April 1, 2019
በዚህ ጽሁፍ ስለ ሰላዩ ኤርሚያስ ለገሰና ስለስለላ ሴራዎች ግንዛቤ፣ ስለ ዜጎች ጥቃትና ስለ ሴረኞች እንቅስቃሴ አነሳለሁ፡፡
የቀድሞው የበረከት ስምዖን አገልጋይና የሕወሀት ቅጥረኛው የዛሬው በኢሳት የሕወሐት ተወካይ ጋዜጠኛ አይሉት ብቻ የሆነ ነገር ግን በኢሳት ዋና የኢትዮጵያ ተንታኝ እንደሆኔታው ቃለመጠይቅ አድራጊ ምናምን የሆነው ኤርሚያስ ለገሰን አስመልክቶ ሰሞኑን አንድ ይገረም አለሙ የተባለ ሰው ጥርጣሬውን በዚህ ግለሰብ ላይ የተነተነበትን ጽሁፍ አነብቤ ነበር፡፡ ይገረም መሠረታዊ እውነታውን ከመናገር ውጭም የተናገረው ነገር አልነበረም፡፡ ስለዚህ ኤርሚያስ ለገሰ ስለተባለ ሰው እኔ ከዚህ በፊት የራሴን እየታ ሰጥቻለሁ፡፡ ለይገረምም ለእኔም ተመሳሳይ በሚመስሉ ሰዎች እነዴት ኤርምያስን ትናገራላችሁ አይነት ብዙ ተናግረዋል፡፡ እኔም ሆንኩ ይገረም ስለምናነሳው የወያኔው ሰላይ ኤርምያስ ለገሰ ጉዳይ ግን በምክነያትና በመረጃ ተሳስታችኋል ሊል የቻለ የለም፡፡ በአጭሩ ስለማይችል ነው፡፡ ኤርምያስ ለገሰ የወየኔ ሚኒስቴር ዴታ ሊያውም የበረከት ማደጎ ለመሆኑ ስህተት የለውም፡፡ ኤርምያስ ለገሰ ኢሳት ውስጥ ዋና የፖለቲካ ተንታኝና መሆኑ ስህትት አደለም፡፡ ኤርምያስ ለገሰ በፖለቲካ ተንታኝነትና በአገኘው አጋጣሚ ሁሉ የሚነዛቸው መርዞችም መረዳት ከቻልን እየፈለጋችሁ ከዬቲዩቡ በአጽኖት ማዳመጥ ነው፡፡ ለዛ ይረዳችሁ ዘንድ ግን ትንሽ ስለ ስለላዊ ሴራዎች ፍንጭ ልስጣችሁ፡፡ ከዛ ብዙዎችን ትታዘባለችሁ፡፡
ወያኔ ሶስት ደረጃ ሰላዮች አሏት፡፡ አንደኛው በቀጥታ ብዙ ኔተወርኮችን የሚቆጣጠሩ ለምንና ለማን እንደሚሰሩ የሚያውቁ ናቸው፡፡ እነዚህ ከበታችም ከበላይም ያሉትን በግልጽ ያውቀሉ፡፡ እነዚህ ብዙውን ጊዜ የሴራ አቀናባሪዎችና ዕቅድ አውጪዎች ናቸው፡፡ በአጠቃላይ የጎንዮሽም ከላይ ወደታችም ያሉትን የእነሱን አባላት ያውቃሉ፡፡ እነሱ ግን በማንም ላይታወቁ ይችላሉ፡፡ በጣም ፊትለፊት በሥልጣናቸው ከሚታወቁት በቀር ማለት ነው፡፡ ሁለተኛው ወደጎን የተወሰኑ ተመሳሳይ ተልዕኮ የተሰጣቸው ጋር ብቻና ለሚያገለግሉት በአብዛኛው አንድ ሰው ጋር የሚገናኙ ናቸው፡፡ የመጀመሪያው ከአገልግሎት ታማኝነት በተጨማሪ ትግሬ መሆንን የሚጠይቅ ነው፡፡ ሁለተኛው ጥብቅ ታማኝ ነው፡፡ ሶስተኛዎቹ ወደጎን ከማንም እንዲተዋወቁ አይፈቀድላቸውም እነዚህ አንዳንዴ ተመሳሳይ ግብ ላይ እየሰሩ በጣም የተጻነፉ ይመስላሉ፡፡ እርስ በእርስ በብዙ አጋጣሚ ይጋጫሉ፡፡ ሁሉም ግን ታዛዥነታቸው ለአንድ ቋት ነው፡፡ ብዙም በአንድም ጥብቅ በሆኑ ከአንድ በላይ አዛዦችም ሊመሩ ይችላሉ፡፡ ከአንድ በላይ አዛዥ ከአለ አዛዦቹ በጣም የሚተዋወቁና ምንም አይነት ሚስጢር ከእነሱ ውጭ እነደማይወጣ ያረጋገጡ ናቸው፡፡ አዛዦቹ ትግሬ መሆን የግድ ይጠበቅባቸዋል ከዛም በላይ ስልጣን ያላቸው መሆን ይጠበቃል፡፡ እዚህ ጋር ሰንሰለቱን ትንሽ ሊያረዝሙት ይችላሉ ግን በምንም መልኩ በሁለተኛው ደረጃ ያለፉ ሳይሆን አነስተኛ ስልጣንም ባይኖራቸው ትግሬ በሆኑ ንዑሳን ሰንሰለቶች እየተዘወሩ ለላኛው የሚሰሩ ነው፡፡ መሀል ያለው በቀጥታ ሳይሆን በእጅ አዙር ነው የሚዘውራቸው፡፡ በዚህ ሴራ የሚሳተፉ ሰላዮች አደገኛና በጣም አምታች ናቸው፡፡ አንዳንዴም እራሳቸው የድርጊት አከናዋኝ ናቸው እንጂ በቀጥታ በመታዘዝ አደለም፡፡ ድርጊቱን የሚፈጽሙት ግን በሌሎች በመዘወር ይሆናል፡፡ ኤርምያስን የቱ ጋር ነው የምናገኘው ከአላችሁ ሁለተኛው ላይ ነው፡፡ እሱ የሚሰራው ለታመነበት የታወቀ ሰንሰለት ነው፡፡ ወደጎንም የተወሰኑ ሰዎች አሉት፡፡ እነዚህ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ያሉት አንዳንዴ እርስ በእርስ የሚቃረን ያወሩ ይሆናል እነዚህ ግን እንደሶስተኞቹ በሌሎች በመነዳትና የምር ሳይሆን ሆን ብለው እርስ በእርስ ተግባብተው ነው፡፡ ሶስተኞቹ እንደዚህ አደልም፡፡ ተቃራኒ የሚሆኑት በሌሎች በመዘወር ነው፡፡ ለዚህ እንደ ምን አልባት እንደምሳሌ ሊሆን ከቻለ አላውቅም ግን የ1997ቱ ቅንጅት ውስጥ የነበረው ሴራ ይህ ነገር ይነበብበታል፡፡ በተለይ ልደቱና ብርሀኑን በደንብ ከአስተዋላችሁ የዚህ ሴራ አስፈጻሚዎች ነው የሚመስለው ሁኔታቸው፡፡ ፕ/ር መስፍን ወ/ማሪያም ዘዋሪው ከላይ ከአሉትና ሌሎች ኔትወርክን ያጣመረ ማቀናበር የሚሰሩ ይመስላል፡፡ ድራማውን ከቻላችሁ እንደገና አስተውሉት፡፡ ከእነዚያ ቡድን ብርቱካንና ኃይሉ ሻወል ከተሸወዱት ይመስላሉ፡፡ ብርሀኑና ልደቱ አይተዋወቁም ግን ለአንድ አላማ እንዲሰሩ የተቀናጁ ናቸው፡፡ ሁለቱም ግን በጋራ እንድ ከላይ የሚያውቁት አካል አለ፡፡ ልደቱ የሱን የበላይ ብርሀኑ እንደሚያውቅ ብርሀኑም የእሱን የበላይ ልደቱ እንሚያውቅ ፈጽሞ እንዲያውቁ አይፈቀድም፡፡ ብርቱካን እስከመጨረሻው እንደተሸወደች ጸንታ ነበር ኃይሉ ሻወልን ከነጠሏቸው በኋላ በግል በንብረት መጡባቸው እሳቸውም አርፈው ተቀመጡ፡፡ ኃይሉ ሻወል ወደ ማይቀረው፣ ብርቱካን ወደ አሜሪካ፣ ልደቱ፣ ብርሀኑና መስፍን ግን እስካሁንም ከወያኔ ጋር እንደቀጠሉ ነው እኔን የሚገባኝ፡፡ እስካሁንም ልደቱና ብርሀኑ ሶስተኛው ደረጃ ናቸው፡፡ መስፍን የመጀመሪያው ደረጃ ላይ ከአሉት ቀዳሚዎቹ ናቸው ብዬ ነው የምገነዘበው፡፡ እነዚህ ምሳሌ እኔ እንደተገነዘብኩት ከጠቀስኩ ወደ ተነሳሁበት፡፡
የኤርምየስ ለገሰን ነገር ራሳችሁ እንድታስተውሉት ልተውላችሁና ሰሞኑን በተለያየ ቦታ አማራ በተባለው ሕዝብ ላይ እየተደረገ ያለውን ሴራ ላስጎብኛችሁ፡፡ እኔ የነገሮችን ትንታኔ እንጂ ፖለቲካዊ ትንታኔ አድለም የምሰጠው፡፡ ግን በተቻለኝ ጥልቀት ነገሮችን አያለሁ፡፡ ለዛ ደግሞ ዝንባሌው ያለኝ መሰለኝ፡፡ ለማንኛውም የሰሞኑ በአማራ ሕዝብ ላይ የአነጣጠረ ሴራ በሶስተኛው ደረጃ ተቀጥረው ለወያኔ ቡድን ከሚሰሩት ሰላዮች ጋር የተያያዘ ነው፡፡ የቤኒሻንጉሉ ሲገርመን(አድስ ባይሆንም) እዛው አዲስ አበባ አፍንጫ ላይ ምዕራብ ሸዋ ዳኖ(ጊንጪ) አማራ የተባሉ ዜጎች በማንነታቸው ከመሬታቸው ተባረው ሰማን፡፡ የወረዳው ተወካይ ተብዬው ነው አሉ ደግሞ ይሄንን ውሳኔ ያስተላለፈው፡፡ ውሳኔውም የአማራ ተወላጆችን ከመሬታቸው በማፈናቀል ለወጣት ኦሮሞ ተወላጅ መሬታቸውን መስጠት ነበር፡፡ ከአልደፈረሰ አይጠራም፡፡ ለመሆኑ ይሄ የወረዳ ተወካይ ተብዬ ማን ነው? የወረዳው ተወካይስ እውን በትክክል እንዲህ ያለ ውሳኔ አስተላልፏል ወይ? ልብ በሉ በአለፈው በቤኒሻንጉል አንድ የቀበሌ ሊቀመንበር ነው ደብዳቤ ጻፈ ተብሎ ሲሰራጭ የነበረው፡፡ በአለፈው እኔ በኦሮሚያ እንዲህ ያለ ነገር አይከሰትም የሚል እምነት ጥዬ ነበር፡፡ ግን ሳይውል ሳያድር ይሄው ሰማን ሊያውም አዲስ አበባ አፍንጫ ስር ዳኖ(ጊንጪ)፡፡ እሺ የወረዳው ተወካይም እንደ ቤኒሻንጉሉ ቀበሌ ሊቀመንበር የሆነ አማራን ከአካባቢው የማባረር ውሳኔ አስተላለፈ እንበልና ግን በማን ትዕዛዝ? ይህ ጉዳይስ ከመጀመሪያው ችግሩ በማስጠንቀቂያ እያለ ለምን አልተሰማም? ለምን ችግሩ ከተፈጠረ በኋላ አዲስ አበባ ላይ ገበሬዎቹ ከእነ ሕጻን ልጆቻቸው ሳይቀር ከተበተኑ በኋላ ተሰማ፡፡ ልብ በሉ የምናወራው ጠረፍ ስላለ አካባቢ አደለም፡፡ ለአዲስ አበባ በጣም ቅርብ ስለሆነችው የዳኖ ወረዳ እንጂ፡፡ መቼም የሆነ ሂደት ነበረው ብዬ አምናለሁ፡፡ እኔ የሄን ጉዳይ የአማራ ችግር ሆኖ ፈጽሞ አልታየኝም፡፡ ኢላማ እየተደረገ የአለው አሁን እየተገነባ ያለው ኢትዮጵያዊነት ነው፡፡ በተለይም ደግሞ ከ27 በሁለቱ ታላላቅ ሕዝቦች አማራና ኦሮሞ መካከል ጥል ጸንቶ እነዲኖር ሲሴር የነበረው ሁሉ እሳት እንደነካው ሰም እየቀለጠ ስለመጣ እንደገና ጥሉን ለመመለስ የሞትሽረት ሴራ እንጂ፡፡ ይህ በሚሊየን የሚቆጠርን ትግራይን ሕዝብ በረሀብ፣ በተለያዩ የአረመኔ ልምምዶች ጀምሮ በመላ አገሪቱ በልዩ አረመኔያዊ ሴራ ያረጀ የወሮበላው ወያኔ ቡድንና አጋሮቹ ሴራ አንዱ ማሳያ ነው፡፡ በዚሁ ሳምንት የዳንጎቴው ሰራተኞችን ግድያም አስታውሱ፡፡ አንዳንድ የቧህነት ይሁን ወይም እንደገና ሌላ ማደናገር ባይገባኝም የዳንጎቴውን ሥራ አስኪያጅ ግድያን አስመልክቶ ሥራአስኪያጁን በግል ኢላማ የደረገ ነው ሲሉ ይሰማሉ፡፡ ከዳንጎቴ ጋር የወሮበላው ቡድን አባላት ከአላቸው ሽርክናም ጋር እንደሚያያዝ ለማስመሰል ተሞክሯል፡፡ በእኔ ግንዛቤ ይሄ ትክክል አይደለም፡፡ ኢላማ እየተደረገ ያለው አሁንም ኢትዮጵያዊነት ላይ ነው፡፡ በአጠቃለይ አሁን እየተደረጉ ያሉ ሴራዎች ኢላማ ያደረጉት የአብይን ሥልጣንና አካሄዱ ላይ ነው፡፡ ከአብይ ቁጥጥር ውጭ ነገሮች እንደሆኑ ለማሳየትና በሕዝቦች ልብ ጥርጣሬን ለመፍጠር ቀጥሎም የሚገኘውን አጋጣሚ ሁሉ ለመጠቅ ነው፡፡
ወደመሬት መፈናቅል ጉዳይ እንምጣ እኔ ብዙ ጊዜ ተናግሬአለሁ ብዙዎች ሕገመንግስት ተብዬው የመለስ የጥንቆላ ሰነድ አፈጻጸም እንጂ ሕገመንግስቱ ችግር የለበትም ሲሉ ይገርመኛል፡፡ ዜጎች ከክልላቸው ውጭ ተዘዋውረው የሥራት መብታቸው በዋናው ህገመንግስት ተብዬው የጸደቀ ይመስላል፡፡ ግን እኮ ዜጎች በሌሎች ክልልሎች ሁለንተናዊ መብታቸው የዘር ፌደራሊዝሙ ላይ ነው፡፡ ቀጥሎም በግልጽ በክልሎቹ ሕገመንግስት ከክልሉ ተወላጆች ውጪ ያሉት ምንም አይነት ስልጣን የለቸውም፡፡ በሄዱበት ክልል የሚኖሩት በእንግድነት እንጂ በዜግነት አደለም፡፡ በድንበር አካባቢ ደግሞ እርስ በእርስ እንደሁለት አገር ባለአንጣ ሕዝቦች እርስ በእርስ እንዲጫረሱ ተደርጎ ሆን ተብሎ የተሰራው የፌደራሊዝም ሥርዓትና ሕገመንግስት እኮ ነው ዋናው ችግራችን፡፡ የመጨረሻው ጥያቄዬ ለመሆኑ ማን ነው በአለመሬት ማን ነው መጤ?ደቡብ አፍሪካን አስተውሉ፡፡ ነጮቹ ዛሬ ጥቁሮቹን እየሰጧቸው ያለው መልስ ደቡብ አፍሪካ አገራችን ነው ነው፡፡ በጣም ትክክል ናቸው፡፡ ዛሬም ጥቁር ደቡብ አፍሪካዊ መጤ ይላቸዋል፡፡ አገሪቱን ግን አገር ሆና እንድትቀጥል እየሰሩ ያሉት ነጮቹ ናቸው፡፡ ጥቁሮቹ የአገሩ በአለቤተ ነን ብሎ ከመደንፋት በቀር የተፈጠረውን ኢኮኖሚ እንኳን ጠብቆ በሚያቆይ ሁኔት አይሰሩም፡፡ በዛም ምክነያት ዛሬም እድሉ ተፈጥሮላቸው ሳለ ባሮች ናቸው፡፡ ይልቁንም ከሌላ አገር እንጀራ ብለው ደበብ አፍሪካ የገቡ ብዙ አፍሪካውያን ስኬታማ እየሆኑ ነው፡፡ በዛው ልክ የአገር በአለቤት ነን ባዮቹ የደቡብ አፍሪካ ጥቁሮች የተሳካላቸውን የሌሎች አፍሪካ ዜጎችን በቅናት መንፈስ ከአገራች ውጡ በሚል ስንት አረመኔያዊ ድርጊት ሲፈጽሙባቻ እናያለን፡፡ አገሪቱ እኮ እነዚህ እየሰሩ ራሳቸውን ለስኬት ያደረሱ ሰዎች ጠቅልለው ቢወጡ መቀጠል ላትችል ይሆናል፡፡ በየትኛውም ክልል በማንነቱ ምክነያት ጥቃት እየተፈጸመበት ያለ የእኛው ዜጋ እንደ ጥቁር ደቡብ አፍሪካውያን ቅናት በአደረባቸው በዘረኝነት ልክፍት ባሪያ የሆኑ ናቸው፡፡ ከዚህ በኋላ አብይ የተናገረላትን ኢትዮጵያ መመለስ ከቻለ(ብቻውን ማለቴ ሳይሆን በመሪነት ነው) እሰየው በየትኛው እንዲህ ያሉ ሴራዎችን የሚያራምድ ግለሰብም ይሁን ቡድን ላይ የማያዳግም እርምጃ መውሰድ በቂ ነው፡፡ ዛሬ ላይ ለዚህ በቂ የሆነ የሕዝብ ድጋፍ አለ፡፡ ይህ አልሆን ከአለም ራሳቸው ተጠቂዎቹ አጥቂዎቹን ከየት የመጣህው መሬት ነው የሚል አቅምን መፍጠር አለባቸው፡፡ ሕግ በሌለበት ሁኔታ መፈራት አማራጭ ነውና፡፡ ከዚያም አልፎ ሌላ በእነሱ ላይ የሚሸረብን የሚያመክን ሌላ ልዩ ስልት ሊነድፉ ይገባል፡፡ እኔ የምመክረው አለኝ ግን እዚህ አልናገርም፡፡
ሰሞኑን ሌላ የሰማሁት የሕዝብ መወያያ መድረክ ተብሎ በሻራተን አዲስ የተደረግን ውይይት ነው፡፡ አብይ ሆይ እንዲህ ያለ የሚያምታታ ውይይት ቢቀርብህ ነው የሚሻለው፡፡ አንዱ አማራ ነገር መሰለኝ ተነስቶ እምዬ ሚኒሊክ አለ፡፡ ብቻ ታሪኩን በውል ከማስጨበጥ ይልቅ ቋትኝ ቋጥኝ በሚያህሉ ቃላቶች አጅቦ ተሰብሳቢውን ለማስበርገግ ሞከረ፡፡ ቀጠለና አንዱ የታሪክ ጉዳይ ከአነሳን ወደማንፈልገው ጭቅጭጭቅ ነው የሚከትን የሥርዓት ችግር ነበረ አሁንም አለ ሲል ደመደመ፡፡ ይሄው ተናጋሪ ግን ስለሕገመንግስቱ ሴራዎች አንዳንድ ነጥቦችን አቅርቦ ተናገረ፡፡ ቀጥላ አንድ ሴት ከጂማ ዩኒቨርሲቲ ነኝ ያለች ሕገመንግስቱ የአለበት የአፈጻጸም ችግር ነው ብላ ደመደመች፡፡ የፌደራል ሥርዓቱንም ደገፈች፡፡ እሷው የኦሮሞ ከሱማሌ መፈናቀልን ምርር ብላ ተናገረች፡፡ እያለ ሌላው ቀጠለ፡፡ ዝም ብሎ ለሰማቸው እሺ ምንድነው ሊያወሩ የፈለጉት ከማለት ውጭ ይሄ ነው የሚለው እንድም መፍትሔ አያገኝም፡፡ እስኪ ከጠቀስኳቸው ከሴቷ ልነሳና ጥቂት ልበል፡፡ የጂማዋ ዩኒቨርሲቲ መምህርት የኦሮሞዎች ከሱማሌ መፈናቀል ምክነያቱ ምን ነበር ተብላ ብትጠየቅ የፌደራል ሥርዓቱ የአፈጻጸም ችግር ነው ከማለት አትመለስም፡፡ እሷ ኦሮሞ ስለሆነች የድመት አይን ምን ያያል ቢሉት አይጥ እንደተባለው ነው እይታዋ፡፡ ያሳዝናል፡፡ እሺ የአማራዎችስ ከበደኖ ጀምሮ፣ ከጉራ ፈርዳ፣ ከቤኒሻንጉል ይሄው ዛሬ ደግሞ ከዳኖ ብትባል ይሄ ትክክል ነው ከማለት የማትመለስ አይነት እይታ ውስጥ ነች፡፡ የዩኒቨርሲቲ መምህሯ፡፡ የታሪክ ጉዳይ አናንሳ ባዩ ተናጋሪ ከሕገመንግስቱ ጠቅሶ ያነሳቸውን ጉዳዮች በጣም ወድጄለት ግን የታሪክን ጉዳይ አናንሳ የምትለዋ መሸፋፈኛ ተናጋሪውን መሠረት የሌለው የራስን ፍላጎት አንጸባራቂ ያስመስለዋል፡፡ ታሪክ የሌለው አገርና ህዝብ ልፍስፍስ ነው፡፡ ታሪክ የዜጎች ልበሙሉነት መሠረት ነው፡፡ ታሪክ ሳይኖረው አለም ላይ ትልቅ የሆነ አገር አላየነም፡፡ ወጣቶቹ እነ አሜሪካ ሳይቀሩ መሠረታቸው ታሪክ ላይ ነው፡፡ የታሪክም ትምህርት በእነዚህ አገሮች ግዴታ እንጂ አማራጭም አደለም፡፡ በመልዕክቱ ግን ሻል ይላል፡፡ እምዬ ሚኒሊክ ባዩ ደግሞ የዩኒቨርሲቲዋ አይነት ነው፡፡ እሷ ኦሮሞ ነበረች ይሄ ደግሞ አማራ ነው፡፡ በቃ ለዚህ ሰው ደግሞ ወደ አንድ ሚሊየን የተጠጋው ተፈናቃይ ኦሮሞ አይታየውም፡፡ ታሪክም አነሳ የጥል ሀውልት ይፍረስ ከማለት ውጭ ተጨባጭ እውነታን መናገር አልቻለም፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ እምዬ ያላቸውን ሚኒሊክን እንዴት ትነቅፋላችሁ አይነት ነው፡፡ እኔ በሚኒሊክ ላይ ያለኝን አቋም ብዙዎች ታዎቃላችሁ፡፡ በዚህ አይነት ግን ሚኒሊክን ማወደስ አልፈልግም፡፡ በአጠቃላይ የዛን ውይይት ሂደት ስትመለከቱት በህዝባዊ ውይይት ሥም ውዥንብር መፍጠር ነው፡፡
በዚሁ ሳምንት አብይ ሳውዲአረቢያን ጎብኝቶ ከተመለሰ በኋላ ለወጣቶች ያደረገው ንግግር ጥሩ ከሚባሉ ነው፡፡ እይታውንም ቁጭቱንም ወድጄዋለሁ፡፡ በተለይም የተጓዘበትን አላማ ያነሳበትን፡፡ ምን ትፈልጋላችሁ ሲሉን ዜጎቻችንን ፍቱልን አልናቸው፡፡ እኛ ዜጎቻችንን ስናከብር እነሱ ያልጠየቅንውን ጨምረው ሰጡን፡፡ ይህ ጉዳይ ትልልቅ ግንዛቤ ነው፡፡ አዎ ዜጎች በመሪዎቻቸው ሲከበሩ በሄዱበት ሁሉ ይከበራሉ፡፡ በኃይለስላሴ ጊዜ ለትምህርት የተላኩ ኢትዮጵያውያን በሄዱበት ሁሉ ትልቅ ክብር እንደነበራቸው ይነገራል፡፡ ዛሬ ኢትዮጵያውያን ከባርነትም በታች ዕቃ ሆነዋል፡፡ በተለይ አረቡ አገር፡፡ እነዚህ ዜጎች የሚፈለጉት ዶላር ለማምጣት ኤክስፖርት የተደረጉ ዕቃዎች እንጂ እነዜጋ ይቅርና እንደሰውም አደልም፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ አብይ ስለሳውዲ አረቢያ እቅድ አድንቆ ሲያወራ ሰምቻለሁ፡፡ ለእኔ ብዙ አያስደንቀኝም፡፡ ለእኛ ሳውዲ አረቢያም ጥሩ ምሳሌ አደለችም፡፡ እኛ ምሳሌ ማድረግ ከአለብን የሩቅ ምስራቅና(ቻይና፣ ኮሪያ፣ ጃፓን) ህንድን ነው፡፡ በተፈጥሮ የጭንቅላት ችግር ያለብን አይመስለኝም፡፡ ችግሩ አራሙቻ በቀለበት እንጂ፡፡ ከ50 ዓመት ጀምሮ የተነሳው አስተሳሰብ ብዙ ዓመት ወደ ኋላ መለሰን፡፡ አብይን አሁን የሚለውን እንዲያስብ ያስቻለው የ60ዎቹ ትውልድ አለመሆኑ እንጂ ከ60ዎቹ ትውልድ አንዱ ቢሆን ዛሬ እያሰበው ያለው የማይረባ በሆነበት ነበር፡፡ አብይ ለራስህ አስበው፡፡ አሁንም ቢሆን ጨለምተኛው የ60ዎቹ ትውልድ አስተሳሰብ እስካልተላቀቅን ብዙ ፈተና አለ፡፡ ግን እየወጣንው መሠለኝ እድሜም ከ60ዎቹ ትውልድ ኢትዮጵያን ነጻ እያደረጋት ይመስላል፡፡
በመጨረሻ አብይ ሆይ የመሪነት ቁርጠኝነቱን ከአፋጠንከው በየትኛውም ደረጃ ልናግዝህ የምንችል አያሌ ዜጎች እንዳለን አትዘንጋ፡፡ እኔ በሙያዬ ኢትዮጵያን ትልቅ ሊያደርጋት የሚችል ሀሳብ አለኝ፡፡ ይህን የምለው ከልብ እንጂ ለማለት አደለም፡፡ አሁን አነት እንደምታስበው እድል መስጠት ከቻልክ በትክክልም የኢትዮጵያ ዕድገት ጉዳይ በፍጥነት የሚሳካ ይሆናል፡፡ በአየኋቸው አገሮች ሁሉ አንድ ሚስጢር ነው ያለው፡፡ እሱም ራስን ከምንም በላይ ከፍ ማድረግና አንሶ ላለመገኘት የሚደረግ እሽቅድምድም፡፡ ጃፓኖች ከጃፓናዊ በላይ ሰው ያለ አይመስላቸውም፣ ጀርመኖችም እንደዛው፣ ራሺያዎቹ ከሚስጥራነታቸው ጋር በአለም የሚስቁበት ነው የሚመስሉት፣ ጀርመኖቹ እንደዛው፣ ኮሪያኖቹ ከጃፓኖች አናንስም ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ መሠረቶቻቸው ነገስታቶቻቸው ናቸው፣ ታሪካቸው ማለቴ ነው፡፡ ወደ አዲሱ አለም ስንመጣ አብዛኞቹ በኢንገሊዞችና ስፓኒሾች የተያዙ ናቸው፡፡ በተለይ በእንግሊዞቹ ማለት፣ አውስተራሊያ፣ ካናዳና አሜሪካ መሠረታቸውን ከኢንግሊዝ ለቀው አደለም፡፡ እስከዛሬም የካናዳና የአውስተራሊያ ንግስት እየተባለች የኢንግሊዟ ኤለሳቤጥ መሆኗን ልብ እንበል፡፡ በእነዚህ አገራትም እንደ ሕግ ንግስቲቱን ማክበር ዋና የዜግነት ግዴታ ነው፡፡ አሜሪካዊያኑ(ዩኤስ) ምን አልባት የጀርመኖችም ተጽኖ ስላለ ነው ንግስቲቱ በሕጋቸው ያልኖረችው፡፡ በአጠቃላይ መሠረትና ምልክት ያስፈልጋል ነው፡፡ የቀደሙ የአገሪቱን መሥራችና ለአገር የቻሉትን ሁሉ ያበረከቱ አባቶችን እናቶችን እየረገምን የእኛ እድገት አይታሰብም፡፡ ለዚህ አብይ አሁን እየሄድክበት ያለው ሂደት ጥሩ መድሀኒት ነው፡፡ ሚኒሊክ ጠላቴ ነው ብሎ የሚያስብ ዜጋ በሞላባታ የሚኒሊክ አገር ሰላምና ፍቅር ብልጽግና እንዲቀጥል የእነዚህን ዜጎች አእምሮ ማከም ተቀዳሚ ሥራ ነው፡፡
አሁንም በየቦታው የሚታዩ የሴራ ምልክቶችን ሥራቸውን ፈልጎ መንቀል ሌላው ተቀዳሚ ተግባር ነው፡፡ ለዚህ አስቸኳይ የተባለው የወሮበሎቹ ሕግ መነሳት ወሳኝ ነው፡፡ የደህነነትም ሆን የመከላከያ መዋቅሩ ከትግሬ ወያኔ የጸዳ ማድረግ ሌላ ነው፡፡
ልዑል እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ዜጎቿን ይርዳ! አሜን
ሰርፀ ደስታ
