የሃገራችን አንዳንድ መገናኛ ብዙሃን የጋዜጠኝነት ሙያን የሚተገብሩበት መንገድ አስደንጋጭ እየሆነ መምጣቱን የሚናገሩና የሚጨነቁ ዜጎች እየበዙ ነው፡፡ አንዳንዶቹ መገናኛ ብዙሃን ሙያውን በጎጥ ዙሪያ እየቀነበቡ፣ እውነቱን በራሳቸው መንገድ እየጠመዘዙ፤ የጥላቻ እሳት ያነዳሉ ተብለው ይተቻሉ፡፡አንዳንዶቹ የክልል መገናኛ ብዙሃን በጀታቸውን የሚያስብላቸውን ክልላዊ መንግስት በማገልገል አተኩረው ሙያውን ለክልሉ ባለስልጣናት ፍላጎት አስገዝተው የጥላቻ መስበኪያ አድርገውታል ተብለው ይወቀሳሉ፡፡በማንኛውም መንገድ ቢሆን ጋዜጠኝነት በሙያው ስነ-ምግባር የማይመራ ከሆነ አስቸጋሪና አደገኛ ውጤት እንደሚያስከትል የታመነ ነው፡፡
