April 1, 2019

Source: http://amharic.abbaymedia.info/archives/46575

ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY

“ለተገፋ ሁሉ ፍርድ እንዳይታጣ፣

ድመት ሌሊት አይሂድ፣ አይጥም  ቀን አይምጣ፡፡”

ኢሣት በኢትዮጵያ የፖለቲካ፣ኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳዬች ያላሰለሰ የመረጃ ምንጭ በመሆን ድምፅ ለሌላቸው ድምፅ በመሆን ሲያገለግል አመታት አስቆጥሯል፡፡  ሆኖም ኢት-ኢኮኖሚ/ /ET-ECONOMY መጣጥፎች ከአገር ውስጥ የምጣኔ ኃብት ሙያተኞች በተለያዩ ድረ-ገፆች ማለትም በሳተናው፣ አባይ፣ ዘሃበሻ፣ ኢትዮጵያ ኤክስፕሎለር፣ አትዮሚዲያ ወዘተ ድረገፆች ለብዙ አመታት ሽፋን አግኝቷል፡፡ ከማንም በላይ ብዙ አንባቢዎች ለማግኘቱ የድረ- ገፆቹ ባለቤቶች ምስክርነታቸውን ሊሰጡ ይገባል እንላለን፡፡ ኢት-ኢኮኖሚ/ /ET- ECONOMY ለኢሣት ጋዜጠኞች ለአበበ ገላውና ሃብታሙ አያሌው እንዲያሳትመው በመፍቀድ፣ በዛ ክፉ ዘመን የደረሰ ጥናታዊ መጽሃፍት ሲሆን በኢሣት ፕሮግራሞች አልቀረበም፡፡ የኢት- ኢኮኖሚ ፁሁፎችና መጽሃፍቶች  በብዙ ድረ-ገፆች ሽፋን ያገኙ ሲሆን በኢሣት አለመቅረባቸው የመረጃዎቹ አስተማኝ ስላልሆኑ ታስቦ ከሆነ  መልስ ሊሰጥበት ይገባል እንላለን፡፡ የኢት-ኢኮኖሚ ዋነኛ ዓለማ በኢኮኖሚው ዘርፍ ለሃገርና ለወገን በማስረጃ ላይ የተመሰረተ ጥናታዊ ፁሑፍ በማቅረብ በተለያዩ ድረ-ገፆች ተደራሽነት በማግኘታችን ደስተኛ ከመሆን ሌላ እስከመቃብር እውቅና የማንሻ በብዕር ስም ብቻ የምንታወቅ ስንሆን ከአመታት በፊት፣ ከለውጡ በፊት፣ ኢሣት በምጣኔ ኃብት የቀረቡ መጣጥፎችን ባለማስተናገዱ፣ የተጎዳው የሃገራችን ህዝብና ምሁራን ሲሆኑ አበበ ገላውና ሃብታሙ አያሌው እጅ የሚገኘው መፅኃፍት ጥናታዊ ሥራ  ዛሬ  በተለያዩ ድረ-ገፆች ተለቀው በመነበብ ላይ ሲሆኑ፣ የጋዜጠኝነት ሥራችሁን ባለመወጣታችሁ ገንቢ ሂስ ለማቅረብ በማሰብ ከዓይናችሁ ጉድፍ ለማውጣት የታለመ ነው፡፡ በጋዜጠኝነት ሥራና ሙያዊ ሥነ-ምግባር፣  ግልፅነት፣ ታማኝነትና ተጠያቂነት ዋነኛዎቹ መገለጫዎች ናቸው እንላለን፡፡ ኢሣት መረጃ ከውስጥ ላበረከቱ ጸሃፊዎች ምስጋና ቢቀር እንደ ነፃ ሚዲያ የማቅረብና የመዘገብ ሥራ ልክ እንደ የኢትዩጵያ የመረጃና መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ (INSA) ከሃገር ውስጥ የተላከ መረጃ ኢሣት ያለ በቂና ሚዛናዊነት በጊዜው አለመዘገቡ በጋዜጠኛ አበበ ገላው የቀረበው ትንተና አሳማኝ ሆኖ አላገኘንውም፡፡ ከሰባት አመታት በፊት በኢሣት ጋዜጠኞች መረጃው ይቅረብ አይቅረብ የነበረ ክርክር ይፋ ቢደረግ ታላቅነታችሁን ያበስርላችኋል እንላለን፡፡ የኢት-ኢኮኖሚ/ /ET- ECONOMY ሥራዎችን በኢሣት በፕሮፌሰር ጌታቸው በጋሻው እና በኢሳት የቀድሞ የሠራዊቱ ድምፅ ስለ ኢፈርትና ሜቴክ በተከታታይ ጹሁፋችን እንደቀረበ ለማመስገን እንወዳለን፡፡  ኢሣት በነዚህ መረጃ አቅራቢዎችን ለምን እንዳላስተናገዱና የመረጃ ምንጩ አስተማማኝ ይሁን አይሁን የሚለው የማምለጫ አብዶ መለኪያው  ምን እንደሆነ በግልፅ ካልተቀመጠ  ከሃገር ቤት መረጃ የማግኘት ገመዳችሁ ይቆረጣል እንላለን፡፡ ኢሣት አገርቤት ገብቶል፡፡

‹‹ከጥንት ጀምሮ እኛ የምናውቀው፣

 ሲነድ ሲቃጠል የሚስቅ እሳት ነው፡፡ ባለቅኔ ኃይሉ ገብረህይወት /ገሞራው

‹‹የህወሓት/ ኦህዴድ የኢንሣ ጡሩምባ፣ መሬት ቀዶ ገባ!!!››

የኢንሣ ወንጀለኞች ለፍርድ ይቅረቡ!!

የህወሓት/ኢህአዴግ ወንጀለኞች ለፍርድ ይቅረቡ!!

ጅብ ከሚበላህ ጅቡን ብላውና ተቀደስ!!!