ሁሌ እናስታውሳቸው
ተቀብሮ እንዳይቀር
አኩሪ ታሪካቸው!!!!!

አሰፋ ማሩ ማን ነው??

Image may contain: 1 person

ከህዝብ ፍላጎት ውጪ በመሆንና ህዝብ ከተነሳበት ጥያቄ በተፃራሪ በመቆም የ 66 ቱን አብዮት አቅጣጫ አስቀይሮ በወታደራዊ ጡጫ ደፍጥጦ ለመግዛት በስልጣን ላይ ቁጢት ያለውን ፋሺስታዊ ደርግ በመቃወምና ከሕዝብ ጎን በመቆም፣ ሴክተር ሪቪውን በመቃወም፤መሬት ለ አራሹ፤ የጾታ እኩልነት፤ የሃይማኖት እኩልነት፤ ዲሞክራሲ ያለገደብ፤ ጊዜያዊ ህዝባዊ መንግስት አሁኑኑ፤ የመሳሰሉትን ሕዝባዊ ጥያቄዎችን ያነሱና ለተግባራዊነቱም የታገሉ ብዙ መምህራንና የኢመማ መሪዎች የሕይወት መስዋዕትነት ከፍለዋል። ብዙዎቹም ለእስርና ከፍተኛ ስዬል ተዳርገዋል።

ዘረኛው ወያኔም በ 1983 ዓ.ም በባእዳን ሃገሮች እርዳታ ስልጣን ከያዘ በኋላ ደርግ አመቻችቶ የሄደለትን ነባርታዊ ሁኔታ በመጠቀም እኩይ ተግባሩን ቀጥሏል። ወድያው ስልጣን እንደያዘም በዘር ከፋፍሎ ለመግዛት እንዲያመቸውና ያልተማረ ትውልድን ለመፍጠር የትምህርት ጥራት እንዲወድቅ ከፍተኛ ስራ ሰርቷል። አላማውን ተግባራዊ ለማድርግም ገና አዲስ አበባ ከመግባቱ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 42 መምህራንን እንዳባረረ ታሪክ ዘግቦታል። ከእነዚህ ተባራሪ መምህራን አንዱ የኢመማ ሊቀመንበር የነበረው ዶ/ር ታዬ ወልደ ሰማያት ነበር።

በዘረኝነት የተካነው ወያኔ የሙያ መሃበሮች ለታሰበው በዘር የመከፋፈል እቅድ አመቺ ስላልሆኑና ዘርን በሙያ ማህበር ማደራጀት የማይመችና ተግባራዊ እንደማይሆን በመገንዘብ፤ እያፈረስ ወይም ቁልፍ ቦታ የወያኔ ሰው በማስቀመጥ የህዝብን እንቅስቃሴ ማፈኑን በገሃድ ቀጥሏል።። እክል ይሆናሉ ብሎ የሚያሰባቸውን የህዝብ ወገኖች በድብቅና በሚስጥር አስሯል፤ ገሏል።። በከፍተኛ ሁኔታ ትኩረት ሰጥቶ ሲሰራበት የነበረውም የመምህራን ማህበር(ኢመማ) ነበር።

በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ለትምህርቱ ጥራት፣ ለመምህራን፣ ለሕዝብ መብትና ጥቅም የቆሙትን መምህራን በጥይትና በሌሎች የግድያ ዘዴዎች ሕይወታቸው እንዲጠፋ አድርጓል። በዚህም እኩይ ተግባር ሰለባ ከሆኑት ጀግና የህዝብ ልጆች መሃከል አንዱ አሰፋ ማሩ ነበር።

አሰፋ ማሩ በወሎ ላስታ አውራጃ መቄት ወረዳ በ1951 ዓ.ም ተወልዶ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ካጠናቀቀ በኋላ በመምህርነት ሙያም ተሰማርቶ አገልግሏል። በሙያ ማኅበሩም የአመራር አባል በመሆንም የመምህራንን መብትና ጥቅም እንዲሁም የትምህርቱን ጥራት ለማስጠበቅ በሚደረገው ትግል በግምባር ቀደምትነት ታግሏል። አሰፋ ማሩ ወደ አዲስ አበባ ከመምጣቱ አስቀድሞ በአርሲ ነገሌ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የታሪክ መምህር በመሆን ሁለት አመት አገልግሏል።


አሰፋ ማሩ የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር(ኢመማ) ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የነበረ ሲሆን ከ1954 ዓ.ም ጀምሮ የኢሰመጉ አባል፣ከመስከረም 26 ቀን 1989 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ የኢሰመጉ ሥራ አስኪያጅ ኮሚቴ አባል በመሆን በኢትዮጵያ ውስጥ ሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩና ለህግ የበላይነት ታግሏል።

የሁለት ልጆች አባት የነበረው አሰፋ ማሩ ሚያዚያ 30፣ 1989 ዓ.ም. በመለሰ ዜናዊ ቀጥተኛ ትእዛዝ፤ በወያኔ ማፍያ አዲስ አበባ ውስጥ በጠራራ ፀሃይ ከቤቱ ወደ ሥራው በመጓዝ ላይ እንዳለ በግፍ ተገድሏል።

በውሸት የተካነው ወያኔም ባሰራጨው የሃሰት ዜና “ራሱን የኢትዮጵያ አንድነት አርበኞች ግንባር ብሎ የሰየመው ፀረ-ሠላም ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር ሲውሉ የቡድኑን መሪ ተክቶ ሲያስተባብር ነበር የተባለው መሪያቸው አቶ አሰፋ ማሩ ለማምለጥ ሲሞክር መገደሉን የፌዴራሉ ፖሊስ የምርመራ ማስተባበሪያ ዋና ክፍል አስታወቀ፡፡” በማለት ዘግቧል፡፡

አሰፋ ማሩ በአሁኑ ሰአት ከወያኔ ጋር እየተዋደቀ ላለው ወጣት ትውልድ አርአያና ምሳሌ ነው። በጣም እንኮራበታለን!!!!!

ነፍስ ይማር ለጀግኖቻችን!!!

የተለያዩ የህዝብ ልጆችና ሰማዕታት አጭር ታሪክ (BIO)ይቀጥላል