አበበ ገላው እንደ የ ቪ ኦ ኤው ሄኖክ ሰማእግዚአብሔር!
ቆቤን አንስቼ ለኢሳቶቹ ለምናላቸው፤ ለኤርምያስ እና ለሃብታሙ እጅ እነሳለሁ!
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)
የኢትዮ-ሰማይ ተከታታዮች እንደምታስታውሱት ‘ኢሳትን’ ስቃወም እንደነበር የምታውቁት ነው። የተቃወምኩባቸውንም ምክንያቶች በርከት ያሉ በብዙ ምክንያቶች አስደግፌ ነው። ዛሬ፤ ዛሬ በቅርቡ ኤርምያስ ለገሰ፥ ሃብታሙ አያሌው፤ ምናላቸው ስማቸው፥ ተወልደ በየነ (ተቦርነ) እና እየሩሳሌም ተ/ክለጻድቅ እና የአውሮጳው ካሳሁን የልቤን እየተናገሩልኝ ቀልቤን በመስለባቸው ያለወትሮየ ኢሳትን ለማመስገን በቅቻለሁ።
ሲሳይ አገና በዘር ጽዳት እና በብዙ ሰብኣዊ ወንጀል እጃቸው የጨቀየ የዛሬ ወጣቶችን በዘረኝነት እንዲታነጹ ያደረጉ፤ የአገራችን ቋንቋ በላቲን ፊደል እንዲተካ ያደረጉ አፍሪቃዊ ስሜት የራቃቸው “ማፈሪያዎች” ‘ኦነግ እና የመሳሰሉ ብዙ ሰዎችን በግድያ እና በዘር ማጥፋት የተካፈሉ የድርጅት መሪ ወንጀለኞች ሁሉ ለመንግሥት ተብየው (የኦሮሞዎቹ አብይ አሕመድና የትግሬዎቹ የወያኔ አፓርታይድ ጥምር መንግሥት) በማሳሰቢያ መልክ “ልዩ ክብር እና የሚጦሩበት ድጎማ/ጡረታ” ይሰጣቸው ሲል የተከራከረውም ሆነ “እኔም ግንቦት 7 ነኝ ሲለን የነበረው ዛሬ ደግሞ እኔም አብይ ነኝ!” ለማለት እየቃጣው ያለው እውቁ ጋዜጠኛ አበበ ገላው (ሁለቱም የኢሳት ጋዜጠኖች) ከላይ የተጠቀሱ ምርጥ ጋዜጠኞችን ባይቀላቀሉዋቸው እና ሁለቱ ከኋላ ተቀምጠው ዜናን የማንበብ ስራ ቢሰጣቸው ለጣቢያው ጥራት ይሰጣል የሚል ምክር አለኝ።
ኤርምያስ እና ሃብታሙ የራስ ቆቤን አውርጄ በአክብሮት ሰላምታ ከማመስገን በላይ በምን ቃላት ላመሰግናችሁ እንደምችል ጨንቆኛል። አብይ የተባለ እጅግ የተካነ “ካን አርቲስትን” (የሕሊና ሰላቢን) በማጋለጥ የታወቀው የኔ ጀግና ብየ የሰየምኩት ‘ቴድሮስ ጸጋየ” (የርዕዮት አዘጋጅ) ልቤን ቅቤ እያስጠጣ ሲያርስልኝ ከርሞ፤ በቅርቡ ደግሞ እስክንድር ነጋ ወደ ፊት በመምጣት የኦነግን “ትግል ወራሽ” የሆነው አብይ አሕመድ(በአብይ ተከታይ ኦሮሞው ዶ/ር ብርሃነመስቀል አባባል) እንዲሁም ዋናው ‘ኦነጉ’ ለማ መገርሳ የተከናነቡበትን አሳሳች “ጭምብላቸውን” አስወልቆ “ወደ ለየለት ጦርነት እንገባለን“ እስኪሉ ድረስ “የደበቁትን ባሕሪያቸው” አዳራሽ ውስጥ በቁጣ ፈንድቶ ለትዝብት እንዲዳረጉ ያደረጋቸው ቆራጡና ምክንያታዊው እስክንድር ነጋ ያረካኝን እያጣጣምኩ ሳልጨርስ፦- ተጨማሪ እርካታ በመጨመር “የፋሺሰቶቹ የወያኔዎቹ የስለላው መዋቅር (ኢንሳ) ዋና ቀያሽና አስተማሪ የነበረው ኮለኔል አብይ አሕመድ/ዛሬ ጠ/ሚኒስቴር/” ማስረጃ በማያልቃቸው በእነዚህ የቁርጥ ሰዓት ልጆች እነ ኤርምያስ ለገሰ፤ ሃብታሙ አያሌው፤ ምናላቸው ስማቸው ፤ተወልደ በየነ (ተቦርነ) ካሳሁን እና እየሩሳሌም ተ/ክለጻድቅ የብዙ ተፈናቃይ እና የብዙ እናቶች እምባ እያስደመጣችሁ ለነዚህ ዜጎች ቆማችሁ የአብይን ከንቱ ውዳሴ እና “ፕሮፓጋንዳ” በማጋለጥ ክንብንቡን በማስወለቅ “ንጉሡ እርቃኑን” እንዲታይ በማድረግ እርሱና ተባባሪዎቹ ውስጠ ገበናቸውን በማጋለጣችሁ ያለኝን አክብሮት በድረገጾች ላስተላልፍላችሁ እወዳለሁ።ሲመሰገን የሚቀብጥና የሚቦጠረቅ፥ ሲነቀፍ ደግሞ “የሚቆጣ” አስገራሚ ንጉሥ እንደ አብይ አላየሁም። እናንተ ግን ምንነቱን መጋለጥ ሲኖርበት እንዲጋለጥ ፥ መመስገን ባለበት እንዲመሰገን መጣራችሁ ጨዋነታችሁ አሳይታችሁታል። እርሱ ግን አልገባውም። …… (Read more)
