On Apr 5, 2019

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን እንደገና ለማቋቋም የወጣውን አዋጅ አፀደቀ።

ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ ልዩ ስብሰባው በአዋጁ ላይ የምክር ቤቱ የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሪፖርትን እና የውሳኔ ሀሳብን ተመልክቷል።

በአዋጁ ላይ ብሄርንና ፆታን በተመለከተ በተቻለ መጠን አካታች እንዲሆን የተቀመጠው ክፍል “በተቻለ መጠን” የሚለው አስገዳጅ በሆነ ሀረግ ቢቀመጥ የሚል ሀሳብ ቢነሳም ቀድሞ የነበረው አገላለፅ እንዲሆን ወስኗል።

በአዋጁ ላይ ብሄርንና ፆታን በተመለከተ በተቻለ መጠን አካታች እንዲሆን የተቀመጠው ክፍል “በተቻለ መጠን” የሚለው አስገዳጅ በሆነ ሀረግ ቢቀመጥ የሚል ሀሳብ ቢነሳም የምክር ቤቱ አባላት ልዩነት በመያዛቸው ድምፅ ተሰጥቶ በአብላጫ ቀድሞ የነበረው አገላለፅ እንዲሆን ወስኗል።

የቦርድ አባላት ከቦርድ አባልነት ከተነሱ በኋላ ለሁለት ዓመት ምንም ዓይነት ሹመት እንዳይሰጣቸው የሚል የውሳኔ ሀሳብንም አካቷል።

በአዋጁ እና ውሳኔ ሀሳቡ ላይ የተወያየው ምክር ቤቱ በአራት ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ አዋጁን አፅድቆቷል።

በአዋጁ እና ውሳኔ ሀሳቡ ላይ የተወያየው ምክር ቤቱ በአራት ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ አዋጁን አፅድቆቷል።

ምክር ቤቱ በተጨማሪም የሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስቴርን የ8 ወራት ሪፖርትን ካዳመጠ በኋላ የተሰሩትን ጠንካራና ደካማ ተግባራትን በዝርዝር ገምግሟል።