March 30, 2019


የባልደራስ ምክር ቤት ጋዜጣዊ መግለጫ የፀጥታ ስጋት መኖሩን ፓሊስ በመግለፁ ተከልክሏል- አቶ ንጉሱ
On Mar 30, 2019329
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2011(ኤፍ.ቢ.ሲ) በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የሚመራው የባልደራስ ምክር ቤት ጋዜጣዊ መግለጫ የፀጥታ ስጋት በመኖሩ ፓሊስ መከልከሉን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የፕረስ ሴክሬታሪ አቶ ንጉሱ ጥላሁን አስታወቁ፡፡
አቶ ንጉሱ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ አዲስ አበባን በተመለከተ የተለያዩ ሀሳቦች እንዲሁም እንቅስቃሴዎች አሉ ብለዋል፡፡
ይህንንም ተከትሎ ተጨባጭ የፀጥታ ስጋት በመኖሩ እና ውጤቱም ወደ ግጭት ሊያመራ የሚችል በመሆኑ ከእስክንድር ነጋና ከአመራሮቹ ጋር ፓሊስ ውይይት እንዳደረገ ነው የተናገሩት፡፡
በዛሬው ዕለትም ለግጭት መንስኤ የሚሆኑ ምልክቶች የታዩ በመሆኑና እነዚህን ነገሮች በሰላማዊ መንገድ ስርዓት ማስያዝ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ጋዜጣዊ መግለጫው እንዲቋረጥ መደረጉን ተናግረዋል፡፡
ሆኖም በመሰረታዊነት ለጋዜጠኛ መግለጫ መስጠት መከልከል እንደሌለበት የገለፁት አቶ ንጉሱ በወቅታዊ ሁኔታ ፓሊስ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግና ችግሮችን መከላከል ስላለበት መቋረጡን ጠቁመዋል፡፡
በቀጣይ ጊዜያት ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የፕረስ ሴክሬታሪያት ከጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ጋር በመነጋገር ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚዘጋጅ ተናግረዋል፡፡
በኤፍሬም ምትኩ
በኤፍሬም ምትኩ
