ሁሌ እናስታውሳቸው
ተቀብሮ እንዳይቀር
አኩሪ ታሪካቸው!!!!!
እፀገነት ሰብሉ ማን ናት??

በ የካቲት 66 ዓ.ም በፈነዳው አብዮት ጨቋኙንና አምባገነኑን ስርአት ታግለው ህዝባዊና ዲሞክራስያዊ ስርአት ለመመስረት፤ በኢሕአፓ ስር ሴቶች በስፋት ተደራጅተው ያደረጉትን ገድል ስናስብ እንደ እፀገነት ሰብሉ ያሉትን ጀግና ወጣቶች ከታሪክ መሃደር እያገላበጥን ማስተዋሳችንና ላሁኑ ትውልድ ማስተላለፋችን የግድ ይላል።
ከንግድ ስራ ኮሌጅ ተመርቃ በብሄራዊ ትምባሆ ሞኖፖልና በሼል ኩባንያ ሰራተኛ የነበረችው እፀገነት ሰብሉ በሰራተኛ መሃበር ውስጥ ተሳትፋ ለሰራተኛው መብት ታግላለች፤ ከፍተኛ የማደራጀት ስራ በመስራትም አታግላለች። በወጣትነቷም ዘመን ለሃገሯና ለህዝቧ ከፍተኛ ፍቅር ስለነበራት፤ ገና በተማሪነት ዘመኗም በኢትዮጵያ ተማሪዎች እንቅስቃሴ በመሳተፍ በግዜው የነበረውን ፈላጭ ቆራጩን የአፄ ስርአት በፅናት ትግላለች።
እፀገነት ሰብሉ በኢሕአፓ ውስጥ በነበራት ከፍተኛ ተሳትፎ አይን ተጥሎባት በፋሺስቶች ለእስር ተዳርጋ ከሰው ልጅ አቅም በላይ የሆነ ስዬል ተፈፅሞባታል። ገላዋ ተተልትሏል፤ የእጅና የእግር ጥፍሮቿ በጉጠት ተነቅለዋል፤ ይሄ ሁሉ ኢሰብአዊ ድርጊት እየተፈፀማብትም ሁሉን በሆዷ ችላ ከእፀጋእነት ፊት ላይ ፈገግታ አይለይም ነበር።
ሊገድሏት ከእስር ቤት ሲያወጧትም ወደ እስረኛው ዞር ብላ ” ሞት ለፋሺስቶች! ኢሕአፓ ያቸንፋል!” በማለት ደጋግማ እየጮኽች እየገፈታተሩና እያዳፉ እንደወሰዷት ያይን እማኞች ይናገራሉ። ጀግናዋ እፀገነት ሰብሉ መጋቢት 13 ቀን 1970 ዓ.ም በጥይት ደብድበው ገድለዋት፤ አስከሬኗን ቀድሞ በምትሰራበት በትብባሆ ሞኖፖል በራፍ ላይ ጣሉት። በዚያን እለት ከሰማንያ በላይ የኢሕአፓ አባላትና ደጋፊዎች በጥይት ተደብድበው ተገድለዋል።
ከነዚህም በከፊሎቹ እንደሚከተሉት ናቸው፤..…
1. ሩቅያ አህመድ
2. ጌታቸው አሰፋ
3.ክፍሌ ተስፋ ገብርኤል
4.ግርማ ደምሴ
5.ሰላትዬል ኅ/ሥላሴ
6.አስፋው ተድላ
7. ፍቃዱ ወ/ጊዮርጊስ
8.ትእግስት ዮሓንስ
9.ናደው ደምሴ
10. ቦጋለ ደምሴ
11.ግርማ ማጋጋቲ
12. በቀለ ቶሎሳ
13. ፍሬህይወት ደመቀ
14. የ 14 ዓመቷ ሃረገወይን ደመቀ
15.ተቋመ ደመቀ
16.ጀርጊ ዲናገ
እፀገነት ሰብሉ በአሁኑ ሰአት ከወያኔ ጋር እየተዋደቀ ላለው ወጣት ትውልድ አርአያና ምሳሌ ናት። በጣም እንኮራባታለን!!!!!
ነፍስ ይማር ለጀግኖቻችን!!!
የተለያዩ የህዝብ ልጆችና ሰማዕታት አጭር ታሪክ (BIO)ይቀጥላል !!!
