን መስማት እንዳለብን ልትነግረን እንደፈለግህ አላውቅም፡፡ ይሄን የምትለው ከአለህ ብትነግረን ጥሩ ነበር፡፡ ችግሩ አንድና አንድ ነው፡፡ ሴረኞች አሉ፡፡ ሕዝብን በጥላቻና ዘረኝነት እየበከሉ ዓላማ ቢስና የእነሱ የአስተሳሰብ ባሪያ በማድረግ አገርና ሕዝብ ማርከስ ነው፡፡ ይሄ በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ በብዙ መልኩ የተሳከ የሴራ ስልት ነው፡፡ አሁን በፍጥነት ይሄንኑ ስልት በአማራ ሕዝብ ዘንድ እያሰራጩት ነው፡፡ እስኪ የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ እየተባለ ዛሬ ድረስ የሚፈዝብን ምንድ ነው፡፡ ሌሎችን ሁሉ አጥፍቶ ሁሉንም የኦሮሞ ማድረግ? ይሄ እኮ ነው የተፈጠረው አስተሳሰብ! ስለዚህ ከእንደዚህ ያለ ነገርህ ውጣና ከልብህ ከሆነ ኢትዮጵያውያንን ተቀላቀል፡፡ በመጀመሪያ የሹመት ንግግርህ ብዙ ኢትዮጵያውያን እምባ እየተናነቃቸው ሲሰሙህ ዛሬ ደጋፊ የሆኑህ እንዴት እንደደነገጡ እናውቃለን፡፡
ራስህን ማስተዋወቅ፡- አብይ ሆይ አንተ መሪ ነህ ሕዝብ በየቀኑ የምትሰራውን ያያል፡፡ የምትናገረውን ያደምጣል፡፡ ራስህን በራስህ ማድነቅ ስትጀምር የብዙዎን እውነተኛ ደጋፊህን እያጣህ እንደሆን አስተውል፡፡ ሰሞኑን ጭራሽ በቴሌቪዥን ስለራስህ ዶኪመንተሪ አሰርተህ ማስደነቅ ጀምረሀል፡፡ በጣም አደገኛ ስህተት ነው፡፡ ከጋዜጠኞች ጋር ያደረከው ውይይት በብዙ መልኩ በጎ ነው፡፡ ግን የበቤተመንግስት ፕሮጄክትህን ስኬት ስትናገር አሁንም አላስፈላጊ ማካበድ ሆኖብሀል፡፡ የፈርስት ሌዲ ኦፊስ በ100 ዓመት ያልተሰራ ሥራ እየሰራ ነው ስትል ምን ምን የሚሉት አለማስተዋል እንደሆነ አላውቅም፡፡ የፈረስት ሌዲ ኦፊስ ሰራው ሌላ ቁም ነገር አይደለም፡፡ የሆነ ወሳኝ ፕሮጄክት የፌረስት ሌዲ ኦፊስ እንዲሰራው ከተደረገ ለፈረስት ሌዲ ኦፊስ ትልቅ ሊሆን ይችላል፡፡ ለኢትዮጵያ እኮ ግን የጠ/ሚኒስቴሩ ኦፊስ ሰራው የፈርስት ሌዲ የሚፈልገው የተሰራውን ድምር ሥራ ውጤት እንጂ እያንዳንዱ ግለሰብ የሚሰራውን የሚያስተዋውቅበት ፕሮጄክት አደለም፡፡ በቤተመንግስቱም አንተ የመጀመሪያው ስኬታማ እንደሆን ልትነግረን ይፈልግሀል፡፡ አስተውል የገባህው አገርን አንድ አድርጎ ኢትዮጵያን የመሠረተ፣ ታላላቅ የዓለም ቴክኖሎጂዎችን ሁሉ ወደ አገር ያስገባ፣ በዘመኑ ዓለም ሁሉ ማቆም ያልተሳነውን የቅኝ አገዛዝን አከርካሪ የሰበረ አደዋን የሚያህል ድል ለዛሬ ታሪክ ያቆየ የሚኒሊክ ቤተመንግስት መሆኑ አስተውል፡፡ ሊያውም በዛ ዘመን፡፡ አንተም እንደተናገርከው የመቶው አመት የግብር ቤት ዛሬም ጠብቆሀል፡፡ ዛሬ በዘመናዊ ዘመን ቤተመንግስቱን ሁሉ ወርቅ ብታለብሰው የሚያስመካህ አይሁን፡፡ መስራትህን ወድጄዋለሁ፡፡ ከኢምባሲዎችም ጋር ተያይዞ ያልከው ከተሳካ ጥሩ ሀሳብ ነው፡፡ ቤተመንግስት ማሸብረቅና ለሕዝብም የአስተሳሰብ ለውጥ ለማምጣት እንደ ግብዓት መጠቀመህ መልካም ነው፡፡ ከዚህ ውጭ ግን በምትለው ደረጃ የሚያስመካ ነገር የለውም፡፡ ከዛ ይልቅ በአገር አቀፍ ደረጃ ያለው ልማትና ሠላም ትልቅ ጉዳይም እንደሆነ አስተውል፡፡ የምትመራው ኢትዮጵያን እንደሆነ አስተውል፡፡ አንተ የምተስበውን ከዛም በላይ የምናሰብ ብዙዎች አለን፡፡ የገጠመህ እድል መሆኑን አትዘንጋ፡፡ ይልቁንም ይህን እደል ከአላስፈላጊ መታበይ በጸዳ ተጠቀምበት፡፡ ሕዝቡ በራሱ ጊዜ የመስክር፡፡ ያም ሆኖ ሕዝብ መሠከረልኝ ብለህ አትታበይ፡፡ ሥራህ ጭምር እንደሆነ አስብ፡፡ እንደምሳሌ ነው የምጠቁምህ፡፡ አነሰም በዛም የቀደሙ መሪዎች ብዙ ሰርተዋል፡፡ ሟቹ መለስ ኢትዮጵያን በዘር ከፋፍሎ አሁን ለገባችበት ምስቅልቅል እንደዳረጋት እናውቃለን፡፡ ግን ዛሬ ጥራታቸው የወረደ ቢሆንም ለወደፊቱ ለሚጠቀምባቸው መሠረት የሆኑ ዩኒቨረሲቲዎችንና በመንገድ ኔት ወርክ ጥሩ የሚባል ሥራ ሠርቷል፡፡ ግን አገርና ሕዝብን አፍረሶ እንደሆነ ዘንግቼው አደለም፡፡
የሠላም ሚኒስቴርና ሠላም፡- ከጅምሩ የሠላም ሚኒስቴር ብሎ ነገር አልተመቸኝም ነበር፡፡ ከሆነም ደግሞ ሥራው ሁሉ ስለሰላምና ስለ ሕዝብ፣ አገር ደህንነት ይሆናልና ብዙ ሥራ ሊሠራ ታቅዶ ይሆናል በሚል ወስደንው ነበር፡፡ እስካሁን የምናየው ግን ጭራሽ የጆሮም የከፉ ችግሮችን ነው፡፡ በአግባቡ የቴሌቪዥንና ሌሎች ሚዲያዎችን ተጠቅሞ የተለያዩ ሕዝብን ከሕዝብ የሚያቀራርቡ ፕሮግራሞችን እንኳን ሲሰራ አናይም፡፡ እንግዲህ አገርና ሕዝብ አንዴት ወደተረጋጋ ሁኔታ ይሂድ፡፡ ዛሬ ከላይ የጠቀስኩትን የዶ/ር መረራን መልዕክት እንኳን የምታክል በተለያዩ ሰዎች ልዩ ፕሮግራም ተይዞ ቢተላለፍ፡፡ ብዙዎች የማህበራዊ ሚዲያዎች ሳይቀሩ ለዚህ ተባባሪዎች ናቸው፡፡ ከሴረኞቹ በቀር፡፡ በየክልሉ የመደንፋትና የመፎካከርን ስሜት የሚፈጥሩ ባለስልጣኖች ዛሬም እናያለን፡፡ የአመራና የትግራይ ክልል አሁን የምናየው እውነት የዚህ ማሳያ ነው፡፡ ማንም ስለሰላም መሸነፍ አይፈልግም፡፡ የእምነት አባቶች ተብለው ያሉ እንኳን በሠላም ጉዳይ ሲናገሩ አይታይም፡፡ ሰሞኑን በሸዋ በኩል በኦሮሞና አርጎባ የሚል ጸብ ይሰማል፡፡ ይሄ አዲስ የግጭት ክስተት ነው፡፡ በየቦታው ደስ የማይል ነገር ነው ያለው፡፡ እስኪ ታዲያ በሚኒስቴር ደረጃ የተቋቋመው መስሪያ ቤት ምን አደረገ?
ልዑል አባት ቅዱስ እግዚአብሔር አገራችንና ሕዝቧን ይባርክ! አሜን!
ሰርፀ ደስታ
