March 30, 2019

እስክንድር ነጋ በህሊናው የቋጠረው ሐሣብ፣ በእጁ የያዘው ኢትዮጵያዊነትን በጉልህ የሚፅፍ ብዕር ብቻ ነው:: እስክንድር ነጋ እራሱ የሚሊዮኖች ሐሳብ እንጂ ግለሰብ አይደለም::

ሃሣብን በነፃነት የማሰብና ሐሳብን የመግለፅ መብት (Freedom of Thought, Freedom of Expression & The Right to Public Assembly) በዓለማቀፋዊ የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌ ውስጥ በማያሻማ ቋንቋ ተቀምጧል::

ኢትዮጵያ በሁለት መንግሥት የምትተዳደር ብቸኛዋ የዓለማችን ሐገር እንደሆነች ጃዋር መሃመድ በይፋ ነግሮናል:: የጠ/ሚ አቢይ አህመድና የጃዋር የቄሮ መንግሥት በማለት:: ይህም በአንድ መንግሥት ውስጥ ሥውር መንግሥት (state-within-state) አለ ማለት ነው:: ያውም በሁለት ሥም የሚንቀሳቀስ ግን አንድ መንግሥት የሆነ::

የዛሬውን የእስክንደር ነጋን የባልድራሱን ም/ቤት የራስ ሆቴሉን ጋዜጣዊ መግለጫ ያገደውና ሐሳብን ያፈነው የትኛው የእህት ኩባንያ ወይም መንግሥት ነው ልንባል ይሆን?

ነብሰ ገዳዮችን እሹሩሩ እያለ የሰላም እጅ የሚዘረጋና የሚሾማቸው መንግሥት በእስክንድር ብዕር ላይ ጦርነትን ካወጀ ይህን የቴዲን ስንኝ ለማለት እገደዳለሁ::

‘በአስራ ሰባት መርፌ በጠቆመ ቁምጣ፣
ለለውጥ ያጎፈረው ስልጣን ለይ ሲወጣ፣
እንዳምናው ባለቀን የአምናውን ከቀጣ፣
አዲስ ንጉሥ እንጂ ለውጥ መቼ መጣ::’

የሠላም በሮች ሲዘጉ የአመፅና የመከላከል መፍትሄዎች በር ይሆናሉ!
===

የጠ/ሚ አቢይ አህመድ ሁለቱም መንግስት የሚከተለውን ማስተዋል ይበጀዋል::

ሄሪ ትሩማን “መንግሥት የተቃዋሚዎች ድምፅ የማፈን መርህ መከተል ከወሰነ እየዘቀጠ መሄዱንና የጭቆና እርምጃ መውሰድ መጀመሩ የሽብር ምንጭ ሆኖ የሚቀጥለው ዜጎቹንና ሐገርን በፍራቻ እንዲኖሩ ማድረግ እስከቻለ ድረስ ብቻ ነው::” ብለውናል::

(“Once a government is committed to the principle of silencing the voice of opposition, it has only one way to go, and that is down the path of increasingly repressive measures, until it becomes a source of terror to all its citizens and creates a country where everyone lives in fear.” (HARRY TRUMAN, August 8, 1950))